#ለራሳችሁ_ዋጋ_ስጡ!
💥አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እኛን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱን (Treat እንደሚያደርጉን) የምናስተምራቸውና የምንፈቅድላቸው እኛው ራሳችን ነን፡፡
🌆ራሳችንን ከናቅን ሰዎች እኛን ይንቁናል፣ ራሳችንን ስናከብር ደግሞ ያከብሩናል፡፡ ራሳችንን ርካሽ አድርገን ካሰብንና ልክ የትም መሄጃ እንደሌለው አይነት ሰው ሆነን ራሳችንን ካቀረብን ሰዎች እንደ ተራና የትም መሄጃ እንደሌለው ሰው ያስተናግዱናል፣ ለራሳችን ዋጋ ከሰጠን ደግሞ ዋጋ ይሰጡናል፡፡
🎈ሰዎች በምን መልኩ እየቀረቧችሁና እያስተናገዷችሁ እንዳሉ ተመልከቱትና ምናልባት በዚያ መልክ እንዲቀርቧችሁና እንዲያስተናግዷችሁ የፈቀዳችሁት እናንተው የመሆናችሁን ጉዳይም በዚያው ለመቃኘት ሞክሩ፡፡
🌙እናንተ ሳትፈቅዱላቸው ሰዎች ሊንቋችሁና በወረደ መልኩ ሊያስተናግዷችሁ አይችሉም፡፡ ከእናንተ ፈቃድ ውጪ በዚያ መልክ እንዳይቀርቧችሁ ማድረግ ባትችሉም ሁኔታው ልክ በማስያዝ ድርጊታቸው የመጀመሪያና የመጨረሻ እንዲሆን የማድረግ መብቱም ሆነ አቅሙ አላችም፡፡
ፈጣሪ ከሰጣችሁ “ሰውነት” በታች አትኑሩ!
✍ዶ/ር እዮብ ማሞ
#ውብ_አዳር_ይሁንልን
@lovefkrlove
@Lovefkr