"ከአፋፍ ከገደሉ ከወንዙ ባሻገር..."
የሚል ስንኝ ያለው፥
ስሜት የሚገዛ፥ ዕፁብ ድንቅ ሙዚቃ ሰምቸልሽ ነበር!
.
ምንድነው አፋፉ፥
ከዝቅታው መሓል ከፍ ብሎ የሚታይ፤
"ልዩ" ኾኖ ያለ፥
ዕይታን የሚስብ እንደ ደማቅ ፀሐይ፤
ተራራ ነው ውበት፥ ምቹ ነው ከፍታ፤
ዕይታው "ክልዔ"፥
መውጣትና መውረድ፥ ግብሩ ሁለት መንታ፤
ከፍታውን አይተሽ፥ "ላይ" መኾን ብትመርጪ፤
ተራራውን ወጥተሽ፥ "አፋፍ" ተቀመጪ...
ግን...
ከወጣሽ በኋላ፥
ቁልቁለቱን ዐይተሽ፥ "መውረድን" አስቢ፤
"የመውደቅን" ሐሳብ፥ በአዕምሮሽ አስገቢ!
ይናዳል ተራራው፥ አለ መንሸራተት፤
ስታምኚው ይከዳል፥ ማንም የለው እምነት!
.
ይልቅ...
አለች አንዲት ጀንበር፥ ከሌሊት እስከ ቀን፤
በልክ የተሰራች፥ ኹሌም የምትሞቀን፤
ሕይወትን ጠባቂ፥ አለች 'ማትፈ'ራ፤
አንቺ ነሽ ጀምበሬ፥ "ጀርባሽ" ነው ተራራ!
ከፍታም ውሸት ነው፥ አይኾንም ዓለሜ ተራራንም ማመን፤
ፍቅርሽ እንዲያደምቀኝ፥ "ተራራዬ" ኑሪ ዕድሜ ነው 'ምለምን!
@amehamarie
የሚል ስንኝ ያለው፥
ስሜት የሚገዛ፥ ዕፁብ ድንቅ ሙዚቃ ሰምቸልሽ ነበር!
.
ምንድነው አፋፉ፥
ከዝቅታው መሓል ከፍ ብሎ የሚታይ፤
"ልዩ" ኾኖ ያለ፥
ዕይታን የሚስብ እንደ ደማቅ ፀሐይ፤
ተራራ ነው ውበት፥ ምቹ ነው ከፍታ፤
ዕይታው "ክልዔ"፥
መውጣትና መውረድ፥ ግብሩ ሁለት መንታ፤
ከፍታውን አይተሽ፥ "ላይ" መኾን ብትመርጪ፤
ተራራውን ወጥተሽ፥ "አፋፍ" ተቀመጪ...
ግን...
ከወጣሽ በኋላ፥
ቁልቁለቱን ዐይተሽ፥ "መውረድን" አስቢ፤
"የመውደቅን" ሐሳብ፥ በአዕምሮሽ አስገቢ!
ይናዳል ተራራው፥ አለ መንሸራተት፤
ስታምኚው ይከዳል፥ ማንም የለው እምነት!
.
ይልቅ...
አለች አንዲት ጀንበር፥ ከሌሊት እስከ ቀን፤
በልክ የተሰራች፥ ኹሌም የምትሞቀን፤
ሕይወትን ጠባቂ፥ አለች 'ማትፈ'ራ፤
አንቺ ነሽ ጀምበሬ፥ "ጀርባሽ" ነው ተራራ!
ከፍታም ውሸት ነው፥ አይኾንም ዓለሜ ተራራንም ማመን፤
ፍቅርሽ እንዲያደምቀኝ፥ "ተራራዬ" ኑሪ ዕድሜ ነው 'ምለምን!
@amehamarie