"ስንት አግብተሽ ፈታሽ"
Semir ami✍
... ልትቋቋመዉ ከምትችለዉ በላይ ልቧ ወደሱ ሸፍቷል። አግብቷት እድሜ ልኳን ከሱ ጋር ብትኖር ምኞቷ ነዉ። አሁንም ወደፊትም አላማዋና ፍላጎቷ እሱ ብቻ ነዉ።
የሱ ስልክ ሲጠራ መታገስ አትችልም። በፍጥነት ታነሳዉና ድምጹን ለመስማት ወደ ጆሮዋ ታስጠጋለች። "ሄሎ የኔ ልዕልት" ሲላት አለምን በሷ ግዛት ስር አድርጋ ንግስት የሆነች ያክል ይሰማታል።
"የኔ ... ዛሬ ማታ እፈልግሻለሁ .. እንገናኝ!" አላት። በደስታ ልቧ ቦታዋን ለቃ ፈነጠዘች። ለዛሬ ማታ የምትለብሳቸዉን ለብሶች መምረጥ የጀመረችዉ ስልኩ ከተዘጋ ጀምሮ ነዉ። የቱ እንደሚያምርባት፤ ማንኛዉ ዉበቷን አጉልቶ እንደሚያሳይ በመሞከር .. ስታነሳ ስትጥል ዋለች።
ቀኑ የአመት ያክል ረዘመባት። "መቼ ነዉ ነዉ ማታ የሚደርሰዉ?" በእድሜዋ ብዙ ማታዎችን ብታሳልፍም። የዛሬዉ ማታ ግን የተለየ እንደሚሆን ልቦናዋ ሹክ ብሏታል። የምትለብሰዉን ልብስ መርጣ ጨርሳለች። ከንፈሯ በስተቀኝ በኩል በቀይ ቀለም፤ በስተግራ በኩል ያለዉን ደግሞ በጥቁር ቀለም አስዉባ የጥቁርና የነጭ እኩልነት መገለጫ አስመስላዋለች። ቅንድቧን በደንብ ተኩላ፤ ድንቡሽቡሽ ያሉ ጉንጮቿን ዱቄት አብዛታበት በጠይም መልኳ ላይ ለብቻዉ ጎላ ብሎ የከረመ ቲማቲም መስሏል። ... ምንም አይወጣላትም። በስሜቱ ለሚነዳ ወንድ ታማልላለች፤ አቅሉን ያልሳተ ደግሞ እንደ አሻንጉሊት ቁጥሮ ያልፋታል።
.
... የአመት ያክል የራቀባት፤ በጉጉት ስትጠብቀዉ የነበረዉ ምሽት ደርሷል። የቀጠረባት ቦታ ስትደርስ አከባቢዉ በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ ማብራቶች ተሽቆጥቁጧል። ጨረቃዋ ከላይ ከላይ አዝቅዝቃ እየተመለከተች ከእኔና ካንቺ ዉበት ማን ይበልጣል የምትል ይመስል ከአንፖሎቹ ዉበት ጋር ተደምራ ምሽቱን የተለየ ድባብ ሰጥተዋለች።
የምታየዉን ማመን አልቻለችም። በደስታ ብዛት ነፍሷ በሀሴት ጮቤ ረግጣለች። ግራና ቀኝ እየተመለከተች በተጎዘጎዘዉ ቀይ አበባ ላይ እየተራመደች ወደሱ እየተጠጋች ነዉ። እሱም ቢሆን በጣም አምሮበታል። የእሷን ወደሱ መጠጋት እየተጠባበቀ ፊቱ የደስታ ነጸብራቅ ይረጫል።
አጠገቡ ስትደርስ በጉልበቱ በርከክ ብሎ "የኔ ቆንጆ ታገቢኛለሽ" ሲል ቀለበቱን በጣቷ ላይ ሊያጠልቅላት ዘረጋ። ደስታዋ ወደር አጣ። ይሄን አልጠበቀችም። የጋብቻ ጥያቄ ይጠይቀኛል ብላ በፍጹም አልጠረጠረችም። መናገር እስኪያቅታት ድረስ ስለተደሰተች እየተንተባተበች "አዎ ... አዎ አገባሀለሁ!" ብላ የዘረጋዉን ቀለበት እንዲያደርግላት እጇን ወደሱ ዘረጋች።
"አንቺ .. አንቺ ኢክራም ተነሺ ... ተነስተሽ ሱብሂ ስገጂ" ብለዉ እናቷ ሲቀሰቅሷት ብንን ብላ ስትነሳ በህልሟ ፈክቶ የነበረዉ ፊቷ በእዉኗ ሬት እንደቀመሰ ሰዉ ጭፍግግ አለ።
"እማዬ... ምናለ ህልሜን ብጨርስ"
"ጓደኞችሽ በእዉናቸዉ ያገባሉ አንቺ በህልምሽ እያገባሽ ትፈቻለሽ። ቆይ እስካሁን ስንት አግብተሽ ፈታሽ?"