. ''ቀናተኛዉ ንስር'' .
መሻሻልን ከመሻል የመምረጥ ምስጢር
~~የጥንት አፈታሪክ ሁለት 🦅🦅 በአንድ አካባቢ ያደጉ ንስሮች እንደነበሩ ይነግረናል። እነዚህ ንስሮች ፈጣንና ወደ ከፍታ ከመብረር አደናቸዉን ከሩቅ በማየት የታወቁ ነበሩ።
በመሀከላቸዉ ግን ከባድ የሆነ ዉጥረት አለ። 🦅 1ኛዉ ንስር ከሌላኛዉ የበለጠ ከፍታ የመብረር ብቃት ስለነበረዉ ከእርሱ እኩል መብረር ያቃተዉ ንስር እጅግ ይቀናበት ነበር።
~~ቅናቱ እየበረታ ሲሄድበት ይህንን በከፍታ የበለጠዉን ጓደኛዉን ለማጥፋት ወሰነ። በምን መልክ ሊያጠፋዉ እንደሚችል ሲያሰላስል ሳለ አንድ ቀስትን በእጁ የያዘ አዳኝ ሰዉ አገኘ 🦅🕴። ወደ እርሱም ቀረብ በማለት ችግሩን አጫወተዉ።
~~''ያ ንስር ይታይሃል?'' አለዉ ቀና ብሎ በሚያስገርም ከፍታ ላይ በመብረር ላይ ያለዉን ንስር አሳየዉ 🦅። የማየት ብቃቱ ከንስር ዓይን ጋር ሊወዳደር ያልቻለዉ አዳኝ ሰዉ በመዳፉ የፀሃዩን ጨረር እየተከላከለ ለማየት ቢሞክርም ንስሩን ሊመለከተዉ አልቻለም።
~~ልክ መታየት ሲጀምር ቀናተኛዉ ንስር ለአዳኙ ፣ ''እባክህ ይህንን ንስር በቀስትህ ግደልልኝ'' አለዉ። አዳኙም ፣ ''ለምን?'' አለዉ። ቀናተኛዉ ንስር ''ከእኔ በላይ ከፍ ብሎ መብረር ስለሚችል ቀንቼ ነዉ'' ይለዋል። አዳኙም ''በእኔ እምነት ከእርሱ ለመሻል ከመታገል ለመሻሻል ብትጥር ይሻልሃል''። ያም ሆነ ይህ ቀስት ጨርሻለዉ አለዉ።
~~ቀናተኛዉ ንስር ጥቂት ካሰበ በኃላ አንደኛዉን ክንፉን ጠጋ በማድረግ ''አንዲትን ላባ ከክንፌ ላይ ንቀልና እንደ ቀስት ተጠቀምበት'' አለዉ። በዚህ ተስማሙና አንድን ላባ ከንስሩ ክንፍ ላይ በመንቀል ቀስቱን ለጥጦ ተኮሰ። ኢላማዉን ግን አላገኘዉም። ቀናተኛዉ ንስር በቀላሉ ሊለቀዉ አልቻለም። በዚህ ሁኔታ የግራ እና የቀጅ ክንፉን እያፈራረቀ ለአዳኙ እየሰጠዉ ብዙ ላባ ካስነቀለ በኃላ ሰዉየዉ ስለደከመዉ ጥሎት ሄደ።
~~በሁኔታዉ የተበሳጨዉ ቀናተኛ ንስር ጉዞዉን ለመቀጠል ሲሞክር ለካ ላባዉ ሁሉ ከክንፉ ላይ ተነቅሎ እልቆ ነበር። መብረር አልቻለም። ይህ ሕይወቱን ሙሉ በከፍታ ላይ በመብረር የታወቀዉ ንስር ''ዶሮ''🐓 ሆኖ ቀረ።
የመፅሀፉ ርዕስ - ትኩረት
የገፅ ብዛት - 160 ገፆች
ፀሀፊዉ - ዶር. ኢዮብ ማሞ
ዋጋ - 50 ብር
የዕለቱ መልእክታችን እነሆ……
The Idle Mind Is The Devils Workshop/ስራ የፈታ አይምሮ. የሰይጣን ቤተ ሙከራ ይሆናል
@lovefkrlove
@yona_man