ጥር ፳፯ /27/
በዚችም ዕለት የአዳም ልጅ ኄኖክን መላእክት ይዘው አሳረጉት።
ይኸውም በመባርቅትና በነፋሳት ላይ ተጭኖ በመብረር ወደ ሰማይ ወስደው ከረቂቃን መላእክት ጋር አኖሩት የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ጸሐፊ ተባለ።
በደብር ቅዱስ ለነበሩ ለኃጢአት ለሚተጉ ለሴት ልጆች ይዘልፋቸው ዘንድ ቃል እንደጠራውና እንዳሳየው ተናገረ። በእሳት ቅጽርም የተሠራ በክብር ከሁሉ የሚበልጥ በውስጡም ከፍ ያለ የእግዚአብሔርን ዙፋን አየሁ መልኩም እንደ ውርጭ ነው አጎበሩም እንደሚያበራ ፀሐይ ነው። ከዙፋኑም በታች የኪሩቤል ድምፅ ይሰማል።
በሰማይ ገጽ ስለሚመላለሱ ብርሃናት እንዲህ አለ አንዱም አንዱ በየወገናቸው በሠለጠኑበትና በተሠየሙበት ጸንተው ይኖራሉ ስለ ነፋሳትም መውጫዎች እንዲህ ብሎ ተናገረ ሦስቱ በሰማይ ገጽ ሦስቱ በምድር ገጽ ሦስቱ በቀኝ ሦስቱ በግራ ናቸው። ስለ አዳምም እንዲህ አለ እነሆ በሬ ከምድር ወጣ ፀዓዳም ሆነ ስለ ሔዋንም ደግሞ ሴት እምቦሳ ከርሱ ወጣች አለ።
ስለ ምኵራብም ያንን አሮጌ ቤት እስከሚአሳንሰው ድረስ አየሁ አለ ምሰሶዎቹንም ከውስጡ አወጣ። ስለ ቤተክርስቲያንም ጌታ አዲስ የበጎች ቤት አምጥቶ እስቲሠራ ድረስ አየሁ ከቀድሞውም ቤት የበለጠ ነው በጎችም ሁሉ በውስጧ ይሠማራሉ አለ ። ስለ ምእመናንም የእሊህም በጎች ፀጕራቸው ንጹሕ ነጭ ነው የተበተኑትም ከአራዊት ጋራ ይሠማራሉ ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ገራሞች ሆነዋልና።
@sebhwo_leamlakne