ለመሆኑ ''ዴል ካርኔጊ ምን ዓይነት ሰዉ ነበሩ?''
እነሆ……🙏💯
⚜ዴል ካርኔጊ ከደሀ ቤተሰብ ነዉ የተወለደዉ። የገበሬ ልጅ ነዉ። በጠዋት ተነስቶ ላሞች ያልባል ፣ እንጨት ይቆርጣል ፣ አሳማዎች ይቀልባል። ይህንን ካከናወነ በኋላ ነበር ት/ቤት ለመሄድ የሚዘጋጀዉ። ይህ አድካሚ ስራ ዴል ካርኔጊን ከአንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ ትምህርቱን እንዲያቋርጥ ምክንያት ሆኖ ነበር።
⚜እንደምንም ኮሌጅ ገባ። አባትየዉ የኮሌጁን ክፍያ ሊከፍሉለት ባለመቻላቸዉ በቀን 62 Miles በፈረስ ጀርባ መጓዝ ነበረበት።
⚜ዘወትር ከሚለብሰዉ ሌላ ቅያሬ ልብስና ጫማ ስላልነበረው ከክፍል ጓደኞቼ ጎን ደፍሮ ለመቆም ጉልበቶቹ ይንቀጠቀጡ ነበር። ቀስ በቀስ የበታችነት ስሜት እያደረበት መጣ። ወጣቱ ካርኔጊ ፈሪና ዓይናፋር ፣ በራሱ የማይተማመን ሆነ። ችሎታዉን በተግባር ለመተርጎም እስከሚያቅተዉ ድረስ ወረደ።
⚜ይህንን የተገነዘቡት እናቱ በክርክር ክበቦች ዉስጥ እንዲሳተፍ አበክረዉ ይገፋፉት ነበር። የሳቸዉን ምክር ተቀብሎ ሞከረ ፣ አልተሳካለትም። የጓደኞቹ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆን አልፎ በሁለት እግሩ ሊቆም አልቻለም።
⚜በየክበቡ እየገባ ብዙ ከሞከረ ፣ ብዙ ከወደቀ በኃላ በመጨረሻዉ ተሳካለት። ይህ ድል ለተሳካ ኑሮ የሚያስፈልገዉን በራስ መተማመንና በሚያደርጋቸዉ ነገሮች እርገጠኛ መሆንን አስገኘለት። በአንድ ዓመት ዉስጥ የተለያዩ ክርክሮችን አሸንፎ ስም ያለዉ ተናጋሪም ወጣዉ።
⚜ይህንን ያዩ ተማሪዎችም ከሱ ምክር ለመጠየቅ ይጎርፉ ጀመር። በትግል ያገኘዉን እዉቀት አካፈላቸዉ። ብዙዎቹ እንደሱ ተሳካላቸዉ።
⚜ዴል ካርኔጊ የደረሰበትን የበታችነት ስሜት ለማስወገድ ባደረገዉ ትግል ሀሳቡን ለአንድ ተማሪ ወይም ለብዙ አድማጮች ለማስተላለፍ የሚያስፈልገዉ በራስ መተማመን መሆኑን ተረዳ። በዚያም አላቆመም። በራስ መተማመን ሰዉን በየትም ቦታ ከሌሎች እኩል በሁለት እግሩ የሚያቆመዉ መሆኑንም ተገንዝቧል።
እያለ…
………ይ………
…………ቀ………………
……………ጥ……………
………………ላ……………
…………………ል……………
እኔ ግን አበቃዉ🙏
የመፅሀፉ ርዕስ ''ጠብታ ማር''
የገፅ ብዛት - 104 ገፆች
ዋጋ - 20.50 ብር
@lovefkrlove
@yona_man