🙋♀ትናንት ስታዜመው የነበረ፣ ለዛሬ ያላደረ አስተሳሰብ አለህ?…
አይግረምህ!!.. ይልቅ ዛሬ የምታወግዘው ሃሳብ የነገ ተረኛ ቅኝትህ ሆኖ ሊከሰት እንደሚችል አስብ… በመኖር ውስጥ ወጥ የሚባል ቅኝት፣ የማይለወጥ የሚባል የማሰብ ፍኖት የለም… ‘ልክ’ ይመስለኝ ነበር ያልከውን መረጃ ‘ልክ እንዳልሆንክ’ ባሳየህ የዛሬ ክስተት ለመለወጥ ስትንደረደርም ሆነ ሽንጥህን ገትረህ የተሟገትክለት ሃሳብ ነገ ደርሶ ብን ሲልብህ ስታይ ውል አልባነት አይሰማህ
☮በሕላዌ ሕዋ ውስጥ ወዲህ ቢሉት ወዲያ የማይለወጥ አንድ ነገር እውነት ብቻ ነው… እውነት እውነትነቷ ነው ውበቷ - እውነት እውነት ትባል ዘንድ የድጋፍ ሰልፍ አትፈልግም… በራሷ የምትቆም ጽኑ ናት… የተከታዮቿ ማነስና መብዛት የእውነትነቷን ሞገስ አይነቀንቀውም… “The truth is like a lion; you don’t have to defend it. Let it loose; it will defend itself.” እንዲሉ... እስስት ሆኖ የሚዘልቀው ምን ይሆን ታዲያ?… መረዳትህ ነው… ግንዛቤህ… የእይታ አንፃርህ /Level of understanding/…
❤️የብዙ ውይይቶች ውጤት ጽንፍ ለጽንፍ በሚተያዩ ሃሳቦች መደምደም የየትኛውንም ወገን ትክክለኛነት አይናገርም… የማንኛውንም ስህትነትም አይገልጽም… የየወገኑን አንፃር እንጂ… ስለዚህ እንደኔ ካላሰብክ ብሎ ሙግት መግጠምም ሆነ የሌላውን ሌላነት የመግለጽ ነፃነት መጋፋት በደል ነው… የእውነት ተክለ ቁመና በአንፃራዊነት ባይዳኝም ታዳሚዎቿ ግን በየልካችን የምንሰፋው ‘እውነት’ ያለን መሆኑ እርግጥ ነው…
☯ፈጣሪ ሕይወትን ሳንሰለች እንዋብባት ዘንድ የተለያየ መነጽር እያቀበለን የእውነት ፀሐይ ከደመና ጥጥ ውስጥ ተፈልቅቃ ስትወጣ ያለውን ሂደት ጊዜ በሚሉት ሃዲድ ላይ ሆነን እንመለከታለን… ግና የገባን እንጂ ደርሶ የጨበጥነው እውነት የለንም!!!
🤍እና ምን ለማለት ነው… ‘ፍጹም እውነትን ይዘናል’ ከሚሉኝ ይልቅ ‘እውነትን እየፈለግን ነው’ በሚሉኝ ሰዎች ዙሪያ መገኘት ያስደስተኛል…
✍ ደምስ ሰይፉ
#ውብ_ምሽት
@Lovefkrlove
@lovefkr