Meleket Tube


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


መንፈሳዊ መረጃዎችን እንዲሁም ዝማሬዎችና የወንጌል ትምህርቶች በየእለቱ ከዚህ ገፅ ያገኛሉ።
ኢየሱስ በክብር ይመጣል!
Find us on more- https://linktr.ee/meleket_tube
Contact us - @LiveMeleket_Bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Christian Music ?
ሰላም ውድ የማራናታ Store ደንበኞች

ለ 2017 ዓመተ ምህረት እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልን የተለያዩ እቃዎችን ከ አለም አቀፍ መገበያያዎች ልክ እንደ Amazon, Alibaba, AliExpress, eBay, Shein እና ከመሳሰሉት አለም አቀፍ e-commerce መገበያያዎች ላይ በ ትዕዛዝ የተለያዩ እቃዎችን ለእናንተ ለውድ ደንበኞቻችን ማስመጣት መጀመራችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።

ሆኖም ማዘዝ ምትፈልጉ ደንበኞቻችን በ ቴሌግራም @MaraStorebot እና በስልክ ቁጥራችን +251930588162 ደውላቹ ማዘዝ እንደምትችሉ ስንገልጽ በትህትና።

መልካም ዓመት በዓል

Dear Maranatha Store Customers

Happy New Year 2017! We are pleased to announce that we now offer a range of products from global marketplaces such as Amazon, Alibaba, AliExpress, eBay, Shein, and other e-commerce platforms. We look forward to delivering these diverse products to you.

To place an order, please contact us via Telegram at @MaraStorebot or call us at +251930588162.

Best wishes for the New Year!

1. Visit Our Website: 
https://bit.ly/maranatha-store
2. Contact Us: 
+251930588162
@MaraStorebot

🔽 J
oin Us🔽
@Maranatha_Store 👍
@Maranatha_Store 👍


ያ መሢሕ
ዘማሪ መስከረም ጌቱ

ቁጥር 3 አልበም ነሃሴ 26 (September 1) በሁሉም ሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርም ወደእናንተ ይደርሳል ።

Join➴
@MELEKET_TUBE
@MELEKET_TUBE
@MELEKET_TUBE


ወዳጆች ሆይ የእግዚአብሔር ሰላምና ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልኩ እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር በቅርብ ወደ እናንተ ስለማቀርበው ስለ አዲሱ ቁጥር ስምንት (Vol. 8 የዝማሬ ሰንዱቅ (አልበም) መልካም ዜና ሳካፍላችሁ በደስታ ነው:: አስጀምሮ የሚያስጨርስ እግዚአብሔር ነውና ክብር ለስሙ ይሁን!! በዚህ አገልግሎት ሙዚቃውን በማቀናበር በሪኮርዲንግ በሚክሲንግ በግራፊክስ ስራ አብረውኝ የደከሙትን በፀሎት እና በምክር በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ የደገፉኝን እንዲሁም ለዚህ ስራ መሳካት ከጎኔ በመቆም ያበረታታችኝን አብራኝ አገልጋይ የሆነች ውዷን ባለቤቴን እንዲሁም ልጆቼን እና አብረውኝ አገልጋይ የሆኑ የዳላስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከልቤ አመሰግናለሁ!!
መዝሙሮቹን በሚለቀቁበት ጊዜ በ Daniel Amdemichael YouTube channel እንዲሁም iTunes, Spotify, google play, Amazon Music እና የመሳሰሉት ላይ ታገኛላችሁ:: የኔን YouTube channel ሰብስክራብ እንድታደርጉ በትህትና አበረታታለሁ:: ሰብስክራይብ ስታደርጉ ከጎን ያለችውን የደውል ምልክት መጫናችሁን አትርሱ ይህን ብታደርጉ YouTube channel ላይ አዳዲስ ነገሮችን ሳቀርብ ወዲያውኑ ማግኘት ትችላላችሁ::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!

- Daniel Amdemichael

Join➴
@MELEKET_TUBE
@MELEKET_TUBE
@MELEKET_TUBE


Hanna Tekle
መሥዋዕት!
ቁጥር 4 ሰንዱቅ
በቅርብ ጊዜ
Join➴
@MELEKET_TUBE


#ካውንስሉ_አስቸኳይ_መግለጫ_ሰጠ
በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ጥቃት ህዳር 27 ቀን 2016ዓ/ም መግለጫ_ሰጠ።

1-ባለፋት ዘመናት በተለይ በደርግ ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተክርስቶስ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2-የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል።የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3-የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት ቤት አድርጎት ይገኛል።እንዲሁም የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ ምንም አይነት የልማት ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4-በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5-የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6-በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በአጠቃላይ ፍትህ ያስፈልጋል ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሊከበሩ ይገባል ይህ ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ። የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

Join➴
@MELEKET_TUBE


ኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎቱ እስኪደርስ ድረስ በየት ከተማ ውስጥ ነበር ሲጠብቅ የቆየው?
Опрос
  •   ቤተሳይዳ
  •   ገሊላ
  •   ቅፍርናሆም
  •   ናዝሬት
393 голосов


አስደሳች ዜና!

እንደ "ዴስፓሲቶ" እና "ጋሶሊና" በመሳሰሉት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የአለማዊ ዘፈን አቀንቃኝ የነበረው የፖርቶ ሪኮ ራፐር ዳዲ ያንኪ ህይወቱን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመስጠት እንደወሰነ እና ከአለማዊው ሙዚቃ እራሱን እንዳገለለ አሳውቋል።

"እንደ ሙዚቃ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ መድረኮች፣ ማይክራፎን ኢየሱስ የሰጠኝ በእጄ ውስጥ ያሉኝ መሳሪያዎች ሁሉ አሁን ለመንግስቱ ነው ሲል ተናግሯል።"

Join➴
@MELEKET_TUBE


Godina Qellem Wallagaa, Aanaa Gidaamiitti ajjeechaa Amantoota irratti raawwate ilaalchise Ibsa WKWW Mekane Yesus Itiyoophiyaatiin kenname.
Sadaasa 24-2016

ህዳር 25 ቀን 2016 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቄለም ወለጋ ዞን በተለይም በጊዳሚ አውራጃ በአባላቶቹ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።


Join➴
@MELEKET_TUBE


ራሴን ስመለከት እንዴት ልድን እንደምችል አይታየኝም ክርስቶስን ስመለከት እንዴት ልጠፋ እንደምችል አይታየኝም፡፡


ማርቲን ሉተር

Join➴
@MELEKET_TUBE


#ይድረስ_ለወንጌል_አማኞች_በሙሉ📌📌

(እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ)

በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል የቃለህይወት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ወንጌላውያን አማኞች ንብረት የሆነ፣ ብዙዎቻችን በግል እና በቡድን እየሄድን ለቀናት የፀለይንበት ስፍራ ነው።
በዚህ ስፍራ ሄዶ ያልተገለገለ፣ ያልፀለዬ አማኝ ይኖራል ማለት ዘበትነው። በአዲሳባ ያሉ ሁሉም ቸርቾች ወጣ ብለው የሪትሪት፣ የፆምፀሎት ፣ የህብረት ጊዜ ማሳለፍ ሲፈልጉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ተመራጩ ቦታ ይህ የኩሪፍቱ ቃለህይወት ነው። ይህ ስፍራ በከተማ አስተዳደሩ ከቸርች ተነጥቆ ለግለሰቦች ሊሰጥ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ቸርቿ ይፋ አድርጋለች። ይህ የሁሉም አማኝ ቅርስ ከቤተክርስቲያን በግፍ ከመነጠቁ በፊት ሁላችሁም የወንጌል አማኞች ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን።

እባኮ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ


Join➴
@MELEKET_TUBE


#ቤቱ_ራሱ_ይናገራል፤ ለጸሎት ቤት እንጂ ለሌላ አልተፈጠርኩም ይላል።

በአዲስአበባ ከተማ ከ1954 ዓም አንስቶ የመጀመሪያው የመሠረተ ክርስቶስ ጸሎት ቤት በደርግ ያለሕግ ወርሶ ግቢውን ትምህርት ቤት "#የአብዮት_እርምጃ" ብሎ ሰየሙት ጸሎት ቤቱን ግን የስፖርት መሥሪያ አደረጉት።
#ቤቱ_የጸሎት_ቤት_ይሁን!!

#MKCchurch

@meleket_tube


የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናንን ወቅታዊ ሁኔታ በመሚመለከት ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን  መካነ ኢየሱስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤ የድሬዳዋ ማህበረ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ህንጻና ሌሎች ተያያዥ ህንጻዎች ያሉበትን ይዞታ ለሌላ አገልግሎት ለማዋል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካብኔ የተላለፈው ውሳኔ ቤተ ክርሰቲያናችንን ብቻ ሳይሆን መላውን ህዝበ ምዕመን በእጅጉ አስደንግጧል፡፡ እናም ውሳኔው እንደገና እንዲጤን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ብርቱ ክትትል በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ የከተማው አስተዳደርም በተለይም ክቡር ከንቲባው ሁኔታውን በጥንቃቄና በሃላፊነት ስሜት እየተከታተሉ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ጋርም ለመምከር ቀጠሮ ተይዟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩ የማይመለከተውና በየትኛም መንገድ ድርሻ የሌለው አንድ አካል፤ ችግሩ መፍትሔ እንዳገኘ አድርጎ በዛሬው ዕለት በራሱ ማህበራዊ ገጽ (Facebook) የተሳሳተ መረጃ አውጥቷል፡፡ ይህን የፈጸመው አካል ይህንን ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርም ጥብቅ ማሳሰቢያ የደረሰው መሆኑን እየገለጽን ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከምታውቀው ድረስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም ዓይነት ውሳኔ ያልተሠጠ መሆኑንና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ አሠራር ኦፊሴላዊ መረጃ እስከምትሰጥ ድረስ ህዝበ ምዕመኑ በትዕግስትና በጸሎት እንዲጠባበቅ እናሳስባለን፡፡

እግዚአብሔር አገራችንን ይባርክ፤ ይጠብቃትም!
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ

@meleket_tube


የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ልትፈርስ ነው!

የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ፈርሳ እንድትነሳ መንግስት ወሰነ። ቤተ ክርስቲያኗ ያለፉትን 40 አመታት በስፍራው ህጋዊ የይዞታ ካርታ ኖሯት፣ መንፈሳዊ ስራዎችን ስታከናውን ቆይታለች። ይሁን እንጂ የከተማ አስተዳደሩ ስፍራው ለሆቴል ግንባታ ይፈለጋል በሚል ምክኒያት ባስተላላፈው ውሳኔ መሰረት እንድትፈርድ ሲል ያስተላለፈው ውሳኔ ደብዳቤ ለክርስቲያንዜና ደርሶታል።

በአሁኑ ወቅት ማህበረ ምዕመናኗ ባለ ይዞታነቷን ለማስጠበቅ ከዋናው ቢሮ ጋር እየሰራች ትገኛለች። በተጨማሪም የሃላባ ቃለ ህይወት ቤ/ክ እና የቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክንም በርካታ ስደቶች እየደረሰባቸው ይገኛል። እነዚህኑ ጉዳዮች በተመለከተ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ዛሬ ጥቅምት 12 ላይ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

©ክርስቲያን ዜና

@meleket_tube


​​የ16ኛው ክፍለ ዘመን ተሐድሶው ሲጀምር

በኦክቶበር 31፣ 1517 ዓመተ እግዚ አንድ ብዙም የማይታወቅ መነኩሴ በአንዲት ትንሽ የጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር የነበረ ሰው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ በሚገኘው የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ አናቅጽት የያዙ ወረቀቶችን ለጠፈ። እነዚያን ወረቀቶች በቤተ ክርስትያን አደባባይ ላይ የለጠፈበት ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ አደባባዩ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደ ማስታወቅያ ሰሌዳ ያገለግል ስለነበር ነው።

በለጠፈው ወረቀት ውስጥ 95 አናቅጽት (Thesis)ወይም አረፍተ ነገሮች ሰፍረዋል። የአናቅጽቱ ዋነኛ ትኩረትም ''የኃጢአት ይቅርታ ሰነድ'' ' indulgence  የመሸጥ ልምምድ ከጳጳሱ ፍቃድ የተሰጠውና ሰው 'ፑርጋቶሪ'/Purgatory (ነፍስ ወደ ገነትም ሆነ ሲኦል ከመውረዷ በፊት የምትሆንበት ስፍራ) ውስጥ በምድር በሕይወት እያለ ስላጠፋው ስለሃጢያቱ የሚቆይበትን ጊዜ (ወደ መንግስተ ሰማይ ከመግባቱ በፊት) በሚገዛው 'ኢንደልጀንስ' መቀነስ ይችል ስለነበረ ነው። ይህ 'ኢንደንጀልስ' በወረቀት የሰፈረና የቤተ ክርስትያንን ይሁንታ አግኝቶ መግዛት ለቻለ ሁሉ የቀረበ ነበር። ህዝቡም ኢንደልጀንሱን ይገዛ ዘንድ 'ቅቤ አቅልጥ' የሆኑ አሻሻጮች ነበሩ። ህዝቡ ለራሱ፣ ለዘመዱና ለወዳጁ ይገዛ ነበር፣ ለሞቱት እንኳን ሳይቀር።

ሉተር 95 አናቅጽቱን ጽፎ ሲለጥፋቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባሉት ፕሮፌሰሮች መሃል ውይይት እንዲፈጥር በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘጠና አምስቱ አናቅጽት ከዊተንበርግ ፕሮፌሰሮች ከባቢ በዘለለ በመላው የጀርመን ግዛቶችና በጠቅላላው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ታላቅ ሁካታን ለመፍጠር በቃ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ህዝብ የዚህን መነኩሴ ስም ማወቅ ጀመረ፣ በዊተንበርግ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ዶክተሩን ማርቲን ሉተርን።

ህዝብን በማወክና ባለመታዘዝ ቤተክርስትያን ከሰሰቸው፣ በጀርመን ንጉስ ፊትም ራሱን እንዲከላከልና ያደረገው ሃሰት መሆኑን አውቆ እንዲያስወግድ ታዘዘ። ያደረገው ስህተት መሆኑን ባለመቀበሉ ምክንያት የውጤቱን ስሜት 500 ዐመታትን ተሻግሮ ዛሬ እኛም ይሰማናል።

እነዚህ የተሐድሶው ማኮብኮብያ የነበሩት የተወሰኑ የወረቀት ቁርጥራጮች እንዴት ይህንን የሚያህል  ትኩረትና ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ውጤት አመጣ ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው። በተመሳሳይም የማርቲን ሉተር አስተምህሮ ከእሱ በፊት ከተነሱት  ከነፒተር ዋልዶ፣ ጆን ዊክሊፍና ጆን ሁስን ከመሳሰሉ ተመሳሳይ አስተምህሮ ከሚከተሉት በላይ ገኖ የወጣበትን ምክንያት መጠየቅ ደግ ሳይሆን አይቀርም። ከሉተር መቶ አመት በፊት የነበረው ጆን ሁስ በተቃውሞ ምክንያት በእሳት ተቃጥሎ እየሞተ በነበረባት ሰዓት "በቀጣይ 100 አመት ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ሰው አስነስቶ የማይቆም ተሐድሶን ያቀጣጥላል" ያለው ትንቢት ያለምክንያት አልነበረም።

ከላይ ላነሳናቸው ጥያቄዎች መልሱ የሚገኘው በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንና ምዕራብ አውሮጳ የነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነው። በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተከወኑ ሁነቶች ተሐድሶ እውን እንዲሆን በር ከፋች ነበሩ። ሶስት መሠረታዊ ነገሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የመጀመሪው የእውቀት ከቤተ ክርስትያን ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው። የእውቀር መስፋፋት ቤተክርስቲያን በእውቀትና ትምህርት ላይ የነበራት ሙሉ ተጽእኖ እንድትነጠቅ አድርጓታል። በዚያ ላይ የማተሚያ ማሽን መገኘቱ እውቀት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን አስተዋጽኦው ከፍ ያለ ነበር። በርግጥ ተሐድሶው የተቀጣጠለው በታተሙ ወረቀቶች ነበር።

ሁለተኛው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊዉ የሃይል ሚዛን ለውጥ ማድረጉ ነው። አውሮጳ የተለያዮ የንግድ መስመሮችን ያገኘችበትና ሃብት በብዛት ወደ መንግስታት የገባበት ወቅት ነበር። መንግስታት ከሮም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በላይ በለጠጋ በመሆናቸውና ሃብታቸውን ማጋራት ባለመፈለጋች ኢኮኖሚያዊ ቅራኔ ነበራቸው። ተሐድሶው የተራ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ ሳይሆን የገናና መንግስታትና የመሃከለኛ መደብ ልሂቃን ጥያቄ ጭምር በመሆኑ ስኬትን አገኘ።

ሦሥተኛው ምክንያት የቤተክርስትያን መሪዎች ከእረኝነት ይልቅ አምባገነን ገዢነታቸው ማየሉ ተሓድሶው እንዲሳካ መደላድል ፈጥሯል። ቤተክርስቲያን ትኩረቷን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ይልቅ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ አድርጋ ነበር። በመንፈሳዊነት ስም ገንዘብ መሰብሰብ ባህልና ልማድ ሆኖ ነበር።

ስለዚህ…የነዚህን ምቹ አጋጣሚዎችን ስናይ እንዲያው ዝም ብሎ አጋጣሚ ሳይሆኑ መለኮት ቤተ ክርስቲያንን ከወደቀችበት ለማስነሳት ጽዋው እንደሞላ ያሳየናል። ነገሮችን እያሰናሰኘ ሁኔታዎችን እያስማማ ተሓድሶውን በትክክለኝ ጊዜ አምጥቷታል። ለዚህም ነው ይህ ተሐድሶ እግዚአብሔር በትክክለኛው ጊዜ ለቤተክርስትያን የላከው ነው የሚባለው። በዚህም ተሐድሶ ምክንያት እግዚአብሔር የመላ አለሙን ፊት ቀይሮታል።

የእኛም ዘመን የመላሸቅ ጥልቀት ተሓድሶን እንድንሻ የሚያደርገን ይመስለኛል። እኛም ተሐድሶ ያሻናል!

#ተሐድሶ
#ክርስትና
#የትሩፋን_ናፍቆት

አማኑኤል አሰግድ


@meleket_tube


ቄስ አለሙ ሼጣ አረፉ። ህብረቱ በጉዳዩ ላይ ይህን ብሏል..

"የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት የመሩት ቄስ ዓለሙ ሼጣ በዛሬው ዕለት ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ዕቅፍ ተሰብስበዋል።

ኅብረቱን በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበሩት ወንድማችንና አባታችን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም በማረፍ ሞቶ ወደ ተቤዣቸው ጌታ ክብር ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በወንድማችን፣ በሥራ ባልደረባችንና በአባታችን እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።"

@meleket_tube


ቅዱስ ቃሉን የመተርጎም ዋጋ: ዊልያም ቲንዴል

..
ከዛሬ 487 ዐመታት በፊት በዛሬው ዕለት መጽሐፍ ቅዱስን ከላቲን ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ ምክንያት በአደባባይ በቋሚ እንጨት ታስሮ ዊልያም ቲንዴል እንዲቃጠል ተደረገ።  ቅዱሱን መጽሐፍ በአገሬው ቋንቋ ስለተረጓመ ብቻ በአደባባይ ጭካኔያዊ ግድያን ተገደለ። እጃችን ላይ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ እጃችን ላይ እንዲገባ ብዙ ሰማዕትነት ተከፍሎበታል።

ዊልያም ቲንዴል መጽሐፍ ቅዱስን ከዋናው እብራይስጥና ግሪክ ቋንቋ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎሙ ምክንያት ለእስር፣ ለእንግልትና መከራ ተዳርጓል። በወጣትነት እድሜው ታዋቂ የኦክስፎርድ ተመራማሪና የነገረ መለኮት ሊቅ ሆኖ ከመኖር ይልቅ የበራለትን የቅዱሱን ቃል እውነት ለሁሉም ለማሳወቅ ሲል ተሳዳጅ ሆነ። የማይነቀነቀውን የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስልጣንን ቃሉን ሁሉም እንዲያነበውና ወደ ጸጋው እውነት እንዲመለስ በማለት በቅዱሳት መጽሐፍ ትርጓሜ ነቀነቀው። በዚህም ምክንያት በ30 ዐመቱ የሞት ፍርደኛ በመሆን ወደ ቤልጀም ተሰደደ። ስደቱ መከረኛና እስር የበዛበት ነበር። በዚያም ውስጥ ሆኖ ግን ትርጉሙን ከማጠናቀቅ ወደ ኋላ አላለም።

ለአስራ ሁለት ዐመታትም በስደት ከተንገላታ በኋላ በዚህ እለት (6 October 1536) ብራሰልስ ከተማ አደባባይ ላይ በቁሙ በእሳት አጋይተውት በ41 ዐመቱ አንቀላፋ።

#ተሐድሶው
#ዊልያም_ቲንዴል

በአማኑኤል አሰግድ

@meleket_tube


የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን መንፈሳዊ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን በተመለከተ ሃገራዊ የጸሎት አዋጅ አወጀች።

ቤተክርስቲያኗ ለሁሉም የመሰረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ባስተላለፈችው መልዕክት  የጥቅምት አራቱ እሁዶች የንስሃ እና የምልጃ ጸሎት እንዲደረግበት መወሰኑን ገልጻለች። በዚህም መሰረት በምደሪቱ ላይ ስለፈሰሰው የሰው ደምና የጠፋው የሰው ነፍስ በዚህም ምክኒያት ለደረሰው መከራና ስቃይ ሁሉ እግዚአብሄርን ምህረት መለመን እንዲሁም እግዚያብሔር አምላክ በህዝቡ መካከል መከባበርን መቀባበልን እና መፈቃቃርን እንዲሰጥ ጦርነትና መገዳደል ቆሞ ሰላም እንዲሆን ምዕመናኑ በትጋት እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርባለች።

@meleket_tube


ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አስተምህሮ፣ ልምምድና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ-ምግባር በተቃረነ መንገድ በመጓዝ የሚታወቀው "ነቢይ" ዑርበርት ኤንጅል፣ ኢትዮጵያ ገብቷል፤ ግለሰቡ ከመሰሎቹ ጋር በመሆን ሕዝቡን ለማጭበርበር የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ለቃሉ እውነት የቆመ ወንጌላዊ አማኝ ሁሉ ድርጊቱን በጽኑ ሊቃወም ይገባል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት።

@meleket_tube


በመድረኮቻችን ኢየሱስ ይሰበክ
#kaluproject

@MELEKET_TUBE


በሕይወት ዘመናችሁ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ በገባችሁ ጊዜ እንዲህ ማለትን ልመዱ። በመጀመሪያ፥ “እዚህ ቦታ ያቆመኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው። በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ያለሁትም በእርሱ ፈቃድ ነው”በሉ። ቀጥሎ፥ “በዚህ ውስጥ እያለሁ እግዚአብሔር በፍቅሩ ይንከባከበኛል፤ ልጁ እንደ መኾኔም መጠን፥ እንድመላለስበት ባሠመረው የሕይወት ልክ ለመኖር እንድችል በዚህ የፈተና ወቅት ጸጋውን ይሰጠኛል”በሉ። በዚያ ላይ፥ “መከራውን ወደ በረከት ይለውጥልኛል፤ እንድማር የሚፈልገውን ነገር እንድቀስም እኔን ከማስተማሩ ጐን ለጐን ሊሰጠኝ የሚፈልገውን ጸጋ በእኔ ውስጥ እንዲሠራ ያደርገዋል”በሉ። በመጨረሻም፥ እንዲህ በሉ፥ “የእርሱ ትክክለኛ ጊዜ ሲደርስ ካለሁበት ኹኔታ ውስጥ መልሶ ሊያወጣኝ ይችላል። እንዴትና መቼ የሚለውን ግን የሚያውቀው እርሱ ነው።” ስለዚህ፥ “አኹን ባለሁበት ያለሁት (1) በእግዚአብሔር ቀጠሮ፥ (2) በጥበቃው ተከብቤና (3) በእርሱ ሥልጠና ሥር ሲኾን፥ (4) የምቈየውም እርሱ እስከ ወሰነው ጊዜ ድረስ ነው” በሉ።

— አንድሪው መሪይ

(መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን እንደተረጎመው)

Показано 20 последних публикаций.

10 983

подписчиков
Статистика канала