የሶስት ትውልድ ጀግኖች ፤
✨1, ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ (አባት)
በዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ስመጥር መኮንን ነበሩ ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግስትን የጦር መሳሪያ እና የህክምና እርዳታ እድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸዉ። እኚህ ጀግና ሰው ታድያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው እረፍት ሳያደረጉ ዓድዋ ድረስ ተጉዘው በ 1888 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ገጥመው የጀግንነት ጀብዱ ፈፅመው በዚያው ዕለት ህይወታቸው እዚያው ጦር ሜዳ ላይ አልፏል።
✨2, ራስ ደስታ ዳምጠው (ልጅ)
የእኚህ የጀግናው ልጅ የሆኑት ራስ ደስታ እንደ አባታቸው ሁሉ በርካታ መልካም ስራዎች ለሀገራቸው የሰሩ ናቸው። በ1928 ዓ.ም የጣሊያን ጦር ሀገራችንን ለ2ተኛ ጊዜ ሲወር በሱማሌ በኩል ይመጣ የነበረው ጦር በጀግንነት እና በወኔ ዶሎ ድረስ ወርደው በመግጠም የጀግንነት ስራ ቢሰሩም ጦሩ በደረሰበት ሽንፈት ሰራዊታቸው ተበተነ እሳቸው ግን በአርበኝነት ለአንድ ዓመት ያህል ሲፉለሙ ቆይተው በቡታጅራ አካባቢ በባንዶች ጥቆማ በጣሊያን እጅ ወደቁ። የካቲት 16 1929 ዓ.ም በጣሊያኖች በግፍ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
✨3, ሪር አድሚራል እስክንድር ደስታ (የልጅ ልጅ)
እኚህ ወጣት ሰው ደግሞ እንደ አባታቸው እና አያታቸው ስኬታማ የአስተዳደር እና የዲፒሎማሲ ሰው ነበሩ። የኢትዮጵያ ባህል ሀይል ምክትል አዛዥ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሪር አድሚራል እስክንድር እናታቸው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ልጅ የሆነችው የልዕልት ተናኘወርቅ ልጅ በመሆናቸው ብቻ ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም ከ60ዎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በደርግ መንግስት በግፍ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
እንግዲ እነዚህ የሶስት ትውልድ ቤተሰብ ለእናት ሀገራቸው በሙያቸው ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸዉ ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ እና ልጃቸው ራስ ደስታ ዳምጠው በጠላት እጅ ነው የተገደሉት የልጅ ልጃቸው እስክንድር ደስታ ያለምንም ጥፋታቸው የንጉሡ ቤተሰብ ናቸዉ ተብለው በሀገራቸው ሰዎች ነው የተገደሉት።
ክብር እና ዘላለማዊ እረፍት ለእነዚህ ጀግና ቤተሰብ