Репост из: ስለ ቀልባችን
~ወዳጆቼ! በምድር ላይ ኑሮ ማግኘት ይሁን ማጣት የትርፍ አልያም የኪሣራ ምልክት አይደለም። ትልቁ ማግኘት አላህን ማግኘት ሲሆን ትልቁ ማጣትም አላህን ማጣት ነው። ከሰው ልጆች ሁሉ አላህ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው በአላህ አምኖ እሱን የፈራ ሙእሚን ነው። ከአላህ ጋር መነገድ ከፈለግን እሱ ዘንድ ትልቅ ዋጋ የሚያወጣልን ነገር ኢማን ነው። ምድር ላይ ስንኖር በርካታ ድሎችን ልንቀዳጅ እንችላለን፣ ትልቅ ድል አስመዝግበናል ብለን በልበሙሉነት መናገር የምንችለው ነፍስያችንን አሸንፈንና ተቆጣጥረን በእጃችን ያስገባናት እንደሆነ ነው።
● ያ ረብ!
እየወደቅንም እየተነሳንም ወዳንተ መጓዝ፤ ካንተ መድረስ ነውና ህልማችን አንተ እገዘን!
= t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
● ያ ረብ!
እየወደቅንም እየተነሳንም ወዳንተ መጓዝ፤ ካንተ መድረስ ነውና ህልማችን አንተ እገዘን!
= t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8