አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እንደትላንት ተወልደን ዛሬ ላይ እድሜያችን ስንት ደረሰ? ወጣትነታችን ወደ ፊት የሚያራምደን መስሎን ተሞኘን። ዕቃቃችንን ስንጥል፥ ጨዋታችንን አልጠገብንም ነበር። ድክ፥ ድክ ያልነው በወጉ ዳዴ ሳንል ነው። ልባችን ላይ የሚነደው የጉርምስና እሳት ደረታችንን ሲፋጅ ሰፊ መንገድ ያለ መስሎን ነበር።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ከአባታችን ወገብ የተከፈለው ዘር፥ በእናታችን ማኅጸን እንቁላል ሳይመታ፤ ፅንስ ሳንሆን፥ ሥጋችን ሳይቦካ፥ አጥንታችን ሥር ሳይሰድ፥ ጅማታችን ሳይዘረጋ፥ ሽል ሳንሆን በፊት. . . ክፉ ዕጣ ቀድሞናል። አንዳችን ለአንዳችን ጠላት ተደርገናል። ለሞትም ታጭተናል። ሳንመርጥ ወግነናል። ደርሰን ባልበደልነው፥ ባልሠራነው ታሪክ. . . አክ እንትፍ ተብለናል።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እኔና አንተ ምንም እንኳ ወደ ፊት መጓዝ ብንፈልግም፤ ይሄ ሀገር የሚሄደው ወደ ኋላ ነው። ዳገቱን ወጣን፥ አቀበቱን አሸነፍን፥ ተራራውን ረታን ስንል. . . እየተንሸራተተ መቀመቅ ይዞን ይወርዳል። በየቀኑ ትርጉም አልባነትን እንድናንከባልል ተፈርዶብናል።
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
አናምንም። ግን ዕውቀት የማይዘልቀው የድንቁርና እና የአረመኔነት ዘረመል ሥጋ ለብሶ ያለው እዚህ ሀገር ነው። ኅዘንተኞች ሳለን መጽናኛ የለንም። ፍርፋሪ እሴት ሳይቀር ነጠቁን። ረክሰው አረከሱን። የሤራ ፖለቲካው ጉንጉን ፈጣሪ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ በላይ ሳይረቅቅ አይቀርም። እግዚዖ!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ከተወለድን ጀምሮ አላስተኙንም። ታዲያ ሕይወታችን ስለምን ቅዠት በቅዠት ሆነ? ማለት መቼ አስተኝተውን? መቼስ ተደላድለን? እስከ መች እንደምንኖር አናውቅም። ሕይወት አጭር ናት፤ እዚህ ሀገር ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ናት። ሕልውናችን ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ነው። ብንነቃም፥ ብናንቀላፋም ሕይወት ጭራቅ መልኳን ለአፍታ አትቀይርም። የቸገረ ነገር!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
እንዴት እንደሆነ ባናውቅም እንደ ትውልድ አምክነውናል። ሳንወለድ ገድለውናል። የእናት ጡት ሳንጠባ አስረጅተውናል። ቆምረውብናል። ቅያሜውን ሳናውቅ፥ ጦርም ሳንገጥማቸው፥ ያለ ወግ ድል አድርገውናል። ያረፈብን የጀግናም አይደለ፥ የፈሪ ዱላ ነው!
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን?
ዳሩ ምርጫ አልነበረን