🥰 #ብቁ_ናችሁ!
☝️ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!
✨እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡
🌞እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!
✨አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡
🔆በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡
✍ዶ/ር እዮብ ማሞ
ውብ ምሽት🙏🙏
@lovefkrlove
@Lovefkr