[…ጎንደር - አዘዞ ምን ተከሰተ ??]
ዝርዝር መረጃ!
በመጀመሪያ በመሐል ከተማ ሙስሊሞች የሚበዙበትን የገበያ እና የመኖሪያ ቦታ ሌላ የገበያ አዳራሽ ልንሰራበት በሚል እንዲለቁና ከከተማው ራቅ ብሎ ወደ መተማ መውጫ በስተግራ በኩል ከመከላከያ ካምፕ በመቶ ሜትር ርቀት በቆርቆሮ የተሰራ ጊዜያዊ ሱቆች በመሸንሸን አንዲገለገሉ ተደረገ ።
https://www.youtube.com/channel/UCTBV3GsEgtW6GECdIAzPPLg?sub_confirmation=1
ከዚህ ቦታም ለጊዜው ተብሎ ቢሰጥም ሙስሊሞች በተቸራቸው ቦታ ያለ አንዳች ቅሬታ ከ አሰር አመት በላይ እየተጠቀሙበት ይገኛል ።
እነዚህ ሙስሊሞች አሁን ላይ ከወራቶች በፊት የገበያ አዳራሹ አልቆ ሲያዩ ተደሰቱ ።
እንግዲያው ዛሬ አልያም ነገ ይሰጠን ይሆናል እያሉ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ መንግስትም የሱቆቹን ተመን በማስላት ከ ጉልት እስከ ሰፋፊ ሱቆች እስከ ወፍጮ ቤቶች ሁሉን የሚያስጠቅም በማለት ከ 40ሽ እስከ 1.7ሚሊየን ከፈሉ ብሎ ወሰነ።
ነጋዴዎቹም ካቅማቸው በላይ ስለሆነ ይሄን ብር ከፍሎ ለመግባት ስለማይችሉ በኮሚቴዎቻቸው አማካኝነት ከ መንግስት ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ ባሉበት ተጨባጭ…
ከ 50ቀን በፊት የሙስሊም ወፍጮ ቤቶችና የ እህል መጋዝኖች ከዛው ተጠልለው የሚያድሩም የቁም እንስሶቻቸው ሳይቀሩ ዶጋ አመድ ሁነው አደሩ ።
የዚህ ቃጠሎ ምክኒያቱ ምንድነው? ሲባል መብራት ነው የወፍጮዎ ናፍጣ ነው በሚል ተለባብሶ ዝም ተባለና ተድበስብሶ ታለፈ።
እነሆ የዚህ ቀጣይ ጥቃት እነዚህን ሙስሊሞች መሰረት አድርጎ ጥር 21 ሐሙስ ማታ ላይ በተመሳሳይ ሰአት በተመሳሳይ ሐሙስ ቀን ይሄው የግፍ ታሪክ ተደገመ ።
በተጠና መልኩ ደህና የሚንቀሳቀሱ የሙስሊም የሸቀጥ መደብሮች ፣ የጨርቅ መደብሮች እና ልብስ ስፌቶች እንዲወድሙ ተፈረደባቸው ።
ይህን ከሌላው ግዜ ለየት የሚያደርገው ጥር 21 ሎዛ ጥምቀት የሚከበርበት ቀን ከመሆኑጋ ተያይዞ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ከየአካባቢው የሚሰባሰቡበት ቀን በመሆኑ ያን ቀን እንኳ መንግስት ተብየው እና ከፊት ለፊት ከገብያው በቅርብ ርቀት የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ጥበቃና ከለላ አለማድረጉ ነው ።
የ አካባቢው ነዋሪና ሙስሊሙ ማህበረሰብም ከምሽቱ 4 ሰአት ከቦታው ቢገኝም ቃጠሎውን በርብርብ ማዳን አልቻለም ።
ያልተቃጠለውን ክፍል ግን ከዘራፊዎች እጅ ለመከላከል ችለዋል። ታስቦ የነበረው ግን ግማሹን በእሳት አንድደው ሌላውን ደግሞ እንደ ሞጣው መዝረፍ ነበር።
ሙስሊሞችን ከ አዲሱ አዳራሽ ከፍለው እንዳይገቡ በኢኮኖሚ የማራቅ ፖሊሲ ቀምረው፣ በራሳቸው እንዳይቆሙ ደግሞ ንብረታቸውን የ ማውደም ስራን በጥሩ መልኩ ተወጥተውታል። በቀጣዩም ሙስሊሞች አገግመው ቀና እንዳይሉ ለመኮርኮም የሚደረገው ሴራና ጥቃት እንደየ አካባቢው ቅርፁን እና ይዘቱን እየቀያየረ ጥቃቱም ያለ ከልካይ እየቀጠለ ይገኛል ።
መንግስት አረ ተው ብልና እርምጃ ብወስድ የመጪው ምርጫን ካርድ ከአጥፊዎቹ አካል ላላገኝ እችላለሁ ብሎ የሙስሊሙን በደል ከነካርዱ አልፈልግህም የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰ ይመስላል።
ይህን ተግዳሮት መፍታት ያልቻለ አቅም ይህን የጋጠወጥ የሽፍታ አካሄድ በእንጭጩ ያልቀጨ መንግስት ምን ይዞ ምረጡኝ ሊል እንደሚችል አልተገለፀልኝም ።
እዚህ ላይ የምጨምራቸው እንደሚታወቀው ፖለቲካው ሁሉ ቁማር ነውና ሁሉም የምርጫ 2012 ተወዳዳሪ በምርጫም አሸንፎ አገሪቱን ለማስተዳደር የቋመጠው መንጋ ተቃዋሚም እዚህ ጉዳይ ላይ ለወንበራቸው ፈተና የሚሆንባቸውን ስሌት ቀምረው ከውግዘቱ እራሳቸውን ያሸሹ ነው የሚመስለኝ።
[… እስቴ ፣ ቢቸና ፣ ወፍገጤ ፣ ሞጣ ዛሬ ደግሞ
አዘዞ … የሙስሊም ጠሉ ግፍተራ ይቀጥላል እያለን ምልክት እያየን ነው።
እነርሱ ያቃጥላሉ እኛ እሪ እንላለን የጠፋውን ለመተካት ገንዘብ እናዋጣለን ይህ ድንበር ያለፈ ንቀት ግን ጉዞውን ባለማቋረጥ ቀጥሏል።
አሁን ለዚህ ጋጠ ወጥ ተግባር የማያዳግም እርምጃ ካልተወሰደ የእኛ ነገር ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው። እኛ የምንገነባው መስጂድ እኮ እነዚህ ነውጠኞች ከህግ ውጭ ያለ ያዥ ከቀጠሉ የሰበሰብነው ሚሊዮን ብር በእሳት ላለመበላቱ ምን ደህንነት አለን።
መንግስት ባለበት ሃገር ህግ እና ስርአት ባለበት ተጨባጭ ይህ አድራጎት ከቀጠለ እኛ ሙስሊሞች እንደ ዜጋ የምንቆጠረው ምን ያህል መስጂዶችን በእሳት ስናስበላ እንደሆነ ሂሳብ አድርጋችሁ ንገሩን።
ለዚህ የጭካኔ ጥግ ሰውን የሚገፋፉ አካላቶች በደንብ በመረጃ እየታወቁ ዝም ብሎ መንግስት ንቆ መተው ለወንበሩ የሚበቃ እሳትን እራሱ እያቀጣጠለ መሆኑን ልብ ይበል።
በእምነቱ የሚደራደር ዱሩዬ አካልን ነጥሎ እምነትህ ለአገር አይበጅም ብሎ ከግፍ ጉዞው የሚገታ አቅም በመንግስት በኩል ከሌለ መፃኢው ተስፋ ለሃገሪቱ ትልቅ መርዶ ነው።
በቤተ ክርስቲያን መሽገው የራሳቸው የእምነቱ ቀኖና ሳይገባቸው ቀርቶ በከፍተኛ ጥላቻ ተመርዘው እናንት አማኞች ሆይ እምነታችሁ እኮ ጠፋ ። እንዲህስ ሁነህ ምን ሰላምህን ትናፍቃለህ? አንተ እኮ ሰላምህ ጠፍቷል! እያሉ በየዋህነት ጆሮ ሰጥቶ ያዳመጣቸውን የዋህ ሰው ልቡን አደንድነው ክብሪትና ጋዝ ይዞ ወደ ወገኑና ወደ ጎረቤቱ እንዲዘምት የሚያሰማሩ አስተማሪ ተብዬዎችን በህግ የበላይነት ህግ ፊት አቁሞ ለተግባራቸው አስተማሪ ቅጣት መቅጣትን አሁን ላይ ካልተቻለ እመኑኝ እነዚህ ትንኮሳና ድፍረቶች ወደ ለየለት እልቂት የሚወስዱን መንገዶች ናቸው።