እስከዛሬ ድረስ ለዓመታት ዋጋ እየከፈልሁ ያለሁት በአጥማቂው ዮሐንስ ምክንያት ነው። ከምወደው መሥሪያ ቤትም የተፈናቀልሁት በእሱ ጀሌዎች እንግርግሪያ ነው። ግን ባንተ ስሜት ልክ የሚጓዝ መሪ ከሌለህ ሁለመናህም ይወረስብሃል። ይኸው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ድረስ ወረሩን። የመጨረሻውን ጦርነት አድርገን ግልብጥ ብለን መጥተን ሀገረ ስብከት የምትሉትን እንበትነዋለን። ብፁዕ አአቡነ አብርሃም ሆይ ከእርስዎ ጋር ስለ አጥማቂያን ገመና ከማስረጃ ጀምሮ አውርተን ነበርና እኔ በግሌ እንደሚያስተካከሉት ተስፋ ነበረኝ። ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ንዋዕያተ ቅድሳት ዝግጅትና ሽያጭ፣ ስለ አእምሯዊ ንብረት፣ አጠቅላይ መንፈሳዊ ሕትመቶች ማእከላዊ ሆነው እንዲታተሙና ሌሎች ጉዳዮችም ጭምር አውርተን በእርስዎ የሥራ አስኪያጅነት ዘመን እንደሚስተካከሉ ተስፋ ነበረኝ። ግን ብፁዕነትዎ የተለወጠ ነገር የለም ይባሱን ይኸው ሀገረ ስብከት ላይ ሃይማኖተኛ መሳይ ከሃይማኖቱ መንገድ ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ጎረምሶች ዕውቅና ሰጥተው እሾህ እንዲተከል አመቻችተዋል ወይም በቀጥትታ ፈቅደዋል ወይም በዝምታ አልፈዋል።