የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ቻናል


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


በዚህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ቻናል ላይ የተለያዪ መንፈሳዊ ነገሮችን ብቻ የምታገኙበት ቻናል ነው ተቀላቀሉን::

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


እንኳን አደረሳችሁ።

በጉጉት የሚጠበቀው ታላቁ ጾም መጥቷል። ይህ ጾም እንደ ስሙ ዐቢይ (ታላቅ) ነው። በኦርትዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 7 የአዋጅ አጽዋማት ቢኖሩም፣ የሰባቱ ራስ ግን ይህ ጾም ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቆመ ሳይቀመጥ የጾመው ቀን ነውና ጾመ ኢየሱስም ይባላል። የሚጾሙት ዕለታትም ከሌሎቹ አጽዋማት ይልቃሉ።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ታላቁን ጾም በሳምንታት ከፋፍሎ ስያሜ የሰጠው ሲሆን፣ የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል። ዘወረደ ማለት የወረደ ማለት ነው። በዚህ ሳምንት የክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው መሆኑ ይነገርበታል።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ በተባለው ድርሰቱ "ዘወረደ እምላእሉ አይሑድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ፤ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን አይሑድ ሰቀሉት፤ በቃሉ ብቻ ዓለምን የሚያድን የሁሉ ጌታ መሆኑን ፈጽሞ አላወቁምና" በማለት ይጀምረዋል። እነሆ ዘወረደ ተጀምሯል።


©




















አስቸኩአይ መልክት ከአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም አባ ጴጥሮስ የሚባሉ ለብዙ አመታት ተሰውረው የኖሩ አባት እንዲህ ብለዋል የመጨረሻው ምፃት ስለሆነ ንስሀ ግቡ ብለዋል።ቢያንስ(ለ10 ሰው) አስተላልፉ ሳታስተላልፉ ብትቀሩ በድንንግል ማርያም የተወገዘ/የተረገመ/ ይሁን ብለዋል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


❤ኪዳነ ምህረት ሆይ ባንቺ የተፈጸመው ድንቅ ነገር ለማንም ያልተደረገ ረቂቅ ነገር ነው ኅብስት ህይወት ጌታን ያስገኘሽልን ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን🙏❤🙏
የእመቤታችን የኪዳነ ምህረት በረከቷ ፍቅሯ በሁላችን ላይ ይደርብን።
🌺እንኳን ለእመቤታችን እርገት ትንሳኤዋ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


✨✨ ፅንሰተ ማርያም ድንግል ✨✨

ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል …፤ ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያውን መረጠ፤ አከበረ፤ ለየ፤ ቀደሰ …›› /መዝ.፵፭፥፬/ በማለት እንደተናገረው፣ አምላክን በማኅፀኗ ለመሸከም የተመረጠችው ማኅደረ ማለኮት፤ የዓለሙን ቤዛ በመውለዷ ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› እየተባለች የምትጠራው፤ በአምላክ ሕሊና ታስባ ትኖር የነበረችው የድኅነታችን ምክንያት የኾነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀን የተቋጠረችው ነሐሴ ፯ ቀን ነው፡፡ ፅንሰቷም እግዚአብሔር በባረከውና ባከበረው ቅዱስ ጋብቻ በተወሰኑት ወላጆቿ በቅዱስ ኢያቄምና በቅድስት ሐና ሥርዓት ያለው ግንኙነት አማካይነት ነው፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ፤ ድንግል ሆይ በሥጋዊ ፈቃድ የተፀንሽ አይደለሽም፤ ሕጋዊ በኾነ ሥርዓት ከሐና እና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› እንዲል /ቅዳሴ ማርያም/፡፡

ታሪኩን ለማስታዎስ ያህል የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ እና በጥሪቃ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጠጎች እና መካኖች ነበሩ፡፡ በጥሪቃ ሚስቱ ቴክታን ‹‹አንቺ መካን፤ እኔ መካን፡፡ ይህ ኹሉ ገንዘብ ለማን ይኾናል?›› አላት፡፡ ቴክታም ‹‹እግዚአብሔር ከእኔ ልጅ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይኾናል፡፡ ሌላ ሚስት አግብተህ ልጅ አትወልድምን?›› ብትለው ‹‹ይህንስ እንዳላደርገው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ ኹለቱም እያዘኑ ሲኖሩ አንድ ቀን ነጭ እንቦሳ (ጥጃ) ከበረታቸው ስትወጣ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ልጅ ስትደርስና ስድስተኛዪቱ እንቦሳም ጨረቃን፣ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ ራእይ አዩ፡፡

ራእያቸውን ለሕልም ተርጓሚ ሲነግሩም ‹‹የጨረቃዪቱ ትርጕም ከፍጡራን በላይ የምትኾን ልጅ እንደምታገኙ የሚያመለክት ነው፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጠልኝም፡፡ እንደ ነቢይ፣ እንደ ንጉሥ ያለ ይኾናል፤›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ጊዜ ይተርጕመው ብለው›› ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ቴክታ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ሄኤሜን አለቻት፡፡ ትርጕሙም ስእለቴን (ምኞቴን) አገኘሁ ማለት ነው፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለዓቅመ ሄዋን ስትደርስም ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ እነርሱም እንደ በጥሪቃና ቴክታ መካኖች ነበሩ፡፡ በእስራኤላውያን ባህል መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይቈጠር ነበርና ሐና እና ኢያቄም ብዙ ዘለፋና ሽሙጥ ይደርስባቸው ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደስ ቢሔዱ የዘመኑ ሊቀ ካህናት ሮቤል መካን መኾናቸውን ያውቅ ነበርና ‹‹እናንተማ ‹ብዙ ተባዙ› ብሎ እግዚአብሔር ለአዳም የነገረውን ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን? እግዚአብሔር ቢጠላችሁ እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ ይሰጣችሁ አልነበረምን?›› ብሎ መሥዋዕታቸውን ሳይቀበላቸው በመቅረቱ፤ አንድም ከአዕሩገ እስራኤል (ከአረጋውያን እስራኤላውያን) የተወለዱ ሰዎች የሚመገቡትን ተረፈ መሥዋዕት እንዳይመገቡ በመከልከሉ እያዘኑ ሲመለሱ ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱ ርግቦችንና አብበው ያፈሩ ዕፀዋትን ሐና ተመለከተች፡፡ እርሷም ‹‹ርግቦችን በባሕርያቸው መራባት እንዲችሉ፤ ዕፀዋትን አብበው እንዲያፈሩ የምታደርግ ጌታ እኔን ለምን ልጅ ነሳኸኝ?›› ብላ አዘነች፡፡

ከቤታቸው ሲደርሱም ‹‹እግዚአብሔር ልጅ ቢሰጠን ወንድ ከኾነ ለቤተ እግዚአብሔር ምንጣፍ አንጣፊ፣ መጋረጃ ጋራጅ ኾኖ ሲያገለግል ይኑር፤ ሴት ብትኾንም መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ስታገለግል ትኑር›› ብለው ከተሳሉ በኋላ ሐምሌ ፴ ቀን ሐና ለኢያቄም ‹‹በሕልሜ ፀምር (መጋረጃ) ሲያስታጥቁህ፤ በትርህ አፍርታ ፍጥረት ኹሉ ሲመገባት አየሁ›› ብላ ያየቸውን ራእይ ነገረችው፡፡ ኢያቄም ደግሞ ለሐና ‹‹ጸዓዳ ረግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በራስሽ ላይ ስታርፍ፣ በቀኝ ጆሮሽ ገብታ በማኅፀንሽ ስታድር አየሁ›› ብሎ ያየውን ራእይ ነገራት፡፡ ሕልም ተርጓሚው ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ባላቸው ጊዜም ‹‹አንተ አልፈታኸውም፤ ጊዜ ይፍታው›› ብለው ተመልሰዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ‹‹ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ብሎ ነግሯቸው ሐዲስ ኪዳን ሊበሠር፤ ጌታችን ሊፀነስ ፲፬ ያህል ዓመታት ሲቀሩ ነሐሴ ፯ ቀን በፈቃደ እግዚአብሔር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀንሳለች፡፡ እመቤታችን በሐና ማኅፀን ውስጥ ሳለች ከተደረጉ ተአምራት መካከልም በርሴባ የምትባል አንድ ዓይና ሴት (አክስቷ) ሐናን ‹‹እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኘሽ መሰለኝ ጡቶችሽ ጠቁረዋል፤ ከንፈሮችሽ አረዋል›› ብላ ማኅፀኗን በዳሰሰችበት እጇ ብታሸው ዓይኗ በርቶላታል፡፡ ይህንን አብነት አድርገውም ብዙ ሕሙማን ከደዌያቸው ተፈውሰዋል፡፡

ዳግመኛም ሳምናስ የሚባል ያጎቷ ልጅ በሞተ ጊዜ ሐና የአልጋውን ሸንኮር ይዛ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት ከሞት ተነሥቶ ‹‹ሰላም ለኪ ኦ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ፤ ሰማይና ምድርን የፈጠረው አምላክ አያቱ ሐና ሆይ ሰላም ላንቺ ይኹን›› ብሎ ሕልም ተርጓሚው ያልፈታውን ራእይ በመተርጐም ከሐና እመቤታችን፤ ከእመቤታችን ደግሞ እውነተኛ ፀሐይ የተባለው ክርስቶስ እንሚወለድ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡
/ምንጭ፡- ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ፣ ፭፥፴፰/፡፡

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ‹‹ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን፤ ማርያም ሆይ እውነተኛውን ምግብ፣ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን፤›› በማለት እንደ አመሰገናት እኛም ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሰጠውን፤ ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ ማዳን የሚቻለውን፤ እውነተኛውን ምግበ ሥጋ ወነፍስ ኢየሱስ ክርስቶስን ስለወለደችልን ‹‹እናታችን፣ አማላጃችን፣ የድኅነታችን ምክንያት፣ ወዘተ›› እያልን እመቤታችንን እናከብራታለን፤ እናገናታለን፤ እናመሰግናታለን፡፡ እናቱን በአማላጅነት፤ ራሱን በቤዛነት ለሰጠን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው፤ የእመቤታችን በረከት አይለየን፡፡


ከመ ፀሐይ ብርህት) ሲሉ ያድራሉ፡፡ እንደ ፀሐይ ብቻ ነው ወይ የምታበራው የሚል ካለ ደግሞ ‹‹ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ›› እያልንም እናመሰግናታለን፡፡

የሙሴን ፊት ትኩር ብሎ ማየት ካስቸገረ እመቤታችንን ያዩ ሰዎች ምንኛ በብርሃን ተሞልተው ይሆን? ‹አሕዛብ ለፊትሽ ይማልላሉ›

እንዳለው የእግዚአብሔርን እናት ያዩ ዓይኖች ምንኛ ክቡራን ናቸው! እንደ አባ ይስሐቅ ‹አርእየኒ እምከ› ‹እናትህን አሳየኝ› ሳይሉ ፤ እንደ ዮሐንስና እንድርያስ ‹ማደሪያህ ወዴት ነው?› ብለው ሳይጠይቁ እመቤታችንን ያዩ ዓይኖች ምንኛ ዕድለኞች ናቸው፡፡

ሰዎች ጠፈርን አዩ ተብሎ ዝናቸው ይነገራል፡፡ ጠፈሩንም ምድሩንም በመሃል እጁ የያዘን ጌታ በእቅፍዋ የያዘችውን እመቤት ከማየት በላይ ምን ክብር አለ፡፡ ጌታ የተወለደበትን ሥፍራ ማየት ድንቅ ነው ፤ የወለደችውን ማየት ምንኛ ታላቅ ይሆን? የእናንተን አላውቅም ፤ እኔ ግን እንደ ቅዱስ ዳዊት የአምላክን ማደሪያ አይ ዘንድ እመኛለሁ፡፡ ‹መቅደሱንም እመለከት ዘንድ› (መዝ.27፡4) በሰው እጅ ከተሠራው መቅደስ ይልቅ ልዑል ራሱ የሠራትን ሕያዊት መቅደስ ድንግል ማርያምን ማየት ይበልጣል፡፡ ሰማይንና ምድርን ሙሉ ከማየት እርስዋን ማየት ይበልጣል ፤ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ነው ፤ ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አላጠባውም አላቀፈውም አላሳደገውም እርስዋ ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይላል ‹‹የሽቱ ዕቃ ሽቱው ካለቀም በኋላ መዓዛው ከዕቃው አይለይም፡፡ እመቤታችን ጌታን ከወለደችም በኋላ የመለኮቱ መዓዛ አልተለያትም››


የጌታችንን የክብሩን መጠን የተረዳ ሰው ማደሪያው የሆነች እናቱን እመቤታችንን ይወድዳል፡፡ እንኳንስ የወለደችውን እናቱን ቀርቶ የለበሰውን ልብስ ሳይቀር አክብሮ ነክቶ ይፈወሳል ፣ ያደረገውን ጫማ እንኳን ልፈታ አይገባኝም ይላል፡፡


ይህን የእመቤታችንን ፍቅር ስንረዳ በሰማያት የጌታ ማደሪያ ወላዲተ አምላክ ወዳለችበት ፣ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት አእላፍ መላእክት ማኅበር ገብተን ለማየት እንበቃለን። ከሁሉም በላይ ከተአምረ ኢየሱስ በፊት "ለላህይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ" (ውበትህን ልናይ እንወዳለን) እያልን የምንለምነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማየትም እንደርሳለን።


መጽሐፉ "በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል" ይላል። በታናሽዋ ብርሃን በድንግል ማርያም ያልታመነ ታላቁን ብርሃን ክርስቶስን እንዴት ሊያይ ይችላል? "ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ባለን" በመጥምቁ ዮሐንስ ብርሃንነት ካልታመንን ወደ "ብርሃናት አባት" እንዴት እንደርሳለን? (ዮሐ 5:35 ፣ ያዕ 1:17) ዳዊትስ "በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን" ብሎ የለ? (መዝ 36:9)


አባ ገብረኪዳን እንዲህ አሉ፣ "ለሰው ልጅ በየቀኑ ሰላማዊ ህሊና የሚሰጠው ምን እንደሆነ ልንገራችሁ? ለሰው መልካም ማድረግ ነው። መልካም ባደረግን ቁጥር ሁልጊዜ አሸናፊዎች፣ ድል ነሺዎች ነን። ሞገስ ይሰማናል፣ ምክንያቱም መስጠት እግዚአብሔርን ስለሚያስመስል ነው።

"መስጠት የሚባለው ቁሳቁስ ብቻ አይደለም፣ መልካም ምክርን መስጠት፣ ዕውቀትን መስጠት፣ ጉልበትን መስጠት፣ ጊዜን መስጠት ስጦታ ናቸው። መልካም ፊት፣ ብሩህ ገፅ፣ ጥሩ ፊት ማሳየት በራሱ ስጦታ ነው። ለአንድ ሰው ብሩህ ገጻችን ስናሳየው ይወዱኛል ማለት ነው፣ ያከብሩኛል ማለት ነው ብሎ እንዲያስብ እናደርገዋለን። በዛን ጊዜ ይፅናናል። የሰው ልጅ አንድ የሚያዝንበት ነገር ቢኖር እኮ ሰው ይጠላኛል ብሎ ማሰቡ ነው። ስለዚህ እኛ ብሩህ ገፅ ስናሳየው እሱም ስጦታ ነው።

"ሳቅ በራሱ ስጦታ ነው፣ ለምሳሌ ቤታችን እንግዳ ሲመጣ መሳቅ ማለት ለዛ ሰው የመጀመሪያ በጎ ስጦታ ሰጠነው ማለት ነው። 'በቃ ይወዱኛል፣ እነዚህ ሰዎች አልሰለቹኝም" በማለት በሙሉ ልብ እንዲያድር እናደርገዋለን። የሀገራችን ሰው "ከፍትፍቱ ፊቱ" ያለው ለዚህ ይመስለኛል።

"ሌላው ቀርቶ እገሌ ችግሩን ቢላቀቅ ደስ ይለኝ ነበር ብሎ ማሰብ በራሱ ስጦታ ነው። ቢኖርህ ስጠው፣ ባይኖርህ ግን ከችግሩ እንዲወጣ መልካም መመኘት እንደስጦታ ይቆጠራል።ከሚደሰቱት ጋር መደሰት፣ ከሚያዝኑት ጋር ማዘን በራሱ ስጦታ ነው።ሰው ሲያለቅስ ቁጭ ብሎ 'አይዞህ' ማለት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ደስ ከሚሰኙ ሰዎች ጋር ሠርግ ላይ ይገኝ ነበር፣ ከሚያዝኑት ደግሞ ለቅሶ ላይ ይገኝ ነበር።"

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ ::

Показано 20 последних публикаций.