አልተዛወረችምና እውናዊ ልብ ወለድ
[ኂሳዊ ዳሰሳ]
በሳሙኤል በለጠ
"የልብ ወለድ ደራሲ ወይ ነገር ተመልካች ወይም ደግሞ አመላካች ነው። በተጨማሪም በልብ ወለዱ በሬካታ ተሞካሪ ነገሮች አሉ፥ ወይ እውነት ይሰጥሃል ወይ የእውነቱን መነሻ ነጥብ ታገኝበታለህ፥ ገጸ ባህሪያት የረገጡትን ምድር አልፎም ማለዳና ጨለማውን ለማሳየት ገጸ-ባህሪ ፈጥሮ የሰውንና የተፈጥሮን ምስል ያሳይሃል።"( Émile Zola, The Experimental Novel, p. 8 )
ደራሲ ገጣሚና ኀያሲ በዮሐንስ አድማሱ በ1961 ዓ.ም በጻፉት "የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ" በሚለው ኂሳቸው ላይ በዘመኑ የነበሩ የልቦ-ለድ መጽሐፎች በሦስት መሰረታዊ ምክንያት ጥሩ እንዳልነበሩ ይነግሩናል።
ሀ/ በቴክኒክ ጉድለት፤
ለ/ በሒስና በሐያሲ እጦት፤
ሐ/ በደራስያኑ አማርኛ መበላሸት።
የነፍቅር እስከ መቃብር ዘመን አልፎ ያልተቀበልናቸው እነ ዳኛቸው መጥተው ልቦለዳችን ወደ ድህረ-ዘመናዊው አጻጻፍ በነ አዳም ረታ፣ በነ ስንቅነህ እሸቱ(ኦ ታም ፕልቶ)፣ በነ ሌሊሳ ሲተካ የልብ ወለዱ ዘርፍ አበበ ነገር ግን አሁንም ዮሐንስ አድማሱ ያነሱት ጉድለቶች ነበሩ ወደ ተነሳንበት እንምጣ አሌክስ አብርሃም በሥስት የሥነ-ጥበብ ዘርፍ ማለትም በግጥም፣ በአጫጭር ልብ ወለድ፣ አሁን ደግሞ በረጅም ልብ ወለድ በዚህ ዘመን ብዕራቸው ከደመቀላቸው እንዲሁም ሠፊ አንባቢ ማግኘት ከቻሉ ደራሲዎች ተርታ ለመሰለፍ ችሏል።
ለዛሬ በሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ገጽ በአራት ክፍል የተከፈለውን "አልተዛወረችም" ሲል አሌክስ ርዕስ የሸለመውን መጽሐፉን ከእውናዊ(Realism Literature) የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃል አንጻር እንመልከተው ሁሌም እንደምጽፈው ሥነ-ጽሑፍ በተለያየ ዲሲፕሊን ሲኄስ የኀያሲው ምልከታ እንጂ ደራሲው እንደዛ አስቦ ላይጽፈው ይችላል።
እንሂድ ዳኛቸው ወርቁ ከሞልቬር ጋር በነበረው ቃለ-ምልልስ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር "Good Literature reflects the life and spirit of a people"¹ (ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ የሚህበረሰቡን መንፈስና ሕይወት የሚያንጸባርቅ ነው።) የአሌክስ አልተዛወረችም የማሕበረሰቡን መንፈስና ሕይወት በማንጸባረቁ ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ይካተታል እንበልና ወደተነሳንበት ጉዳይ እንዝለቅ:-
ሀ.የአጻጻፉ ይትባህሉ ምንነት!
ሪያሊዚዝም በአሌክሳንደር ሹሽኪን የተዋወቀ ርዕዮተ ዓለማዊ የአጻጻፍ ፍልስፍና ሲሆን በራሺያ በሥፋት የተሰራጨ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ሪያሊዝምን ያጠኑት ደራሲና ኀያሲ ኤምሊ ዞላ እንደሚሉት ከሆነ የአጻጻፍ ይትብሃሉ እሙናዊ(faithful) በሆነ መልኩ ሕይወትን ድጋሚ መግለጽ ነው።² እውናዊ ሥነ-ጽሁፍ እንዲህ ይተረጎማል።
ለ. ጭብጥ (Themes)
አንድ ልቦ-ለድ ልብ ወለድ ከሚያስብሉት አንዱ ጭብጥ ነው። ነገር ግን በእውናዊ (Realism) አጻጻፍ ጊዜ ጭብጡ ሊያንስ ይችላል።³ "ዓይኖቿን ጨፍና ዕንባዋ ጠይም ጉንጮቿ ላይ ግራና ቀኝ ወደ ጆሮዋ እየፈሰሰ ነበር"(©አልተዛወረችም ገጽ-31) ይሁንና የሥነልቦና መደፍረስ፣ የሰውነት ግንብ በሌላ ሲናድ፣ ፍቅር፣ ጥላቻና ብቸኝነት ተራኪውን አብርሃምን የልቡ ጓዳ ገብተው የሚጎበኙት ስሜቱች ሲሆኑ ማህደርና ዮናስም የሚታመሱበት ትራውማ(ሽብር) በመጽሐፉ ተተርኳል።
ሐ.መቼት(Setting)
እውናዊ የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃልን ያጠኑ ምሁራን እንደሚሉት ከሆነ መቼና የቱ ተለምዷዊ(ordinary) ነው ይላሉ "ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤቱና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ"(©አልተዛወረችም ገጽ-54) የአልተዛወረችም መቼት ቀለል ያለና ተለምዷዊ ነው። ደምሥራ ሳይቀር ውበት የሞላባት ማህደር ከንፈሯ የማደንስበት ካፍቴሪያ እንዲሁም የአብርሃም ቤት የልብ ወለዱ ተለምቶሻዊ መቼና የቶች ናቸው።
መ. Causality built into text
የሠው ልጅ የኅላዌ ጣጣ አያበቃም⁴ ከዚህም አልፍ በጥላ(shadowed) ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ግን የሰውን ዘለለት ያበራያሉ⁵ ወይም ያፈካሉ ይሄንን መመርመር የሥነ-ጽሑፍ በተለይም የእውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል መገለጫው ነው። "ባሌ ዕረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሊመለስ ሲዘጋጅ፣ በመለያዬታችን እንደ ሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።"(©አልተዛወረችም ገጽ-68) ማህደር የአብርሃምን የዕድሞ⁶ ጫፍ ጣቱ ሲነካው ተራኪው አብርሃም የነፍሱ ጫፍ ላይ ሲደርስ መልኳን ተመልክቶ ብቻ ለመኖር ሲጓጓ የኦሄነሪን "The last leaf" ያስታውሰናል። ኦ ሄነሪ ጆንሲን ገጸ ባህሪ አድርጎ በተረከው ትረካ ጆንሲ የሚረግፉ ቅጠሎችን ስታይ የመኖር ነገሯ እየጠወለገ ሲመጣ መጨረሻ ቅጠል ቀረች እሱን እያየች መኖር ቀጠለች ይሄንን ሥዕል ሲስል የነበረው በህርማን በበሽታ ይሞታል። የማህደር የሕልሟ መክሰምና የልጅነት ትራውማ(ሽብር) የአገር እንደ ጀንበር መንጋደድ የተደበቁ የሁላችንም ጥላ ታሪኮች የዛሬ አካላችንን የሠሩ ናቸው። አሌክስ ይሄንን በደንብ ተርኮልናል።
ሠ.ፍልስፍና (Emphasis on morality)
ማህበራዊነት ፍልስፍናና ፍልሱፋን የተብሰከሰኩበት የፍልስፍና ዐይነት ነው። እውናዊ አሳቢያን ደግሞ ለሥነ ምግባር አጽንዖት ሲሰጡ ውስጣዊ አንጻራዊ ነው። ይላሉ ሆኖም ይህ አስተሳሰብ ማሕበረሰብን በደገኛ ይሰራል። እውናዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ያሉ ገጸ-ባህሪዎች መዳረሻቸውን ጨብጠው ማህበረ-ከባቢውን ያሳዩናል። ነገር ግን ልብ ወለዱ ሲያልቅ ለአፍቃሬ አንባቢው ሐሳቡም፣ ስሜቱም፣ እውነቱም፣ እምነቱም፣ ክፍት ነው። "ትንሽ ሐውልት ውለታቸው ባረፈበት ሰው ልብ ቢቀር ምኑ ነው ክፋቱ!?" (©አልተዛወረችም ገጽ-239)
ማጠቃለያ
ይኽ የአሌክስ የመጀመሪያ የረጅም ልብ ወለድ ሥራው ነው። እውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል(Realism Literature) በአልተዛወረችም ልብ ወለድ ውስጥ እንዴት ስላለው ተጽኖ የተሰማኝ ይህ ነው። ሌሎች የሥነ-አዕምሮ፣ የፍልስፍና፣ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎችም ልብ ወለዱን ወደራሳችሁ ቤት ብትጋብዙት እላለሁ!
የሕዳግ ማስታወሻዎች
1.Dannyachew Worku in "Black Lion" -An Overview By Sebhat G/Egziabher p.2
2.ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም እንዲል መጽሐፉ የሥነ-ጽሑፍ ሰው የሚታወቅን እንደማይታወቅ የማይታወቅን ደግሞ እንዲታወቅ አድርጎ መጻፍ እንዳለበት ይላል ደራሲ ሳሙኤል ጆንሰን
3.Themes are less obvious Indira Gandhi National Open University American Drama P.128
4.ኀያሲ ዓብደላ እዝራ
5.why something happens foreshadowed Foreshadowing in everyday