ለልኀቀት ማእከሉ ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የአሜሪካ ማእከል አባላት አሳወቁ !!!
ማኅበሩ ባለ 14 ወለል የልኀቀት ማእከል ግንባታ ግንባታ መጀመሩንም ለአባላቱ አብስሯል:: በውይይቱ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኅ/ማርያም የማኅበሩ አገልግሎት እየዘመነ እና እየሰፋ በመሄዱ ተጨማሪ ሕንጻ ግንባታ ማከናወን እንዳስፈለገው አብራርተዋል :: በተጨማሪም የሚገነባው የልኀቀት ማእከል የማኅበሩ አገልግሎት የደረሰበትን ጥልቀት እና ስፋት ከግምት በማስገባት የተጀመረ ሥራ መሆኑን አንስተው ሲጠናቀቅ ማኅበሩ ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል::
የልኀቀት ማእከሉ ከመሬት በላይ 14 ወለል የሚኖሩት ሲሆን ከመሬት በታች ደግሞ 2 ወለሎች ይኖሩታል :: እስከ 1000 ሰው ድረስ የሚይዝ ግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሽ እስከ 40 ሰዎች የሚይዙ የተለያዩ መለስተኛ አዳራሾች እና ዘመናዊ የሚዲይ ስቱዲዮዎች በልኀቀት ማእከሉ የሚካተቱ ናቸው። ለማኅበሩ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ቢሮዎች እና በቂ የመኪና መቋሚያም የማእከሉ ግንባታ የሚያካትታቸው መሆኑ በውይይቱ ተገልጿል :: ይህን ማእከል ለመገንባት 4 መቶ ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን እስካሁን በተከናወነው ሥራ የከርሰ ምድር ቁፋሮን ጨምሮ ከመሬት በታች ያሉት ሥራዎች ተከናውነዋል ::