በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። ኃጢአትን ከፈጸሙና ከሠሩ በኋላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኃጢአት ነው። በዚህ አይነት ለኃጢአቱ ምክንያት እየደረደረ የሚጽናና ሰው ኃጢአትን እየለመደ ወደ ባሰ አዘቅት ከመውረድ በቀር ንስሐ ለመግባት አይችልም። ምንም ምክንያት ቢደረድር ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነውና። ለሠራነወ ኃጢአት የተለያዩ ምክንያቶችን በማበጀት ራሳችንን እያጽናናን ነፃ ለመሆን መጣር የለብንም ።
ስለ ሰሩት ኃጢአት ምክንያትን የደረደሩ አዳምና ሔዋንም ባቀረቡት ምክንያት ከመቀጣት አልዳኑም ። እግዚአብሔርም አዳም ስለ አቀረበው ምክንያት "የሚስትህን ቃል ሰምተኻልና ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዘዝኩህ ዛፍም በልተኻልና " በማለት ለኃጢአቱ የሚገባውን ቅጣት ሰጠው እንጂ አልተወውም። [ዘፍ3፥17] ይባስ ብሎ በእነርሱ ምክንያት በመጣው መርገም ቅጣቱ በትውልዳችን ሁሉ ሆነ እንደ እነርሱ ሁሉ እኛም ዘወትር ምክንያት በመደርደር ከኃጢአታችን የተነሣ ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ የምንሞክር ሆንን ስለዚህ ንስሐ ለመግባት በጣም ስንቸገር እንታያለን ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ