ነይ ሶልያና
ነይ ሶልያና ተጫምተሽ ደመና፣
ነይ አዛኝቱ እመ ትህትና፣
አግዢኝ እናቴ፣
ይሙላልኝ ጉድለቴ፣
አቅርቢኝ ከፊቱ፣
ይማረኝ ምሕረቱ።
እኔ የማላውቀው ብዙ ነው ጉድለቴ፣
ጥሪት አልቆብኛል ባዶ ነው ሌማቴ፣
ምርኩዝ ያደረኩት ድንገት ተቀየረ፣
የእኔ ያልኩት ሁሉ የወረት ነበረ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
በሃዘን ተከብቤ ሰላም ርቆኛል፣
ወገን ዘመድ ሁኚኝ እናቴ ከፍቶኛል፣
የሚያጽናናኝ የለም አይዞሽ ባይ ከጎኔ፣
እመ አምላክ አብሺው እንባዬን ከዓይኔ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
ዙሪያዬን ያጠረው በእሾህ አሜኬላ፣
ጠላቴ እንዳይውጠኝ ሁኚልኝ ከለላ፣
እኔ ኃጢአተኛ ነኝ የለኝ መልካም ምግባር፣
ልጅሽ ፊት አልቆምም በደሌ ቢቆጠር።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
ሸክሙ ከብዶብኝ ቀሏል ማንነቴ፣
አሳስቢልኝ ማርያም የእንባ ነው ራቴ፣
ከስደት መልሺኝ አልሁን ወገን አልባ፣
ከናፈቀኝ ደጅሽ መባን ይዤ ልግባ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
በዘማሪት ሰላማዊት ሶርሳ
ነይ ሶልያና ተጫምተሽ ደመና፣
ነይ አዛኝቱ እመ ትህትና፣
አግዢኝ እናቴ፣
ይሙላልኝ ጉድለቴ፣
አቅርቢኝ ከፊቱ፣
ይማረኝ ምሕረቱ።
እኔ የማላውቀው ብዙ ነው ጉድለቴ፣
ጥሪት አልቆብኛል ባዶ ነው ሌማቴ፣
ምርኩዝ ያደረኩት ድንገት ተቀየረ፣
የእኔ ያልኩት ሁሉ የወረት ነበረ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
በሃዘን ተከብቤ ሰላም ርቆኛል፣
ወገን ዘመድ ሁኚኝ እናቴ ከፍቶኛል፣
የሚያጽናናኝ የለም አይዞሽ ባይ ከጎኔ፣
እመ አምላክ አብሺው እንባዬን ከዓይኔ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
ዙሪያዬን ያጠረው በእሾህ አሜኬላ፣
ጠላቴ እንዳይውጠኝ ሁኚልኝ ከለላ፣
እኔ ኃጢአተኛ ነኝ የለኝ መልካም ምግባር፣
ልጅሽ ፊት አልቆምም በደሌ ቢቆጠር።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
ሸክሙ ከብዶብኝ ቀሏል ማንነቴ፣
አሳስቢልኝ ማርያም የእንባ ነው ራቴ፣
ከስደት መልሺኝ አልሁን ወገን አልባ፣
ከናፈቀኝ ደጅሽ መባን ይዤ ልግባ።
ደግፊኝ ልቁም፣
አግዢኝ ማርያም፣
አሳስቢ ስለ እኔ፣
ይቅለል ሃዘኔ።
በዘማሪት ሰላማዊት ሶርሳ