💡 የራሳችሁ አይደላችሁም 💡
" ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:19-20)
እኛ ክርስቲያኖች ዳግም ስንወለድ ከከንቱ የአባቶቻችን ኑሮ ክቡር እና ቅዱስ በሆነው #በክርስቶስ #ደም ተገዝተን ነው ስለዚህ እግዚአብሔር በጣም ትልቅ እና በአይምሮ በማይገመት ዋጋ አውጥቶ የራሱ አድርጎናል የራሱ ስለሆንንም የራሱ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አድርጎናል ስለዚህ እንደ ሌሎች በራሳችን ላይ የፈለግነውን የማድረግ #ስልጣን #የለንም ምክንያቱም #የራሳችን #አይደለንም የራሳችን ለመሆን ብንፈልግ እንኳ የተከፈለብንን ዋጋ መክፈል አለብን የክርስቶስን የደም ዋጋ የሚያክል ደግሞ አናገኝም
(❗️የኢየሱስ ደም የኢየሱስ ሕይወት ነው መጽሐፍ ሲናገር የሥጋ ሕይወቱ በደሙ ውስጥ ነው ይላል❗️)
ስለዚህ በራሳችን ላይ የምናደርጋቸው ውሳኔውች በሙሉ በእኛ የሚያድረውን እግዚአብሔርን ማክበር አለበት፡፡
እንደ ፈጥረታዊ ሰው በራስ አይምሮ ብቻ ከሚመራ ሕይወት መውጣት አለብን ይልቁን "በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ" ቃሉ እንደሚል ለውሳኔዎቻችን በውስጣችን ያለውን የመንፈስ ቅዱስን ፍቃድ ማወቅ አለብን የድርጊቶቻችን ግብ እግዚአብሔርን ያከብራል ወይስ አያከብርም ነው መሆን ያለበት ምክንያት? አሁንም ደግሜ እላለው የራሳችን አይደለንም ስለዚህ? በሥጋችን እግዚአብሔርን እናክብር።
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ለመኖር የገዛንን የራሱ ያደረገንን እንዲሁ መቅደሱ አድርጎ በእኛ ያደረውን የሕያው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ፍቃድ እየተከተልን መኖር ነው እርሱ እንዲመራን ከፈቀድንለት እግዚአብሔር አብዝቶ ክብሩን እና ሕልውናውን የሚገልጥበት ቤተመቅደስ እንሆናለን።
#ጸሎት
እግዚአብሔር አባት ሆይ አመሰግንሃለሁ አንተ በልጅህ በኢየሱስ ደም ገዝተህ የራስህ አድርገኸኛል
የቅዱስ የመንፈስህም ማደሪያ ቤተመቅደስ አድርገኸኛል እኔ የራሴ አይደለሁም፡፡
ያንተ ሆኜ ሳለሁ በራሴ ሥጋ ፍቃድ አንተን በማያከብር ስለተጉዋዝኳቸው ጉዞዎቼ ይቅር በለኝ በደሌ በኢየሱስ ደም እጠበው ከእንግዲህ በመንፈስህ በመመራት ላንተ ክብር መኖር እፈልጋለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስህ ይምራኝ ልጅህን ኢየሱስንም በሕይወቴ ያክብረው አባት ሆይ ስለሰማኸኝ በውድ በልጅህ በኢየሱስ ስም አመሰግንናሃለው አሜን።
ተባረኩ!
@mkc1933