እንስሳት ትኩረት ይሻሉ የተባለ የጎዳና እንስሶችን የሚረዳ እና ስለመብታቸው የሚሟገት የቮለንቲሮች ተቋም እንደተናገረው ዛሬ ማታ በአራዳ ክፍለ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት ጀምሮ ውሾችን በመርዝ የማስወገድ ዘመቻ እንደሚካሄድ መረጃው ደርሶናል ያሉ ሲሆን ይህም ዘመቻ ኢትዮጵያ በ 2012 ዓ.ም የተፈራረመችውን አለም አቀፍ ውሾችን በመርዝ ያለማስወገድ ስምምነት የሚጣረስ ሲሆን ባሳለፍነው ወር በታህሳስ 4 /2017 ዓ.ም በፒያሳ እና አካባቢው የነበሩ ብዙ ጤነኛ የሆኑ ቡድናችን ይንከባከባቸው የነበሩ ባለቤት አልባ ውሾች ጭምር የተወገዱ መሆኑን እናስታውሳለን።
ሀገራችን አሁን የጀመረችውን የልማት እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጣም ብዙ የመኖርያ ቦታዎች እና መንደሮች በመፍረሳቸው ምክንያት ሰዎች እንደ ልጅ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ውሾች ወደ ተሰጣቸው የኮንደሚንየም መኖርያ ቤቶች ይዘው እንዳይሄዱ በመከልከላቸው ምክንያት በብዙ ሀዘን እና ለቅሶ ጎዳና ላይ ጥለዋቸው እንዲሄዱ የተገደዱ ሲሆን እነዚህ ካለምንም ጥፋት ተገደው ወደ ጎዳና የወጡ ውሾችን መንግስት ከባለቤቶቻቸው ጋር እንዲሄዱ ሊያደርግ አልያም መጠለያ ሰርቶ ሊሰበስባቸው ሲገባ ይሄ እንቅስቃሴ ባልተደረገበት ሁኔታ ጎዳና ላይ ያሉ ውሾችን በመርዝ አሰቃይቶ ማስወገድ አግባብ ስላይደለ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን በማለት እንስሳት ትኩረት ይሻሉ የተባለው የእንስሳት መብት ተከራካሪ ግሩፕ ያሳስባል።
#የአንድ ሀገር ታላቅነት እና የሞራል እድገቷ የሚለካው በእንስሳቱ አያያዝ ነው
መሐተመ ጋንዲ