🌻ራሀቱል ቀልብ ኢምርዐቱ ሷሊሀ 🌻


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


📲የሴትነቴ ውበት ቻይነቴ ነው።ውበታችን ለውጣችን የዚች ምድር ማስዋቢያ ፀጋነታችን ሁሌ እንሰብካለን ድክመታችን ይታረማል ጥንካሬያችን ይበረታታል ማንነታችን ይታነፃል! ሴትነቴ መከበሪያየ ነው! ድንቅነታችን ከትናቱ አይደለም ዛሬ ይጀምራል! ሴት ሴት መሆን አለባት ።
https://youtube.com/channel/UCn_By35yZhxoNmkLd5PnDhw

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🌹 ከምትወጅው ጋር ሳይሆን
ከማትወጅው ጋር ባለሽ ግንኙነት

✍ የሚስማሙሽ ጋር ሳይሆና የማይስማሙሽ
ሰዎች ጋር የምታደርጊው ግንኙነት

✍ በሀሳብ ከምትግባቡት
ሳይሆን ከማትግባቡት

✍ አንች ከምታምኒባቸው ጋር ሳይሆን
ከማያምኑብሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት

💎🔝 በአስደናቂ ሁኔታሽ በምቾት ውስጥ
ሳይሆን በአስቸጋሪ ሁኔታዎችሽ ውስጥ ውሳኔ
አወሳሰድሽ በደህና ጊዜማ ሁሉም ሰው
ደግ ነው ለሚወደው ሁሉም ሰው ጥሩ ነው
ግን ሁኔታዎች ሲቀየሩ 👍

ሀሳቦች እና አስተያየቶች ሲለያዩ🔝
እውነተኛው ገጸ ባህሪ ይገለጣል!🔝
.
#ነፋሳችን ትመከር!

ምሳሌ እኔ ልጄን ወደዋለሁ ምናገረውን
ሲሰማኝ ሲታዘዘኝም ሳይረብሽ ሲቀር
ቤት ሳያቆሽሽ ሳይጮህ ብቻ በጥቅሉ
እኔ እምፈልገውን ሲያረግልኝ ጥሩ ጥሩ
ነገር አረግለታለሁ ለየት ብሎ
ማልፈልገውን ሲያረግ እቆጣዋለሁ
ምናልባትም አስለቅሰዋለሁ!
በመጠኑ የማረገው ቀርቶ ያለውን
እቀማዋለሁ እሱም በተናደደበት
ስአት ጥሩ አደለሽም ይለኛል ሲረጋጋ
ጥሩነሽ ይለኛል ልጅ ያው ልጅ ነው ካልተኮተኮተ
አይሆንም ይህ ህይወት ግን በዙሪያችን ባሉ
ሰዎችም ላይ አለ!!

ጥሩ ስነ ምግባር ያለው ሰው በክፍው
ጊዜም ጥሩ ነው!

~ በሁላችንም ሀያት ያለ ነው እስከ ወደድናቸው
እስከተስማሙን ድረስ ሁሉም ለሁሉም ጥሩ ነው!
ለየት ስንባባል ትክክለኛ ማንነት ይወጣል!

~ የትክክለኛ ስነ ምግባር ባለቤትነት
ራሳችንን የምንፈትሸው በፈተናዋ ስአት
ነው ወዳጅ ጠላት ሲሆን ያመንሽው
ሲከዳ ሀሳብሽ ሲለያይ ባንች ላይ ሲዶልቱ
ሲያስመስሉብሽ ሲዋሹብሽ
ሲቀጥፉውብሽ በምትሰጭው
ምላሽ ይወሰናል!!

~ አስተውይ ሰዎች የራሳቸው ጉዳይ
ልብሽ እንዳይቆሽሽ ህሊናሽ እንዳይሞት
ሚሊየን ጊዜ ራስሽን ወደሽ ስነ ምግባርሽን
ለማነፅ ሞክሪ ራስሽን ለመሆን ያለሽ
አማራጭ ይህው ነው ።።
ከፍ እንድትይ ካንች በታች እና የወረደ
አመላካከት ያላቸው አንችን ከማናናቅ
ስህተትሽን ከመፈለግ ሀሳብሽን ከማርከስ
ውጭ ሊያረካቸው የሚችል የራሳቸው የሚሉት
ነገር የላቸውም!!!

የሚመጣውን በጥሩ መመለስሽ
ደረጃቸው ሁሉ ላቅ ያለውን የሀቢብሽን ሱና
ሀይ ማረግሽ ደረጃሽን በጀሊሉ ላቅ ማረግሽ
ነው አበደን እንዲያደፈሩስሽ እድል አትስጫቸው!!!






Репост из: የአፍሪካ አካዳሚ ዲፕሎም ፕሮግራም - የሶስተኛው ዙር ቻናል
✨አፍሪካ አካዳሚ 3ኛውን ዙር የሸሪዐ ዲፕሎም ትምህርት መመዝገብ ለፈለጋችሁ ባጠቃላይ ምዝገባ መጀመሩን ያበስራችኋል።

📲 የመመዝገቢያው ኪው አር ኮድ ወይም ሊንክ
https://t.me/africaacademy_diplom3

⭐አካዳሚውን ልዩ የሚያደርገው:
💵 በነፃ መሆኑና ለሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ወንዶችም ይሁን ሴቶች ምቹ መሆኑ፤
💻 በስልክ ወይም በላፕቶፕ ባሉበት ቦታና ርቀት ለመማር ምቹ መሆኑ፤
📚የትምህርት አሰጣጥ መንገዱ እጅግ ያማረና ገር መሆኑ፣ እንዲሁም በተመረጡ ዑለሞች የሚሰጥ መሆኑ፤
🗒️ለየሁሉም የትምህርት ክፍል በይሳምንቱና ትምህርቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጡ ፈተናዎች መኖራቸው፤
🎊ላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑና የምርቃት ፕሮግራም የሚዘጋጅ መሆኑ፤

📖በአካዳሚው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች:
1 - ሲራ
2 - ዓቂዳ
3 - ፊቅህ
4 - ተርቢያ
5 - ተፍሲር
6 - ሐዲሥ

⏱️የትምህርት ቆይታው አንድ አመት ሲሆን በሁለት ሴሚስተሮች የተከፋፈለ ነው።

📋ትምህርቶቹ ለተማሪዎች የሚቀርቡት በነዚህ መልኩ ነው:
- በፒዲኤፍ (pdf)
- በቪዲዮ
- በድምፅ

(የመመዝገቢያውን ሊንክ በመጀመሪያው የኮሜንት መስጫ ሳጥንና ባዮ ላይ ያገኙታል።)

✨እድሉ አያምልጥዎ! በዙሪያዎም ላሉ ሁሉ ያጋሩ።


ጥንዶች በራሂ 🌹

ውድ ባልና ሚስት በህይወችሁ
ውስጥ ብዙ አዲስ ፋይሎችን ከፍታችሁ የምታነቡበት ክፍለ ጊዜ መኖር
አስፈላጊ ነው.

በቀላሉ ይችን እራቁ:

↝ ህመምን ሀዘን የሚያስታውስ
ያለፈ ነገር አለመቀስቀስ

↝ ፋይሎች ረጅም አለማረግ

↝ ወቀሳ የወቀሳ መለፍ አለመክፈት.

🌹በጥቂቱ ትኩረታችሁን ስጡኝ
ለአዲሱ ፋይል መሰረት🌹


↝ 🥇Your ፍቅርህን እንደገና ለማደስ

↝ 🥇ልጆቻችሁን ስለማሳደግ

↝🥇 ስለ ወደፊት ..ያማረ ህልም

ምክር ቤቱ በዙሪያችሁ በሚዛን እንዲፈረድ ይህ ይኑረው

 ……አክብሮት እምነት መተናነስ
ብሩህ ተስፋ.……



⚂⚂⚂⚂
JOIN AND SHERE
🥇🥇🥇🥇🥇🥇
JOIN JOIN JOIN
)


*እለተ ማክሰኞ አነቃቂ መልክት*

🎙~•°

።#ትንሽ ጊዜ ለነፍስሽ ስጭ 🎙

💕 •°አዘጋጅ ኢምርዐቱ ሷሊሀ
👉 @IMRATUSUALIHA

🔻 👉 @Rahatul_Qelb

> የጊዜ ቆይታዉ 6:31 ደቂቃ >

➳➳➳ ሼር ያድርጉ ለተጨማሪ
ጆይን በሉ!! ➢➢➢
T.me/RAHATUL_QELB


https://t.me/Rahatul_Qelb


በአላህ ላይ እምነት እና ተስፋው የለመለመ ሰው የትም ቢጥሉት የትም ቢወድቅ አይገርመውም ከምንም መነሳት ማለፍ እንደሚች በርግጠኝነት ያውቃልና።
አትፍሩ ባለባችሁ ጫና አትስጉ በደረሰባችሁ ኪሳራ
አትጨነቁ ባላችሁበት መከራ ያልፋል ፈተናውም ይታለፋል ህመም ይሽራል ማጣትም ይታበሳል ማግኝት ይመጣል እዳም ይከፈለል አንገት ተደፍቶ አይቀርም ቀና ማለት ይመጣል ሀዘንም ይረሳል ተጨንቆ አይቀርም ደስታ ይወርሰናል
አይዞን አላህ ሁሉንም ሀጃ ላይፈርጀን አልሰጠንም ።
የማንችለውን አላሸከመንም በርታ በሉልኝ ወገኖቼ

ትንሽ ያማረ የሆነ መታገስን እንታገስ
ተስፋችንን ይለምልም
በእምነታችን እንጠንክር
ተወኩላችን ይሙላ
የቂናችን ይጠንክር ………………ኢን ሻ አላህ
አላህ ከታጋሾች ጋር ነው ።
ከአማኞች ጋር ነው ።
አላህ ከተወከሉበት ጋር ነው።
አላህ ከሚፈሩት ጋር ነው።
አላህ ካመኑበት ጋር ነው።
አላህ ከጠየቁት ከለመኑት ጋር ነው ።

ፈ አብሽሩ ነፍሳችሁንም አበሽሩ ………

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድ
ስለላሁ አለይሂ ወሰለም።

https://t.me/Rahatul_Qelb
https://t.me/Rahatul_Qelb


ትልቅነት ጊዜያዊ ፋላጎቶችን ለዘላቂ ነገሮች ሲባል በመተው የሚገኝ ዋጋ ነው። ትልቅ ማንነትን አለማጣት የሞራል ከፍታችሁን አለማጣት ስብእናችሁን መጠበቅ ፍላጎታችሁን ማሸነፍ ትልቅነታችሁን መጠበቅ ነው።

እያመሻችሁ ♥♥


°• ሰባህኩም ቢኸይር 🌹🌹🌹


°• የበደላችሁትን ይቅርታ
ፍቅራችሁን ልትገልጹለት የምትፈልጉትን
ሰው ውዴታችሁን ከመግለፅ ወደኋላ አትበሉ። ህይወት አጭር ናት በፍቅር አጣፍጥዋት
🌹🌹🌹 የጣፈጠ ንጋት 🌹🌹🌹

https://t.me/Rahatul_Qelb
https://t.me/Rahatul_Qelb


#እውነተኛ ሰባህ ♥♥
ሰዎች ባሰመሩት መንገድ ዝም ብሎ መጓዝ በመጨረሻ መንገዳችን ሌሎች ሰዎች የደረሱበት ላይ ያደርስናል ብንቆጭም ጊዜው ረፍዶ ይሆናል …………
የሰው ልጅ ካርቦን ይመስል ቅጅ መሆን የለበትም
ሁሉንም ነገር መርጠን አገናዝበን የመውሰድ ህግ መከተል አለብን
ከሰው ልጅ ጥፋት ስህተት አይጠፋም የቅዱስነት ውርስ ያለው የለምና ሁሌም ሚዛናችን እንጠብቅ ።


لا إله الا أنت سبحانك إني كنت من الظالمين.

እናንተ የተጨነቃጭሁ ወዳጆቼ ሆይ አመስግኑ ……አወድሱ ጌታችን ጥራት የተገባው ብቸኛ ቻይ አሸናፊ ነውና።


❤️❤️ አብሽሩ ያለንበት ሁኔታ ሁሉ
እሱ ወደመረጠልን መልካም ሁነቶች ይቀየራል
ኢን ሻ አላህ በፍቃዱ ሁሉ ይሆናል።❤️❤️😘

https://t.me/Rahatul_Qelb
https://t.me/Rahatul_Qelb


"በህልማችን ወደ ትልቅነት እናድጋለን። ሁሉም ትላላቅ ሰዎች ህልመኞች ናቸው።"

አንዳንዶቻችን ሕልሞቻችን እንዲሞቱ እንፈቅዳለን፤ ሌሎች ግን ይመግቧቸዋል፣ ይጠብቋቸዋል። ወደ ፀሀይ እና ብርሃን እስኪያወጡዋቸው ድረስ በመጥፎ ቀናት ውስጥ ይመግቧቸዋል። ይህም ሁልጊዜ ህልማቸው እውን እንደሚሆን ከልብ ለሚመኙት ነው


❤️❤️❤️


አስቸጋሪ ጊዜዎች ቀላል እንዳልሆኑ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብንሆን (ሀኪሙ ወዱዱ ጌታችን) በጥበቡ የሚበጀንን እንደሚመርጥልን አስታውሱ ። እሳቤያችሁ ከፍ አድርጉ በፈገግታ ተሻገሩ።
ምክንያቱም ነገ አዲስ ተስፋ ይዟል………ዛሬም አዲስ ነገር ይዞ መጥትዋል ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ።

መልካም ነገሮች ሁሉ ካንተ ናቸው ።
የሚሆነው ሁሉ ሚሆነው ለበጎ ነው።
ቀናችን ስራችንም ያማረ ይሁን።

https://t.me/Rahatul_Qelb


ሰው ፀባዩን ከገራውና ካፀዳው ወደ ላቀ ማንነቱ ከፍ ይላል። መረን ከለቀቀው ግን ከሚገባው ክብሩ ይወርዳል። ክብራችሁን ጠብቁ
ሰባሁል ኸይር♥


1)    አል-ፋቲሐህ
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

1:1 - በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

1:2 - ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤

1:3 - እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

1:4 - የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡

1:5 - አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

1:6 - ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

1:7 - የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡


"ትዳር በሚስት ውበት ወይም በባል ገንዘብ
ብቻ አይገነባም."

ትዳር በመካከላቸው ባለው መከባበር የተገነባ ነው ።

ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ የሴቶችም ውበት ይጠፋል
የወንዶችም ጥንካሬ ይዳከማል

በጥንዶቹ መሀከል ከመዋደድ እና ከእዝነት በስተቀር
የሚቀር ነገር የለም። ❤

አንዲት ሴት ከባልዋ ጋር አማን ደህንነት ታገኛለች
ወንዱም ከሚስቱ ጋር እረፍት ብርታት እና ደህንነት
ይሰማዋል ♥ ”

ጥምረት ከምታከብሩት ጋር… …………¶ 🫀🌸


ልቤን ነካኝና ላካፍላችሁ ወደድኩ

‍ እዲህ ነበሩ የኛ ነብይ ፣የኛ ረሱል ﷺ

ረሱል ﷺ ወደ መስጂድ ለመሄድ የሚጠቀሙት መንገድ ጠብቃ
"ቆሻሻ" የምትወረውርባቸው አንዲት አዛውንት ነበረች። ነብያችንﷺ በየቀኑ ወደመስጂድ ሲመላለሱ እየጠበቀች "ቆሻሻውን "ትደፍባቸዋለች ነብያችንም ﷺ ችለውት በዝምታ ምንም አይነት መቆጣትን ሳያሳዩ ያልፍሉ። ይህ የተለመደ ክስተት ሆኗል። አንድ ቀን የአሏህ መላዕክተኛ ﷺ በመንገዱ ሲያልፍ እንደ ወትሮው ቆሻሻ የምትደፍባቸው ሴት የለችም። ነብያችንﷺ በቦታው ላይ ቆመው ስለ ጤንነቷ ጎረቤቷን ጠየቁ።

የሴትዬዋ ጎረቤትም አዛውንትዋ ታማ አልጋ ላይ እንደተኛች ነገሯቸው። የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ ወደ አዛውቷ ቤት መግባት እንደሚችሉ በትህትና በመጠየቅ ሲፈቀድላቸው ገቡ።

ሴትዪዋ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ን ስትመለከት ለበቀል እንደመጡ በማሰብ አቅሜ ሲደክም በሽታ አልጋ ላይ ሲያስተኛኝ ልትበቀለኝ መጣህ?

አለቻቸው።"እርሳቸውም" የመጡት ለበቀል ሳይሆን መታመሟን በመስማታቸው አዝነው ሊጠይቋትና የምትፈልገው ነገር ካለ ሊያሟሉ ፍቃደኛ መሆናቸውን ገለጹላት።

አዛውቷም ከመገረሟ የተነሳ መናገር አቃታት። በአትኩሮት ትመለከታቸው ጀመር "ከዚያም እንዲህ አለች አንተ " እውነተኛ "የአሏህ መልዕክተኛ" መሆንህን እና አሏህም ጌታህ መሆኑን እመሰክራለሁ በማለት እስልምናን ተቀበለች። ሱበሃን አሏህ!!

እንዲህ ነበሩ ነብያችን ﷺ እጅግ በጣም አዛኝ ተፈቃሪ ፦አዛውቱ ህጻን ሳይሉ ሁሉንም በቸርነት የሚያስተናግዱ ምርጥ ነብይ!!!!ﷺ ﷺﷺﷺﷺﷺ

በቀን በቀን 1የረሱል ...🌹 ﷺሀዲስ መስማት ከፈለጉ ቴሌግራም ጉሩፓችን ይቀላቀላሉ
https://t.me/+W3eSM3pq7E5mNDc0
✨━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━✨
አንተ ረሱልን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የተሳደብከው ሰው እንዲህ በሰደብካቸው ግዜ እሳቸው በሀያት ቢኖሩና

በስድብህ ንዴት የአለም ሙስሊም ህዝብ በሙሉ አንተን ሊገድል ቢመጣ

እሳቸው ግን ከኋላቸው ሸሽገው እንዳትገደል ይከላከሉልህ ነበር እሳቸው እንዲ ናቸው አንተ ሰደብካቸው።

ፊዳ ልሁንልሎ ያሀቢበላህ❤️❤️❤️






ከሌሊት ቅዥትሽ ከቀን መንከራተትሽ ከረጅሙ የህይወት ጉዞሸ አንዴ ቆም በይና ዙሬያሸን አሰስ አርጊ ።
ታቻምናን ከአምና አምናን ከዘንድሮ አስተያየው ሁሉም ነገር ተቀያያሪና እንዳልነበረ ሆኖ ታገኝዋለሽ
አምና ልሙትልሽ ሲልሽ የነበረው ዛሬ ከነመፈጠርሸ እረስቶሻል ከሀሳቡ እንደ በጋ ጉም በነሽ ጠፍተሻል
ስለዚህ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሰውም ተቀያያሪ ነው ፡፡
ሰው ሰው መሆንን ትቶ ጊዜ መምሰል ከጀመረ ቆይትዋል፡፡
ሰው ጊዜን ሲመስል ጊዜ ግን ሰውን መሆን አይችልም
ምክንያቱም ተፈጥሮ እንደሰው ተቀያያሪ አደለም ፡፡

እስኪ ራስሽን አየት አርገሽ ቀየር ማለት
ወደምትፈልጊው መንገድ
ለመቀየር ሞክሪ #መልካም ቀን ይሁንላችሁ ውድ እህቶቼ 🙏

Показано 20 последних публикаций.