ጌዲዮን በፍቅረኛው ምክንያት ከእንዴም ሦስት ጊዜ ራሱን ሊያጠፋ ሞክሯል።
ጌዲዮን የተባለ አንድ ደንበኛዬ ነበረ፡፡ ከፍቅረኛው ጋር ሲጋጩ በእግሩ ከሳሪስ ኮተቤ ሊገባ ይችላል፡፡ ይህ ደንበኛዬ ከእሷ በመለየቱ ራሱን ሊያጠፋ ብሎ ቤተሰቦቹ ናቸው ያመጡት፡፡ በምክክር ወቅት በጣም ነው የምወዳት፡፡ ከእሷ ተለይቼ መኖር አልችልም፡፡›› ነው ያለኝ፡፡
ቀጠለና ደግሞም ብዙ ሀያላን እኮ በፍቅር ምክንያት ሞተዋል›› ብሎ ነው የጠቀለለልኝ፡፡ እንግዲህ ዓለም ላይ ያሉ ሀያላን ለፍቅር መስዋዕት መሆናቸውን ኪነጥበቡ ነው የነገረው። ጌዲዮን ራሱን ለማጥፋት ከአንዴም ሦስት ጊዜ ሞክሯል፡፡ ይህ ደንበኛዬ በፍቅር ስም መታመምም መሞትም ልክ እንደሆነ አድርጎ ተቀብሏል፡፡ ለፍቅር መታመም ልክ ከሆነ ለምን ወደ ህክምና ይሄዳል? ለፍቅር ሲባል መስዋት ልክ ከሆነ ለምን መኖርን ይመርጣል? ችግሩ ይህ ነው፡፡
ለፍቅር ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ በድራማ፣ በልብወለድ ወይም በእውኑ ዓለም ያሉትን ሰዎች እንደ ጀግና ነው የምንቆጥራቸው፡፡ እናጨበጭብላቸዋለን፡፡ “ጀግና” እንላቸዋለን፡፡ ናቸው ግን? የፍቅር ግቡ ራስን ማጥፋት ነው? ፍቅር ራስን ከማጥፋት ሳይሆን ከማኖር፣ ራስን ከመውደድ፣ ራስን ከማክበር ነው የሚጀምረው እንደውም፡፡
ጀግንነት ያለው ራስን በመውደድና በማክበር ውስጥ ነው፡፡ ፍቅር ማለት መስጠትና መቀበል ነው፡፡ ሰጥቶ መቅረት አይደለም፡፡ መቀበል ብቻም አይደለም፡፡ ለመስጠት መጀመሪያ አንተ ራስህ ሊኖርህ ይገባል፡፡ ኖሮህም ደግሞ ስመስጠት መፍቀድ አለብህ፡፡ በመስጠትህ ልትደስት ይገባሃል፡፡ ራስህን ልታዋርድ ሳይሆን ልታከብር ነው የሚገባህ፡
ጌዲዮን በፍቅረኛው ምክንያት ከእንዴም ሦስት ጊዜ ራሱን ሊያጠፋ ሞክሯል። ጌድዮን በሦስተኛው ጊዜ ራሱን ሊያጠፋ ሊሞክር ቤተሰቦቹ አይተው አተረፉት እናት አለቀሰች። ቤተሰቡ ሁሉ ተከዙ ከዚያ ቤተሰቡ ተሰብስቦ ‹ለምንድነው እዚህ ውሳኔ ላይየደረስከው አሉት፡፡
እኔ እወዳታለሁ፡፡ እሷ ደግሞ አልፈልግህም አለችኝ አለ፡፡ እናት በመጀመሪያ ልጀቷ ጋ ሄደው እግሯ ላይ ወድቀው ለመኗት። እሷ በጭራሽ አለች በልጅቷ በኩል የተሞከረው ስላልተሳካ በድጋሚ እንዲያደርገው የስነልቦና ባለሙያዎች ጋ መውሰድ የተሻለ መፍትሔ እንደሆነ አውቀው ነው ያመጡት፡፡
በመጀመሪያ ከጌድዮን ጋር ያደረግነው እንዲረጋጋና ነገሮችን በጤናማ አዕምሮ እንዲያስባቸው የተረጋጋ ሁኔታን መፍጠር ነው፡፡ ይህን ማድረግ ቀላል የማይባል ጊዜ ወስዶብናል፡፡ ከተረጋጋ በኋላ ደንበኛዬ እንደነገረኝ ምን ገጥሞታል መሰለህ?
ጌዲዮን በልጅነቱ በጣም የሚወዳቸው አባት፣ ሁለት ወንድምና እህቶች ነበሩት፡፡ 7 ኛ ዓመቱ ላይ በጣም የሚወዳቸው አባቱ ሞቱ፡፡
እናት የቤት አመቤት ስለሆኑ በምን ሁኔታ ቤተሰቡን መምራት እንዳለባቸው ስለማያውቁ እዚህ ቤተሰብ ውስጥ ብዙ የተመሰቃቀሉ ሁኔታዎች ተፈጠሩ፡፡ እናት ገቢ ስላልነበራቸውና ልጆቹን ማሳደግ ስላልቻሉ ሁለቱን ሴቶች ለአንድ ዘመድ ፣ ቀሪዎቹን ሁለት ወንዶች ደግሞ ለሌላ ዘመድ እንዲያሳድጉላቸው ሰጧቸው።
ይህን ልጅ ስታየው መጀመሪያ አባቱን (በሕይወት) አጣ፡፡ ቆጥሎ እናቱን አጣ፡፡ ቀጥሎ ሁለት እህቶቹን አጣ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ እሱና ወንድሙን የወሰዷቸው ዘመድ ‹‹ሁለቱን ማሳደግ አልችልም›› አሉና ወንድሙን ለሌላ ዘመድ ሰጡት፡፡ ወንድሙንም አጣ ማለት ነው፡፡ እሱ ባደገበት ቤተሰብ ውስጥ ልብስም፣ ምግብም ከሌሎቹ የተረፈው ነው የሚሰጠው፡፡ ምግብም እንደነገሩ ነው፡፡
ጌዲዮን “እልህ ያዘኝ አለ። ይህን ሁሉ ም ስቅልቅል መለወጥ የሚችለው ራሱን በትምህርት ሲያበለጽግ ብቻ መሆኑን ስለተረዳ መማርለድርድር የማይቀርብ የሕይወት ጉዳዩ አድርጎ ያዘው፡፡ እንዳሰበውም በትምህርቱ ጎልቶ የሚታይ ልጅ ሆነ።
9ኛ ክፍል ሲገባ ከአንዲት ቆንጆ ኮረዳ ጋር ይቀራረባል፡፡ “እፎይ! አንድ የማምነው ሰው አገኘሁ አልኩ ይላል። አባቱን፣ እናቱን፣ ቤተሰቦቹን አጥቶ ይህቺ ልጅ ናት በቅርቡ ያለችውና የሆዱን ሊያወራት የምትችል ብቸኛ ልጅ፡፡ ይህቼም ልጅ ግን እንዴት እንደሆነ ሳያውቀው እዚያው ክፍላቸው ውስጥ ካለ እንዱ ጎረምሳ ጋር ፍቅር ይይዛትና ጌዲዮንን “አልፈልግህም›› ትለዋለች፡፡
እንደገና ሌላ ማጣት በሕይወቱ ውስጥ መጣ ማለት ነው፡፡ አራተኛ ወይም አምስተኛ ማጣት፡፡ ከዚያ ሕይወት ቀጠለና ዩኒቨርሲቲ ገባ፡፡
ዩኒቨርሲቲም ሌላ ፍቅረኛ ያዘ፡፡ እሷም በማያውቀው ምክንያት እየሸሸችው፣ እየሸሸችው ትመጣለች። እንደገና ሌላ ማጣት፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ከወጣ በኋላ “እፎይ! ሕይወትን ማሸነፍ ቻልኩ›› ብሎ እናቱን ማገዝ ጀመረ፡፡ እህትና ወንድሞቹም ደረሱ። የፈረሰው ቤተሰብ እንደገና መቋቋም ቻለ ማለት ነው፡፡
ከዚያ በኋላ ይህቺን ራሱን ለማጥፋት ሙከራ ያደረገባትን ልጅ ተዋወቃት፡፡ ጌዲዮን ለፍቅረኛው ደውሎ ልጅቷ ስልክ ካላነሳች ወይም ትንሽ ዝም ካለች በጣም ነው የሚናደደው፡፡ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፡፡ በጣም ይበሰጫጫል፡፡
አንድ ዕለት ፍቅረኛው ጋ ደውሎ ስልክ ሳታነሳ ስትቀር እየበረረ ቢሮዋ ሄደ፡፡ እሷ ትልቅ ድርጅት ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ ጌዲዮን በስሜት ተሞልቶ ጥበቃውን ገፈታትሮ ነው የገባው፡፡ ጭንቅላቱ ውስጥ ያለው “ከሌላ ወንድ ጋር ትሆናለች›› ወይም «ጥላኝ ሄዳለች የሚል ሀሳብ ነው፡፡ ቢሮዋ ሲደርስ ግን ስልኳን ቻርጅ ልታደርግ ሰክታው ያገኛል፡፡ ፍቅረኛው ይህ ሁሉ ከምትችለው አቅም በላይ ስለሆነባት ‹‹ከአንተ ጋርመቀጠል አልፈልግም፤ እንለያይ›› ትለዋለች፡፡
ቲጂ የምፈልጋቸውን ሰዎች ማጣት ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይህቺን ልጅ ማጣት ግን ለምን አዲስና የማልችለው እንደሆነብኝ አላውቅም.. አለኝ፡፡
ጌዲዮን ይህቺን ልጅ ማጣቱ በራስ የጎዳው መስሎት ነው የተሰማው፡፡ ይህቺን ልጀ ማጣት አዲስና የማይችለው ሆኖበት አይደለም እሱ እንደሚለውም ፍቅረኛውን ማጣቱ የጎዳው እሱ እንደሚያስበው ከሌሎቹ ሁሉ እሷ በልጣ አይደለም፡፡ እሷ የተጠራቀመው የአዕምሮ ቁስለቱ ውጤት ናች። ይህ ስሜት አባቱን በሞት፣ እናቱን፣ እህትና ወንድሞቹን በኑሮ፣ ናቅረኛውን በመለየት ከማጣቱ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው፡፡ የእሷ ጉዳይ የዛራ ብቻ አይደለም:: በ7 ዓመቱ አባቱን በሞት ከመነጠቁና ቤተሰቡ ከእራሱ ጋር ይያያዛል። ውስጡ ያላወቀው የማጣት ፍርሀት አለበት፡፡
ፍቅረኛ ስልክ ባለማንሳቷ ከቢሮ ወጥቶ ቢሮዋ ድረስ የሄደው በዚህ ፍርኮት ተገፍቶ ነው። እሱ ማጣት አዲሴ አይደለም፡፡ ለምን እዚህችኛዋ ላይ አዲስ ሆነብኝ? ነው ያለው፡፡ ውጤቱ ግን በግልባጩ እዚህችኛዋ ላይ ጉዳቱን ያበረታበት ማጣት አዲሱ አለመሆነ ነው፡፡ አዲሱ ስላልሆነ የተለማመደው መስሎታል። ግን መለማመድ ሳይሆን ይበልጥ ፍርሀት ውስጥ ነው የከተተው፡፡ ያ ፍርሀት ነው ዛሬ ራሱን ለማጥፋት እስኪነሳ ያደረሰው፡፡
ምንሆኛለሁ መፅሃፍ ገፅ 32
አላለቀም አንብበው ከወደዱት እንዲቀጥል 👍👍 React