አንዳንድ እውነታዎች ስለ ካንሰር
━━━━━✦━━━━━
→ ሁሉም ሰው በካንሰር ሊጠቃ ይችላል።
→ ከ100 በላይ የካንሰር ዓይነቶች ያሉ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የካንሰር ዓይነቶችን መከላከል ይቻላል።
→ 90 በመቶ የካንሰር መንስኤ አካባቢያዊ ሲሆን 10 በመቶ ደግሞ ዘረ-መላዊ (ከወላጆች በዘር የሚወረስ) ነው።
→ በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ 25 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል። 90 በመቶ የሳምባ ካንሰር መንስኤም ሲጋራ ማጨስ ነው።
→ አንዲት ሲጋራ ውስጥ ከ7 ሺህ በላይ ኬሚካሎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ የሚበልጡት ካንሰር አምጪ ናቸው።
→ በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ አልኮል መጠጣት ከ3 እስከ 5 በመቶ ድርሻ ይይዛል።
→ ዓለም ላይ ሴቶችን በብዛት የሚያጠቃው የካንሰር ዓይነት የጡት ካንሰር ነው።
→ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ከ25 - 30 በመቶ ይቀንሳል።
→ ወንዶችን በብዛት ከሚገድሉ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ የሳምባ ካንሰር፣ የጉበት ካንሰር፣ የጨጓራ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር እና የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ይጠቀሳሉ።
→ ሴቶችን በብዛት ከሚገድሉ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ የጡት ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር፣ የማህፀን በር ካንሰር እና የጨጓራ ካንሰር ይጠቀሳሉ፡፡
→ ካንሰር የዓለም ኢኮኖሚን ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በዓመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ለካንሰር ሕክምና ያወጣሉ።
→ ትምባሆ ባለማጨስ፣ አልኮል ባለመጠጣት፣ ጤናማ አመጋገብ በመከተል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ የካንሰር ተጋላጭነትን እስከ 30 በመቶ መቀነስ ይቻላል።
━━━━━━