ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ
ጥር ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጿል።
ሜትሮ ፖሊታን ማር ዩልዮስና ፋዘር ጆሲ ጃኮብ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ መልዕክትን በመያዝ የመጡ ሲሆን የልዑካኑ መምጣት ዋነኛ ዓላማ ከዚህ በፊች ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመንፈሳዊ አገልግሎት፣ በጤና ዘርፍ ፣ በትምህርት ና በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ የነበረውን የጋራ ስምምነት በኮሮና ምክንያት ተቋረጦ የነበረውን ዳግም መቀጠል የሚያስችል ውይይት ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።
በተለይም በውጭው ዓለማት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጋራ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ ነውም ተብሏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በልዑካኑ መምጣትና በገንቢ ሐሳቡ መደሰታቸው በመግለጽ በስምምነቱ መሠረት መተግበር እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን ልዑካኑን በመላክ ስምምነቱ እንደገና እንዲጀመር ስላደረኩ የሕንድ ማላንካሳ ኦሮቶዶክስ ፓትርያርክን አመስግነዋል።
በቅዱስነታቸው ምላሽና አቀባበል የተደሰቱት ልዑካኑ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የተላከ ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ልዑክ ምላሽ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።