176 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግዱ የለይቶ ማቆያ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል ተባለ!
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር እንዲያስችል በሀገር አቀፍ ደረጃ 176 ሺህ ሰዎችን ማቆየት የሚያስችሉ 170 የለይቶ ማቆያ ቦታዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ስር የሚገኘው የለይቶ ማቆያ ስፍራችና ሎጅስቲክ አስተባባሪ ንዑስ ኮሚቴ በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን ለማቆየት የተዘጋጁ ሥፍራዎችን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘውን የለይቶ ማቆያ ስፍራን የጎበኙት የንዑስ ኮሚቴ አባላት ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ 200 ሰዎች ወደ ማቆያው እንደሚገቡ አስታውቀዋል፡፡የንዑስ ኮሚቴው አስተባባሪ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደገለጹት በማቆያው የሚጠለሉ ሰዎች የሚያስፈልጉ ምግብን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪያቸውን ዩኒቨርሲቲው በራሱ በጀት ይሸፍናል፡፡በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎች የምርመራ ውጤታቸው እስከሚታወቅ ለ14 ቀናት እንደሚቆዩም ተገልጿል፡፡
ምንጭ: ዋልታ
#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT