📌
ድንቅ ታሪክ 👉ይድረስ ልጄን ለሀብታም እንጂ አልድርም ለምትሉ ወላጆች❗️
👉ኢማም አቡ ኑአይም አህመድ ቢን አብደሏህ ቢን አህመድ ቢን ኢስሀቅ አልአስበሀኒ ሂልየቱል አውሊያ በሚለው ኪታባቸው እንዲህ ይላሉ
🔖
ሰኢድ ኢብንል መሰየብ ሴት ልጁን በሁለት ዲርሃም ዳረ :-
የታሪኩ ባለቤት ከሲር ቢን ሙጠሊብ እንዲህ ይተርከዋል :-
☂"ሰዒድ ብን ሙሰየብ ጋር ሀዲስ ለመማር እቀመጥ ነበር ታዲያ ለተወሰኑ ቀናቶች ሀዲስ ከምማርበት ቦታ አጣኝ ከቀናቶች በኋላ ወደሱ ስመለስ የት ነበርክ ብሎ ጠየቀኝ? ባለቤቴ ሞታ በዛ ጉዳይ ነበርኩኝ አልኩት ከዛም እንዲህ አለኝ ብትነግረን ኖሮ ለሰላት እንዲሁም ለቀብር እንመጣ ነበር አለኝ። ከዛም ልቆም ስፈልግ
አዲስ አገባህ እንዴ? አለኝ እኔም አላህ ይዘንልህ
ለኔ ማን ይድረኛል ሁለት ወይም ሶስት ዲርሃም ይዤ አልኩት ከዛም እኔ እድርሃለው አለኝ የምር ይህን ታደርጋለህ? አልኩት🌷ከዛም አላህን አመሰገነ በነብዩ ላይ ሰላምና ሰላት አወረደ ከዛም በያዝኩት ሶስት ወይም ሁለት ዲናር ዳረኝ።
👉ከዛም ከተቀመጥኩበት ተነሳው ከደስታ ብዛት ምን እንደምሰራ አላውቅም ወደ ቤት ስመለስ ከማን ልበደር እችላለው እያልኩኝ እያሰብኩኝ መጣው ከዛም መግሪቤን ሰግጄ ወደ ቤቴ ሄጄ አረፍ አልኩኝ ከዛም ለማፍጠሪያ ዳቦና ዘይት አቀረብኩኝ
📌በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለው ቤቴ ተንኳኳ ማነው? አልኩኝ ሰዒድ ነኝ አለኝ ከዛም በአይምሮዬ ሁሉንም የማውቃቸውን ሰዒዶች አሰብኩኝ ከሰዒድ ኢብን ሙሰየብ ውጪ እሱ ለ40 አመታት ከቤቱ መስጂድ እንጂ ሌላ ቦታ ታይቶ አያውቅም። ቆሜ በሩን ከፍቼ ስወጣ ሰዒድ ኢብን ሙሰብ ነው ወዲያው የጠረጠርኩት ነገር ቢኖር የሆነ ነገር በትዳሩ ዙሪያ አስታውሶ ይሆን የሚለውን ነበር ከዛም አባ ሙሀመድ ሆይ ብታስጠራኝ እኮ ያለህበት እመጣ ነበር አልኩት ከዛም እንዲህ አለኝ የኔ አንተ ጋር መምጣት የተገባ ነው አለኝ ከዛም ምን ታዘኛለክ አልኩት?
🔹እሱም እንዲህ አለ፦ ያላገባህ ነበርክ ከዛም አገባህ ከዛም አሁን ብቻህን ሆንክ እኔ ደግሞ ብቻህን ማደርህን ጠላው አለና ይኸይው ባልተቤትህ ብሎ ወደ ውስጥ አስገባትና በሩን ዘጋው ።
🌺
ከዛም ከማፈሯ የተነሳ ወደቀች👉ከበር አንስቼ ወደ ቀስሩ አስገባኋት ዘይትና ዳቦ ወዳለበት ቤት ከብርሃኑ ጥላ ላይ አስቀመጥኳት ከዛም ዘይቱንና ዳቦውን እንዳታየው ሌላ ቦታ አደረኩት ከዛም ወደ ጣራ ላይ ወጥቼ ጎረቤቶቼን ጠራዋቸው እነሱም መጡና ምነው? አሉኝ ሰዒድ ኢብን ሙሰየብ ልጁን ዳረኝ ሳላስበው በድንገት ይዟት መጣ አልኳቸው ።
🥢እነሱም ተገርመው ሰዒድ ልጁን ዳረክ? አሉኝ አዎ ይኸው ቤት ናት እናቴም ወሬው ደረሳትና መጣች እንዲህም አለችኝ ፦
ሳላስተካክል ብትነካት ፊቴ ባንተ ላይ ሀራም ይሁን አለችኝ።
👉
ከዛም ከሶስት ቀን በኋላ ስገባ በጣም ውብ ከሆኑ የአደም ልጆች ውስጥ አንዷ ናት ፣ቁርኣንም በኢትቃን ከሚሃፍዙት እንዲሁም ሀዲስንም በደንብ ከሚያውቁት ናት። የባልንም ሀቅ በደንብ ታውዋለች
👉ሰዒድ ዘንድ ሳልሄድ እሱም ሳይመጣ አንድ ወር አካባቢ ቆየን ወር ሊሆን ሲቀርብ ሰዒድ ዘንድ ሄድኩኝ ሰዒድም እያስተማረ ነበር ሰላምታ አቀረብኩለት ሰላምታዬን መለሰልኝና ማስተማሩን ቀጠለ ከዛም መጅሊሱ ላይ ያሉት ተማሪዎች ከተበተኑ በኋላ እኔ ብቻ ስቀር አዋራኝና ወደቤቴ ስመለስ 20 ሺ ዲርሃም ላከልኝ "
🎁
አብደሏህ ቢን ሱለይማን رحمه الله እንዲህ ይላል :-"
👉 የሰዒድ ኢብንል ሙሰየብ ሴት ልጅ ለከሲር የተዳረችው አብድልመሊክ ቢን መርዋን ለልጁ ወሊድ አጭቷት ነበር።
ሰዒድ አልድርም ሰላለው ብዙ ቅጣት ስቃይ እና ሰቆቃ አደረሰበት
መቶ ግርፋትም ገረፈው ቀዝቃዛ በሆነ ቀን ውሀም ደፋበት"።👉
https://t.me/Muradkelifa🔗
https://t.me/mesjidalsunnah/18118