ካህሊል ጅብራን
============
ብቸኝነትን የፈለኩት:- ለማምለክ ፣ ለመፀለይ እና የአንድ ፃድቅ ህይወት ለመምራት ብዬ አይደለም ማምለክ ለብቻ ተነጥሎ መኖርን አይጠይቅምና
ብቻኝነትን የፈለግሁት:- ራሳቸውን ሽጠው ፣ በተመሳሳይ ዋጋ በመንፈሳዊም ሆነ በቁስ አካላዊ መስፈርት ከእነሱ ያነሰች ነገርን የሚገዙ ሰዎችን ፊት ላለማየት ስል ነው...
ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በመንገድ ላይ ከናፍሮቻቸው ላይ አንድ ሺህ አይነት ፈገግታዎችን ቢያሳዩም በሺዎቹ ልቦቻቸው ውስጥ በጥልቀት አንድ ብቻ አላማ ያላቸውን በኩራት የሚራመዱ ሴቶች ላለማግኘት ነው...
ብቸኝነትን የፈለግሁት:- የእውቀት መንፈሰ በህልሞቻቸው ውስጥ አይተው ግባቸውን እንደመቱ ከሚያምኑት ከእነዚያ በራሳቸው ከሚረኩት ሰዎች እራሴን ለመሸሸግ ስል ነው...
ከማህበረሰቡ የሸሸሁት:- እውነትን ባያዩም መንፈስ ከማይገነዘቡት እና ለአላማቸው መሳካት ሲሉ ብቻ የእውነትን ፍሬ ነገር ሙሉ በሙሉ እንዳገኙት አድርገው ከሚለፍፉት ለመራቅ ነው።
ከአለም ተነጥዬ ብቸኝነትን የፈለግሁበት ምክንያት:- ትህትናን ደካማነት ፣ ምህረትን ፍርሀት ፣ ትምክህትን ደግሞ የጥንካሬ መግለጫ እንደሆነ አድርገው የሚያምኑትን ህዝቦች በይሉኝታ መቅረቡ አሰልችቶኝ ነው።
ብቸኝነት የመረጥኩት:- ነፍሴ ከነዚህ ፀሀይ ፣ ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት በገንዘብ ካዝናዎቻቸው ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ እንደማይወጡና በእነሱ የአትክልት ስፍራዎች ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንደማይጠልቁ ፅኑ እምነት ካላቸው ጋር አብሮ መኖሩ ስላንገፈገፈኝ ነው...
እናም በአይኖቻቸው ላይ ወርቃማ አቧራ እየጨመሩና ጆሮቻቸውን ትርጉም አልባ በሆኑ ወሬዎች እየሞሉ የህዝቦችንን ምድራዊ ዕጣ ፈንታ ከሚበጠብጡት ባለስልጣናት ሸሸሁ...
እንደስብከታቸው የማይኖሩትንና ህዝቦችን እነሱ የማይፈፅሙትን ነገር እንዲያደርጉ የሚመክሩትን (የሚያስገድዱትን) ቀሳውስት ለመሸሽ ስል ትቻቸው ሄድኩ...
ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በልቤ ሙሉ ዋጋ ካልከፈልኩ በስተቀር ከሰው ልጅ ዘንድ ርህራሄን በጭራሽ ባለማግኘቴ ነው...
ብቸኝነትን የፈለግሁት:- ሰዎች ስልጣኔ ብለው የሚጠሩትን ያ ታላቅና አስቀያሚ ህገመንግስት ፣ ያ በሰዎች ልጆች ላይ ዘላቂ ሙከራ ያመጣ ተመሳሳይ ጎኖች ያሉት ጭራቅ አንገፍግፎኝ ነው...
ብቸኝነትን የፈለግሁት:- በውስጡ ለመንፈስ ፣ ለልብና ለአካል የሚሆን ሙሉ ህይወት ስሌለ ነው።
እናም የፀሀይ ብርሀን የሚያርፋባቸውና መጨረሻ የሌላቸው አበቦች መአዛቸውን ወደ ህዋ የሚተነፍሱበት እንዲሁም ጅረቶች እያዜሙ ወደ ባህር የሚያቀኑበትን የሳር መስክ አግኝቻለሁ።
የፀደይ ወራትን ትኩስ ግንዛቤ፣ የክረምትን ቀለመደማቅ ናፍቆት ፣ የመኸርን ጣፋጭ መዝሙሮች እና የበጋ ወራትን ውብ እንቆቅልሽ ያገኘሁባቸውን ተራራዎች ደረስኩባቸው...
ምንጭ •••የጠቢባን መንገድ ገፅ (115-117)
ደራሲ •••| ኻሊል ጂብራን
@gbw_dan |