ባልና ሚስት በፍች በሚለያዩ ጊዜ ህፃናት ልጆችን መበቃቀያ ማድረግ አይገባም። አንዳንድ ወንዶች ጨቅላ ህጻንን ከእናት በመንጠቅ መበቀያ ያደርጋሉ። እንደዚሁም አንዳንድ ሴቶች ልጁን አስታቅፌ ህይወትን ፈተና አደርግበታለሁ በሚል አጉል እሳቤ የአብራካቸውን ክፋይ ልክ እንደማይረባ ቁስ ገፍተው ይሰጣሉ። እዚህ መሀል ላይ ልጆች ብዙ ግፍና መከራ ያስተናግዳሉ።
ሊሰመርበት የሚገባ ነገር ቢኖር አብሮ መኖር ያልሆነላቸው ጥንዶች እንደ ጠላት ሊተያዩ አይገባም። በመሀላቸው የማይበጠስ ገመድ አለ፣ ኢስላም። ቢለያዩም እህቱ ነች፤ ወንድሟ ነው። ልጅ ሲኖር ደግሞ የማይቆረጥ ዝምድና ተፈጥሯል። የልጇ አባት ለሴቷ፣ የልጁ እናት ለወንዱ ተራ ሰዎች አይደሉም። ልጆች ለኛ ቅርብ እስከሆኑ ድረስ የነሱ ቅርብ ሰዎች ለኛም ቅርቦች ናቸው። ከዚህም አልፎ አብረው በትዳር የኖሩበትንም ዘመን መርሳት አይገባም። "ምንስ ቢሆን አብረን በአንድ መአድ በልተናል'ኮ!" ይላል ያገራችን ሰው። ልጅ እስከማፍራት የደረሰ ህይወት ሲያሳልፉ ደግሞ ይለያል።
﴿وَلا تَنْسَوُا الْفَضْلَ بَيْنَكُمْ﴾
ወደ ጀመርኩት ነጥብ ስመለስ መለያየት ከገጠመን ፈፅሞ ልጆቻችን መበቃቀያ ልናደርጋቸው አይገባም። እንዲያውም በተቻለ መጠን በወላጆች መለያየት የተነሳ የሚገጥማቸውን ማንኛውንም አይነት ጎዶሎ በመመካከር ለመሙላት መጣር ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewo