✍ ብስጭት ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ዙሪያ ገባችን ሲጨልምብን ደርሶ ሆድ ይብሰናል፡፡
✍ በዘሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር የተካረረ ጠብ ወስጥ በገባንብት ጊዜ በዚሁ የስሜት ወጀብ ክፍኛ ልንመታ እንችላለን፡፡ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም የአዳም ዘር ከብስጭት ዳፋ አያመልጥም፡፡
✍ የቁጣ ወይም የብስጭት ስሜት በራሱ አጥፊ አይደለም፡፡እንደውም ስሜቱን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ማሳካት ለምንሻቸው ሕልሞቻችን እንደ መስፈንጠሪያ መደላደያ ሆኖ ያገለግላል፡፡
🤔 ታዲያ የብስጭት ስሜት መች ነው ችግር የሚሆነው ?
✍የቁጣ ስሜት ጠንቅ የሚሆነው የራሳችንንም ሆነ የአካባቢያችንን ሰላም መንሳት ሲጀምር ነው፡፡ በዙሪያ ገባው ላይ ገጽታን ማጥቆር አንዱ የቁጣ ስሜት መገለጫ ሊሆን ይችላል፡፡ይህ የስሜት ቁርቋሶ ውሎ አድሮ አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ መናጋት መፍጠሩ የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ፈጥነን ለመፍትሄው የማንቀሳቀስ ከሆነ ከባድ የሆነ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ እንወድቃለን፡፡
✍ጎጂ የቁጣ ስሜት ልክ በደረታችንን ላይ እንደተሰነቀረ እቶን እሳት ይቆጠራል፡፡ድንገት ከደረታችን በአፋችንን ሽቅብ ተመዘግዝጎ ከሰዎች ላይ የሚያርፍ የእሳት ጅራፍ እንደማለት ነው፡፡
✍መችም ሁላችንንም የሚከሰትብንን የቁጣ ስሜት በአንድ አይነት መንገድ አናጠባርቅም፡፡ ቁጣ የሚገልጥባቸው መንገዶች ውጫዊ፣ውስጣዊ እና ነውጥ አልባ ናቸው፡፡
✍ ውጫዊ፡እንደ መብረቅ እየጮኽን፣ፊት ለፊታችን ያገኘነውን እቃ በመስበር ንዴታችንን ስንገልጽ
• ውስጣዊ፡የውስጣችንን ረመጥ በሆዳችንን ይዘን ስንብሰለሰል
• ነውጥ አልባ፡በልግመኝነት እና በሽሙጥ ባሕሪ ይገለጻል
✍ውጫዊ የቁጣ ስሜት በንጽጽር ለራስም ሆነ ዙሪያ ላሉ ሰዎች እጅግ አደገኛ ነው፡፡ይህ አይነት የቁጣ ስሜት መዘዙ የከፋ ስለሆነ በአፋጣኝ የባለሙያ እገዛ ማግኘት ይኖርብናል፡፡በአጠቃላይ በብስጭት ምክነያት የሚመጡ የጤና እክሎች ብዙ ናቸው፡፡ የምግብ ፍላጎት መቆለፍ፣እንቅልፍ ማጣት ባስ ስልም ራስን ለማጥፋት የሚያንደርደር ጨለምተኝነት ምንጩ ዞሮ ዞሮ በረባው ባልረበው ቆሽታችን የሚልጥበት የብስጭት ስሜት ነው፡፡
🔑ቁጣን በመላ
✍ የቁጣ ስሜት የአእምሮ የጤንነት መጓደል መገለጫ ብቻ ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ከዚህ ይልቅ የሕይወታችን አንድ አካል እንደሆነ በፀጋ መቀበል ይኖርብናል፡፡ይህም ሲባል የቁጣ ስሜትን ልጓም መልቀቅ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያስከትልም ማለት አይደለም፡፡
✍ ስለዚህ ቁጣን በመላ ልንገራው ይገባል፡፡ ቁጣን በኃይል፣በትግል ለመቆጣጥ የምንጠር ከሆነ እሳትን በእሳት ለማጥፋት እንደመሞከር ይቆጠራል፡፡
✍ ከዚህ ይልቅ ኮረንቲ እስከመጨበጥ የሚያስድርስ ብስጭት ላይ ብንሆንም እንኳን የአተነፋፈስ ስልተ ምትን በማጤን እና የጥሞና ልምምድ በማድረግ እንደ እሳት ጎመራ በሚንተከተከው የቁጣ ስሜት ላይ በረዶ መቸለስ ይቻላል።
@Lovefkr