✨TOT እንዴት እንመዘገባለን? ከ8 መቀመጫ በታች ሁነው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በሙሉ አመታዊ የገቢ መጠናቸው ከ2 ሚልዮን በታች ከሆነ ግብር በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ሂደው የ10% TOT ሪሲት ማሳተም እንደሚፈልጉ ገልፀው አሰራሩ በሚፈቅደው መንገድ የTOT ተመዝጋቢ መሆን ይችላሉ:: በዚህም መንገድ ከመንገድ ላይ ያለሲስተም በሚጭኑበት ግዜ ለደንበኛው ሪሲት መስጠት ይኖርባቸዋል:: በአንፃሩ በራይድ ሲስተም ተጠቅመው ሰርተው ከሆነ ራይድ ኤሌክትሮኒክ ሪሲት ስለሚሰጥ ለደንበኛው ምንም አይነት ሪሲት መቁረጥ ሳያስፈልጋቸው በቴክኖሎጂ ማስተናገድ ይችላሉ::