ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስር
ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢመስጥህ ነው?››
‹‹ባክሽ የድሮ መስሪያ ቤቴ..ማለቴ ቆርቆሮ ፋብሪካ ምናምን ብዬ አውርቼሽ ነበር አይደል?››
‹‹እ..ስለምትናፍቅህ ልጅ እያወራኸኝ ነው?››
‹‹አዎ ..ትክክክል?››
‹‹እና እሷ ምን ሆነች?››
‹‹እባክሽ ጠፋች…አንድ ብቸኛ ልጃቸው ጠፋችባቸው…ከዛሬ ነገ አገኛታለሁ ብዬ ስቃትት የእህቴንም ልብ ይዛ ጠፋች››
‹‹ጠፋች ማለት?››
‹‹እኔ እንጃ ..ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ስለእሷ ነው የሚያወራው››
‹‹ስለጠፋች ብቻ?››
‹‹አዎ አባትዬው ያለችበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዬን ብር በሽልማት መልክ እክፍላለሁ ብሎ ስላሳወጀ ምድረ ድርዬ ጠቅላላ መንገድ ላይ ያገኞትን ወጣት ሴት ሁሉ እያስቆሙ ከእሷ ፎቶ ጋር ማስተያያት ጀመረዋል፡፡››
‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት?››
‹‹እውነቴን ነው…አታይውም እንዴ..?››ብሎ ስልኩን አቀበላት… ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ሁለት ሶስት ፎቶዋን አየች…ውስጧን በረዳት…ግማሽ ፊቷ በፋሻ የተሸፈነ ቢሆንም አስተውሎ ያያት ሰው ሊለያት ይችላል…ፊቷ የተቀመጠው ፊራኦል እስከአሁን እንዴት እንዳለያት ተደንቃለች፡፡
ስልኩን መለሰችለት‹‹ምን ሆና ይሆን …..?የሀብታም ልጅ ነገር ይሄኔ ቀብጣ ሊሆን ይችላል?››ስትል አፏ ላይ እንደመጠላት ተናገረች፡፡
‹‹አይ እንደዛ እንኳን ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም…እሷ የሀብታም ልጅ ስለሆነች ነገሩ ጮኸ እንጂ በየቀኑ እኳ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚህም እዛም ከያሉበት ተወስደው የሚጠለፉበት…በሰው ሚሊዬን ብር የሚጠየቅበት ሀገር ነው እኮ ያለነው….ስንቶች የተጠለፈባቸውን ልጃቸውን ወይም ባላቸውን ለማስመለስ ቤታቸውን ሸጠዋል…?ስንቶች የመኪናቸውን ሊቭሬ አስይዘው አራጣ ተበድረዋል….?.ንብረቱን አሟጦ ሸጦ ከከፈለስ በኃላ ስንቱ ሬሳ ተልኮለታለል…….እዚህ አገር በዚህ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች እንኳን ለማውራት ለማሰብም ይከብዳ…እና ይህቺ ልጅ ምን እንደገጠማት ማንም የሚያውቅ የለም….፡፡››
‹‹እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን አላውቅም››
‹‹እንዴ!! ሀገር ውስጥ እየኖርሽ አልነበረም እንዴ…..?ክፍለሀገር ያለች የእናቱን ሞት ሰምቶ ሄዶ መቅበር ያልቻለ ስንት አለ….?ዘመድ ከዘመድ ከተቆራረጠ እኮ ቆየ፣ስንቱ የትውልድ አካባቢውን ሄዶ ለማየት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ እንደመሄድ ከባድና የማይቻል ሆኖበታል…እና የዚህች ልጅ ቤተሰብ ጭንቀታቸውን ተመልከቺ…ስንቱን ያስባሉ… እህቴ ብትሆንስ ብዬ ሳስብ ዝግንን ይለኛል…እንደውም በቀደም የሰማሁትን ታሪክ ላጫውትሽ…››
በጉጉት ትኩረቷን ወደእሱ አቅንታ‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..››አለች ፡፡
ከአስር ወራት በፊት አዳማ አካባቢ ካለ አንድ የጠበል ቦታ ታጣቂዎቹ ድንገት ይመጡና የተወሰኑ ሰዎች አፍነው ይወስዳሉ፡፡ከተወሰዱት ውስጥ አንዱ ከአርሲ አካባቢ ነው የመጣው…የተጠየቀውን ብር ወላጆቹ በቀላሉ ማሟላት አይችሉም ቢሆንም ተለምኖና ከየሰው ተለቃቅሞ ከተጠየቀው ሩቡን ያህል ብር ለታጣቂዎች ይላክና የልጁ መለቀቅ ይጠበቃል..ግን ከዛሬ ነገ ይመጣል ሲባል ወራቶች ያልፋሉ፣..እናት እንቅልፍ ታጣለች…ቀንና ለሊት ማልቀስ ይሆናል ስራዋ…ልጇ ይኑር ይሙት የምትጠይቀው ሰውና የምታጣራበት መንገድ አልነበራትም…በመጨረሻ ሰው መፍትሔ ያለውን ይነግሯታል…የሞተ ሰው ነፍስ ጠርተው የሚያናግሩ ሰዎች ጋር ይዘዋት ይሄዳሉ…እንደተባለውም የልጇ ነፍስ ሲጠራ ይመጣል..‹‹አዎ እማዬ እኔ ልጅሽ ከሞትኩ 6 ወር አልፎኛል….እርምሽን አውጪ ይላታል››እናትም ወደቤቷ ተመልሳ ድንኳን ጥላ የልጇን እርም ታወጣለች…ዘመድ አዝማድ ሁሉ ለቅሶ ደርሶ እርማቸውን ያወጣሉ..በጣም የሚገርመው ምፀት ደግሞ ምን መሰለሽ እሷን ለቅሶ ለመድረስ ከሚመጡት የቅርብ ዘመዶቾ ውስጥ ሶስቱ ዳግመኛ በታጣቂዎች ተጠልፈው አረፉት፡፡››
ንግግሩ ይበልጥ ሆድ እንዲብሳት አደረጋት..እንባዋን ሊዘረገፍ ሲተናነቃት ተሰማት..
እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹አባዬ ይሄንን ባይሰማ ደስ ይለኛል…ከሰማ በጣም ነው የሚያዝነው….እሷን ሰፈራቸው ድረስ እየሄደ ከመኪና ስትወርድና ከቤት ስትወጣ እንደሚያያት አውቃለው…ልጄን በውስጧ ይዛለች..እሷን ሳያት ልጄ በከፊልም ቢሆን በህይወት እንዳለች ይሰማኝና እፅናናለው ይላል…ይገርምሻል እኔ እራሱ እንዲዚህ እንዳስብ ተፃዕኖ ያደረገብኝ እሱ ነው››
‹‹ይገርማል ….ግን ጋሼ ምን በሩቅ አሳያቸው ማለቴ እቤት ገብተው ቢያዮት እኮ ሰዎቹ የሚቃወሙ አይመስለኝም፡››
አዎ እንዳልሽው አይቃሙም ይሆናል..ግን አባዬ እኛን ፊት ለፊታቸው ካዩ ይሳቀቃሉ…ልጅቷ ፊት ከቀረብን ማልቀሳችን አይቀርም.. እሷ ፊት ማልቀስ ማለት ደግሞ ልጅቷ ልክ በሌላ ሰው ህይወት እንደምትኖር እንድታስብ ማድረግና ልጅቷን መጉዳት ነው….ሁላችንም ከእሷም ሆነ ከቤተሰቡ በስህተት እንኳን መገናኘት የለብንም ብሎ ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ለሁሉም አስተላልፏል…እኔንም ከዛ ፋብሪካ ስራዬን ጥዬ እንድወጣ ያስገደደኝ በዛ ምክንያት ነው፡፡አሁን አሁን ግን ያንን የእሱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ እየተቸገርኩ ባለሁበት ሰዓት ነው…ይሄው አንደምታይው ልጅቷ የጠፋችው…››
‹‹‹በቃ ደከመኝ መሰለኝ ትንሽ ልተኛ ››ብላ አልጋ ልብሱን ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነችና ..በፀጥታ እንባዋን ዘረገፈች…አባትና እናቷ አሳዘኗት….ቢሆንም ለአመታ ያበሳጮትን ብስጭት ልትረሳላቸው አልቻለችም….በውሳኔዋ ፀንታ እስከመጨረሻው መቆየት እንዳለባት ዳግመኛ ወሰነች፡፡‹‹አዎ አሁን እያዩት ያሉት ስቃይ ይገባቸዋል››በማለት በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ ////
ሰለሞን በሶስተኛው ቀን አርፍዶ ሶስት ሰዓት አካባቢ ወደቢሮ እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ…የማያውቀው አዲስ ቁጥር ነው…አነሳው፡፡
‹‹ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው፡፡››ድርጅቱን ኪያ ብሎ የሰየመው አስቴርን ለማስደሰት ስለፈለገ ነበር…አስቴር እናቷ ከመሞታቸው በፊት ‹‹ኪያ ›› እያሉ ነበር የሚጠሯት እሱም አልፎ አልፎ ይሄንን ስም ይጠቀማል…ድርጅት ለመመስረት ሲያስብ ግን ወዲያው በምናብ የመጣለት ስም ይህ ኪያ የሚለው ስም ነው፡፡እንደምንም ብሎ አግብቶ ከእሷ ጋር አንድ ቤት መኖር ሲጀምሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በወጥነት ኪያ የሚለውን ስም ይጠቃማል..ሚስቱም ሆነ ድርጅቱ በአንድ ስም ይጠራሉ…ይህ ነው እቅዱ፡፡
ሴሎቹ ሁሉ ተነቃቁ…‹‹በስተመጨረሻ ተሳካ…በስተመጨረሻ የመጀመሪያ ደንበኛዬን አገኘሁ….‹‹ሰሎሞን ጀግና ነህ፣›››ብሎ ተደሰተና ድምፁን ጎርነንና ሻከር አድርጎ፡፡‹‹አዎ ትክክል ኖት..ምን ልታዘዝ?፡፡››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እባኮት የቢሮዎትን ትክክለኛ አድርሻ ላስቸግሮት…?››
‹‹ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 ፡››
‹‹አመሰግናለው ..ከ15 ደቂቃ በኃላ ደርሳለሁ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
እሱ ደግሞ ቢሮ ለመደርረስ 5 ደቂቃ ብቻ ነው የሚቀረው.. ‹‹ቢያንስ የመዘጋጃ 10 ደቂቃ ይኖረኛል›› ሲል አሰበ…‹‹ ደንበኛዬ መጀመሪያ የምትፈልገውን ምክር ሆነ ማንኛውንም አገልግሎት በነፃ ነው የምሰጣት ..ክፍያ አልቀበልም….››ሲል ወሰነ ፡፡መልሶ ደግሞ ሀሳቡን ቀየረ‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም….የእኛ ሰው ላልከፈለበት ነገር የሚሰጠው ዋጋ ትንሽ ነው….ምክሬን ከልቧ ሰምታ ተግባራዊ ለማድረግ የምትሞክረው ገንዘብ ካወጣችበት ብቻ ነው….ስለዚህ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያማ ላስከፍላት የግድ ነው…አዎ የተወሰነ አስከፍላታለው.፡፡››ሲል ውሳኔውን አሻሻለ፡፡.ቢሮው ደረስና ከፍቶ