ፀጉር ቆራጩ ደምበኛውን ያዝናናል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በሙሉ ያደርጋል...
“ያ.. ይታይሃል..?...አስፖልቱ ዳር የተቀመጠው ልጅ..?”
“አዎ”
“ከምታስበው በላይ ጅል ነው..”
“እንዴት? ”
“ቆይ ላሳይህ”....ብሎ ወጣና ልጁን ጠርቶ ወደ ውስጥ አስገባው።
“ተመልከት እንግዲህ...”
ከኪሱ አንድ የአምስት ብር እና አንድ የአስር ብር ኖት አወጥቶ ሁለቱንም መሬት ላይ ጣላቸው ከዛ ልጁን “ ከሁለቱ ትልቁን ብር አንስተህ ሂድ” አለው።
... ይሄኔ ያ ልጅ አምስቷን ብር ብድግ አርጎ ወደ መጣበት ይመለሳል...
“አየህ ይሄን ደደብ...?
በዚህ ዕድሜው አምስት ብርና አስር ብርን መለዬት አይችልም...!!”ሲል ተናገረ።
“በጣም ሚገርም ነው” አለ ፀጉሩን ሊቆረጥ የመጣው ሰውዬ ባዬው ነገር የእውነት ተገርሟል...
ፀጉሩን ተቆርጦ ጨርሶ ከፀጉር ቆራጩ ጋር ተሰነባብተው ተለያዩ።
ይሁን እንጂ ሰውዬ ቅድም ባየው ነገር ተገርሞ ብቻ ሊቀር አልፈለገም።
በቀጥታ ወደ ቅድሙ ልጅ ሄዶ ያሳሰበውን ነገር ጠየቀው...
“እውነት አንተ...አስር ብር እና አምስት ብርን መለየት አትችልም..?”የሰውየው ጥያቄ ነበር...
“አዪዪ..” አለ ልጁ ፊቱ ላይ የአሸናፊነት ፈገግታ እያሳየ...
“አዪዪ...10 ብሩን ያነሳሁ ቀንማ ጨዋታው ያበቃል” ብዬ ነው ሲል መለሰ