ቢዝነሳችሁ በመሠረተ ልማት ወይም በጦርነት የተቃወሰባችሁ
1) ካሳ የምታገኙ ከሆነ ሞክሩ፡፡ ግን እኛ ሀገር የሰነድ አደረጃጀታችን ለካሳ ስለማይመች ጊዜና ገንዘብ ባትፈጁ ይመከራል፡፡ የሚያሰጥም ከሆነ እንደ አንድ ጉዳይ ያዙት እንጂ ሕይወታችሁ እዚያ ላይ አይንጠልጠል፡፡ ባይሆን ጉዳያችሁን ተደራጅታችሁ ለጠበቃ ስጡት
2) ፋይናንሻል ሪከቨሪ ላይ አተኩሩ
- መቋቋሚያ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ የልሆኑ ድርጅቶች፣ ወረዳዎች የሥራ ፈጠራ ተቋማትን ቅረቡ፡፡ ቀላል ብድር ፈልጉ
- ከአበዳሪዎቻችሁ ጋር ተደራደሩ፡፡ የቀድሞ ብድር ሠርታችሁ እንድትከፍሉዋቸው እንዲያግዙዋችሁ አድርጉ እንጂ አትራቁ፡፡ ስልክ ዘግቶ መጥፋት ለተጨማሪ ድብርት ይዳርጋል፡፡ ስል ጭንቅላት ይዶለዱማል፡፡
- ቀድሞ ሥራውን ስለምታውቁት በአጋር የሚያሠራችሁ ድርጅት ፈላልጉ፡፡ የሦስት ዓመት ውል ግቡ፡፡
- ከባንክ የተበደራችሁም ከባንኮች ጋር የብድር ሪስኬጁል እና አማራጮች ተነጋገሩ፡፡ የባንኮች የሐራጅ ማስፈራሪያ አትፍሩ፡፡ አንድ ባንክ ቢበዛ ሐራጅ የብድሩን 5% ብቻ ነው፡፡ በአብዛኛው NPL (Non performing loan) 3% አካባቢ ነው፡፡ ለራሳቸው ሲሉ ይተባበሯችኃል፡፡
3) ድጋሚ ሥራችሁን ጀምሩ
-ተመሳሳይ መረበሽ የማይገጥማችሁ ሰፈር ወይም ከተማ በመቀየር ያንኑ ሥራ ጀምሩት፡፡ ከመጀመራችሁ በፊት ቢያንስ ሦስት ቦታ ሂዱ፡፡ የመሬት ማኔጅመንት፣ ፕላን ኮሚሽንና የኮሪደር ልማት ጽሕፈት ቤት ጠይቁ
-የወትሮ ሥራ ለምትሄዱበት ሰፈር የማይገጥም ከሆነ ሪብራንድ አድርጉት፡፡ ስሙን ቀይሩት ለማለት ነው፡፡ ለሰፈሩ የሚመች ሐሳብ ለማፍለቅ መንደሩን በእግርም ሆነ በመኪና ዙሩት
-ከስተመር ቤዝ ቀይሩ፦ ወትሮ በጨረታ ወይም እግረ መንገዱን ለሚገዛ እየሸጣችሁ ነበር ይሆናል፡፡ አሁን ጨረታውም በመስመር ላይ (ኦንላይን) ሆኗል፡፡ የሶሻል ሚድያ የሽያጭ አማራጮች ጥሩ ናቸው፡፡
-የጎንዮሽ የተለያዩ ቢዝነስ አማትሩ
-ባልና ሚስት ብቻ ሳይሆን ልጆችም ከሶሻል ሚድያ scrolling ጋብ ብለው ይስሩ፡፡ በቴክኖሎጂ ያግዙዋችሁ፡፡
-ዕድሜያችሁ ገና ከሆነ ለተወሰነ ጊዜ ከሀገር ወጣ ብላችሁ ኑ
4) ሳይኮሎጂያዊ ዝግጅት
-በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሕይወቱን ያጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ አለን፡፡ እናንተ ግን በሕይወት አላችሁ፡፡ ብዙ የምትናገሩት ታሪክ አላችሁ፡፡ መከራ በዘነበ ማግስት ያለ ጥርጥር ጸደይ ይመጣል፡፡ ሱስ ግን በተቸገሩ ወቅት ይብስ ያስቸግራል፡፡ ይህ ምናልባትም ከሱስ መላቀቂያ ምቹ ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡
-የሃይማኖት መሪዎች ቢበላሹ እንኳ ቅዱሳት መጻሕፍቱ አሉ፡፡ ትጉና ጸልዩ፡፡
ምንጭ - ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን