Maraki News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
👇ማስታወቂያ ለማሰራት
@Adis_pro

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: 🔥Best folder disk channel🔥
ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል


የ200 ብር ካርድ የሚያሸንፍ  ጥያቄ !!

በኢትዮጽያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መቼ አመተ ምህረት ነዉ....


Репост из: 🔥Best folder disk channel🔥
◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል።  Join 👇
https://t.me/addlist/ywaPLkXhze04NGY0
https://t.me/addlist/ywaPLkXhze04NGY0


#AAU

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወሰዳቹ ተፈታኞች ውጤታችሁን ኦንላይን ማየት እንደምትችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ውጤት ለማየት 👇
https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus

በተመሳሳይ በመንግስት ስፖንሰር ተደርጋችሁ የቅድመ ምረቃ ትምህርታችሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከታተል ፈተና የወሰዳችሁ አመልካቾች፣ ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/ ላይ ገብታችሁ Username (email) እና Password በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

ዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በቅርቡ ይሰጣል ማለቱ አይዘነጋም።

@MarakiNews


Репост из: Maraki Crypto
#Hamster

✅ ሀምስተር መሸጥ የምትፈልጉ ከታች ባስቀመጥነው username ተጠቅማችሁ መሸጥ ትችላላችሁ።

ማድረግ ያለባችሁ

1. ስክሪንሽት መላክ
2. ቶን ከሌላችሁ ቅድሚያ ብር በመላክ ቶን ይላክላቸዋል

ለመሸጥ 👇

@adis_pro


ገና ከተጀመረ ደቂቃዎች ተቆጠሩ
🤑 $DOGS የሰራችሁ ሰዎች አላችሁ ወይስ የላችሁም
Hamater ጉድ ሰራን
💥 Bear Hunters! 🐻 መስራት እንዳትረሱ
      ⭐️ አያስለፋም ጀምሩት
      ⭐️ በቀን አንድ ከገባችሁ በቂ ነው
Start 👇👇👇👇

https://t.me/BearsTon_Bot/bears?startapp=5657767633

Channal name 👇👇👇
@XE_Combo


እንስቶቹ ድል አድርገዋል !

በሴቶች የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ የአርሰናል የሴቶች ቡድን 4-0 በማሸነፍ በቻምፒየንስ ሊግ የሚያሳትፋቸውን አግኝተዋል።

በመጀመሪያ ዙር 1-0 ተሸንፈው ነበር ቢሆንም ግን በመልሱ ጨዋታ 4-0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 4-1 በማሸነፍ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። 🔥
@MarakiNews


#SalaleUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፤ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከታወቀ በኋላ የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ቀናት ከዚህ በፊት በተገለፀው መሰረት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@MarakiNews
የእርስዎ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !!


አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ::
----
➫ ሲቲ ስካንን ጨምሮ በግዙፍ ቴክኖሎጅዎች ታግዞ ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ የሀገር ዉስጥ ሆስፒታሎች ልምድን ባካበቱ በርካታ የህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ፣ስፔሻሊስት ሀኪሞች እንዲሁም ሜዲካል ዶክተሮች ስብስብ የሆነዉ አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
➫ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አዲሱ አሳየ የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ካስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በተጨማሪ ሆስፒታሉ ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ተደራጅቶ ለአካባቢው ፣ ለአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

➫ የአካባቢው ህብረተሰብ የዘመናት ጥያቄ የነበረውን አጠቃላይ (comprhensive)የዘመናዊ ህክምና አገልግሎት ሆስፒታሉ በተመሠረተ 7 ወራት ውስጥ መስጠት እንደተቻለም አክለዉ ገልፀዋል።
➫ በሆስፒታሉ ዉስጥ ያገኘናቸዉ ግለሰብ በሆስፒታሉ ቋሚ ሰራተኛ መሆናቸዉን ገልፀዉ ሆስፒታሉ ለስራ ምቹ ሁኖ በመደራጀቱ መደሰታቸዉን እና በሆስፒታሉ የሚገኙት በርካታ ዘመናዊ ማሽኖችና ቴክኖሎጅዎች የሆስፒታሉን ደንበኞች እፎይታ እየሰጡ እንደሚገኙም ገልፀዋል።
➫ ከወረቀት ነፃ ሆነ የህክምና አሰራር ስርዓት በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ ሆስፒታሉ በቀጣይ አጭር ቀናት ዉስጥ በአካባቢው የመጀመሪያ የሆነዉን የስነ -ደዌ (ፓቶሎጂ )ምርመራ እንደሚጀምር የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ አሳየ ገልፀዋል።
➫ ይህም ሆስፒታሉን በአከባቢዉ የመጀመሪያና ብቸኛ የስነ-ደዌ የምርመራ ማዕከል ከመሆኑ በተጨማሪ ለህብረተሰቡ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥም ገልፀዋል።
አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል !


#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል እና የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2017 ዓ.ም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ ጥሪ የተላለፈ ቢሆንም፤ ምዝገባው በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

Note:
የሌሎች ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@MarakiNews


በየአካባቢያችሁ የደመራ በዓልን የሚገልፁ ፎቶዎችን ላኩልን !!
በቴሌግራም ገፃችን ወይም
በ Facebook :-https://www.facebook.com/um.real.986 ይላኩልን
@MarakiNews
@MarakiNews


#DebreBerhanUniversity

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የርቀት እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለነባር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 27 እስከ 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የነባር የሁለተኛ ዲግሪ የርቀት እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 4 እስከ 6/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@MarakiNews


ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ

ማራኪ ኒዉስ እንኳን ለደመራ በዓል በሰላም፣በጤና አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣የደስታ፣የፍቅር እንዲሆንሎ ይመኛል።

መልካም በዓል!!
@MarakiNews


#የምዝገባ_ጊዜ_ተራዝሟል

በ2016 ዓ.ም በሪሜዲያል መርሃ ግብር ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ በ2017 የአንደኛ ዓመት ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ ሲሆሄ ወደ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበትን ቀን ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል " ሲል የዲላ ዩኒቨርስቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አሳዉቋል።

@MarakiNews


የመስቀል ወፍ ምን አይነት ናት?
@MarakiNews


መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ፦
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

በአሉ ያለ አንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና የበዓሉ ታዳሚዎች ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
Source :- አዲስአበባ ፖሊስ
@MarakiNews


#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበራችሁ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ምዝገባ ከመስከረም 28 እስከ 30/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በ2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው መሔድ ያልቻለችሁ እንዲሁም ዊዝድሮዋል መሙላት ሳትችሉ የቀራችሁ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ዩኒቨርስቲው ስለፈቀደ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ።

Note:
በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የምትቀላቀሉ (በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪ የነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የምትመደቡ) ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@MarakiNews


ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ‼

ለነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም፦

► ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች፥
► በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም
► በ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ብቻ በዋናው ግቢ ነቀምት ሲሆን፤ ሌሎቻችሁ በየነበራችሁበት ካምፓስ።

@MarakiNews


ይድረስ ፦ ለእጅጋየሁ ሽባባው ቤተሰቦችና
ለጂጂ አድናቂዎች !

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ ስለ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( ጂጂ ) ከአሜሪካ መልዕክት አስተላልፏል።
የአዲስ አበባ ኤግዚበሽን ማእከል ዛሬ ላይ በስራቸው የገነኑና ተወዳጅነትን ያተረፉ ድምፃዊያን ገና ከጅማሯቸው ከህዝብ ጋር የመገናኛ መድረክና ለስካኬታቸው በር የከፈተ ባለውለታቸው ነው።
ከ1980ወቹ አጋማሽ ጀምሮ በመድረኩ ስራቸውን ያቀርቡ ከነበሩት ባንዶች አክሱማይት ፣ኤክስፕረስ ፣መዲና ፣ሴቫንስና ዳኒ ቦይ የሚጠቀሱ ሲሆን በማእከሉ አልፎ አልፎ ብቅ ከሚሉት ባንዶች በአርቲስት ቻቺ ታደሰ እና በሙዚቀኛ ወንድሞቾ በቤዚስቱ ፖሊ ታደሰ እንዲሁም በድራመሩ ዘላለም ታደሰ የሚመራው "ሩትስ ኤንድ ካልቸር ባንድ " ይታወሳል።
ሩትስ
እኔና ጂጂ እዉቂያችን በ1987 አ.ም የሚጀምር ሲሆን በዚያን ግዜ የአስቴር አወቀና ፡የቡዙዬ ጥሩ አድርጋ ትጫወት ነበር ።ብዙም ሳትቆይ ወደ አሜሪካን ሀገር ሀገር ሄደች ፡እሷ ከሄደች ከጥቂት አመታት በኋላም እኔም ወደ አሜሪካን ሀገር አቀናሁ የተለያየ ስቴት እንኖር ስለነበር ሳንገናኝ ቆየን ከአመታት በኋላ ከኒዮርክ አንድ ወዳጄ ያለችበትን ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ ስለነገረኝ በስልክ እየተገናኘን ማውራት ያዝን በየቀኑ በሚባል በስልክ እናወራለን ወደ ቀልቧ ስትመለስም በትዝታ የኢትጽያ የመድረክ ቆይታዋንም አንስተን እንጨዎወታለን ፡

ዛሬም ድረስ ጂጂ ወደ ሀገሯ ልትገባ ነው እየተባለ የሚነገረው ሁሉ ከሀቅ የራቀ ሲሆን ያለችበት ሁኔታ ህዝብ እንዳያቀው የሚደረገው ሴራም እጅግ ያሳዝናል ፡ጂጂ ካለችበት የህይወት ጥልፍልፍ ወጥታ የምናይበት ቀን እንዲመጣ እግዚአብሔር ይርዳን።
ወንድወሰን ከበደ /ከዋሽንግተን ዲሲ
@MarakiNews


ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ይፋ አድርጓል
====


እጅግ አስደንጋጭ ነዉ!!
➫➫➫➫
ለ20 ዓመታት ያለ ምንም ትምህርት የቀዶ ጥገና ህክምና ሲሰጥ የቆየው ሀሰተኛ ሐኪም ታሰረ

የ36 አመቱ ታይላንዳዊ ላለፉት 20 ዓመታት ለበርካታ ህክምና ፈላጊዎች የቀዶ ህክምና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በአንድ ወር ውስጥ በአማካኝ ለሁለት ታካሚዎች አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚነገረው ይህ ታይላንዳዊ÷ ከሰሞኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ኪቲኮርን ሶንግስሪ የሚባለው ይህ ሰው በማዕከላዊ ታንላንድ በምትገኘው ሳሙት ሳኮን በተሰኘችው ከተማ ይኖር ነበር፡፡

ይህ ግለሰብ በዚች ከተማ በብልት ቀዶ ጥገና ህክምና ታዋቂነትን ያተረፈ ሲሆን÷ አንድ ደንበኛው ባቀረበበት ክስ ምክንያት ባሳለፍነው ሳምንት ለእስር መዳረጉን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

የብልት መጠን መጨመር ቀዶ ህክምና የተዋጣልኝ ሐኪም መሆኑን የሚናገረው ይህ ሰው በፖሊስ ከታሰረ በኋላ ሀሰተኛ ሐኪም መሆኑን ተናግሯል፡፡

“ሕክምና የትም አልተማርኩም፣ ነገር ግን ገና ከ14 ዓመቴ ጀምሮ ራሴን በልምድ አስተምሬያለሁ” በማለት÷ የህክምና ፈቃድም ሆነ ከየትኛውም የህክምና ተቋም የተማረበትን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡
@MarakiNews

Показано 20 последних публикаций.