ታሕሳስ ፴ /30/
በዚቸም ዕለት ተጋዳይ የሆነ ዘካርያስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በእግዚአብሔርም ፈቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያት ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ።
ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የሀገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው። ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ሒዶ የምንኲስናን ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው።
የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስከአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ በሆሳዕናም ዕለት ወደ አበምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያበራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አገኛቸውና አብሮዋቸው ሔደ።
ከዚህም በኋላ አበምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጎበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎችም በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል አባት ሆይ ሲመግበን የነበረ ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው። አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ።ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@sebhwo_leamlakne