✧ ገብርኤል በሰማይ ✧
ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር/2/
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር/2/
ትፀንሺ ሲልክ በከበረ ዜና
ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እንዲፅናና
ከገብርኤል ሰምተው መላዕክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ
ብፅሂት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን ልዑል አብነት አድርገን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማህፀንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አገኘነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡት ጋር ብፅሂት ብለናል
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ከተፈጥሮ በላይ ፅንስን ያዘለለ
የእሳት ምሰሶ ባንቺ ተተከለ
የእግዚአብሔር ሀገሩ የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን
ብፅይት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዪት
ሰዉና መላዕክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግርግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግማዊት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ
እጅ እንነሳለን ሁነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነው እና
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯
ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤጥ በምድር/2/
ይመሰክራሉ ድንግል ያንቺን ክብር/2/
ትፀንሺ ሲልክ በከበረ ዜና
ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እንዲፅናና
ከገብርኤል ሰምተው መላዕክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደሪያ ክብርን ይሰጣሉ
ብፅሂት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን ልዑል አብነት አድርገን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ስርሽ በምድር ነው ሀረግሽ በሰማይ
ንፁህ መሶበ ወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማህፀንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አገኘነው
የተሰወረውን መና በልተነዋል
ከተመረጡት ጋር ብፅሂት ብለናል
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ከተፈጥሮ በላይ ፅንስን ያዘለለ
የእሳት ምሰሶ ባንቺ ተተከለ
የእግዚአብሔር ሀገሩ የእንጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን
ብፅይት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤጥን አብነት አድርገን
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዪት
ሰዉና መላዕክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግርግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግማዊት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ
እጅ እንነሳለን ሁነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነው እና
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯