╔════════════════╗
ካፉር አል-ኢኽሺዲ
(ከባርነት እስከ የሙስሊሞች መሪ ኸሊፋነት)
╚════════════════╝
ጥቁር ጀንደረባ ነው። አጭርና ወፍራም፣ አስቀያሚ መልከ ጥፉ መልኩ መስህቦቹን አሳጥተውታል። የታችኛው ከንፈሩ የተገለበጠ፣ የተወላገዱ እግሮች ባለቤት ነው። ቀርፈፍ ያለ እግሮቹ ሰውነቱን መሸከም ይከብዳቸዋል። ካፉር አል-ኢኽሺዲ ይባላል።
በኑባ የባርያ ገበያ ተሽጦ ወደ ግብፅ ጉዞውን ጀምሯል። እጁ በሰንሰለት አብሮ ወደተጠፈረው ባርያ ዞሮ ስለ ወደፊት ምኞቱ ጠየቀው በርሀብ ሆዱ እየጮኸ የነበረው ሰው እንዲህ ሲልም መለሰለት "በፈለግኩበት ጊዜ የፈለኩትን መብላት እንድችል ምግብ ሰሪ ብሆን እመርጣለሁ" አለ።
እሱም በተራው ካፉር ኢኽሺዲን ስለምኞቱ ጠየቀው "የዚህች ሀገር ባለቤት መሆን እመኛለሁ" ሲል ካፉር መለሰ። ለገበያ የቀረበ ባሪያ ሻጮቹን ለመምራት አሰበ። በሰዎች እየተገዛ የሚሸጥ ኒያውን ከፍ አድርጎ የመሪነት ዙፋኑ ላይ ተደላድሎ ህዝብን ሲመራ በሐሳብ ነጎደ። በተንፈላሰሰና በወርቅ በተጌጠ አልጋ ላይ ተኝቶ ሀገሩን በፍትህ ሲያስተዳድር በዓይነ ህሊናው ታየው። "ይህንን ሀገርና ህዝብ ማስተዳደርን እመኛለሁ" ሲልም በእርግጠኝነት ተናገረ።
ካፉር ኢኽሺዲ ለአንድ የዘይት ነጋዴ ተሸጠ። ሰውየውም በተለያዩ ስራዎች ላይ አሰማርቶ ጉልበቱን በዘበዘው። ለዘይት አገልግሎት የሚሆን እህል አጭዶና አዘጋጅቶ፣ በእግሩ እየረገጠ የጨመቀውን ዘይት በማሰሮ ሞልቶ በትከሻው ላይ ይጭንና በየመንገዱ እያዞረ ለፈላጊዎች ይሸጣል። ዘይት በነካካው እጆቹ እሳት እያቀጣጠለ ምግብ ያበስላል። አረፍ ብሎ የሚተኛውም መሬት ላይ ነው። ፍራሽም ሆነ ምንጣፍ አያውቅም። ከዚህ የእለት ተእለት ተግባር በተጨማሪ የአሳዳሪው ዘርፈ ብዙ መከራዎች እየተፈራረቁበት ችግሮችን ለመጋፈጥ የሚያስችለውን ጥንካሬ አላበሰው። በእርግጥም ጠንካራ ሰው አደረገው።
ዘይት ነጋዴው የበለጠ ትርፍ ያመጣ ዘንድ መህሙድ ቢን ወህብ ለተባለ በስነ ፅሑፍ ለመጠቀ ሰው ሸጠው። ከዘይት ፍሳሾች እጆቹን አፅድቶ የንባብና የፅሑፍ መንገድን ተቀላቀለ። ከፊደልና ከወረቀት ጋር ተፋጠጠ።
በወቅቱ ግብፅን ያስተዳድር የነበረው የአባሲያ ኸሊፋ በሺዐ ፋጢሚያ ኢንፓየር ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ሙሐመድ ቢን ጠግጅ የተባለን ቱርካዊ ወጣት የሾመበት ወቅት ነበር።
ካፉር ኢኽሺዲ የፅሑፍ ትምህርቱ ላይ ጎብዟል። ቋንቋም አቀላጥፎ ይናገራል። አሳዳሪው ከግብፁ ገዥ ጋር ወዳጅ ነበር። ታዲያ አንድ ቀን ካፉርን ለግብፁ ገዢ ውድ እቃ በመጠቅለያ አሸብርቆ ስጦታን ያደርስ ዘንድ ላከው። ካፉር ወደ ቤተ መንግስቱ አምርቶ ስጦታውን አስረከበ። የግብፁን መሪ ቀልብ ገዛ። ይሸጥ ይሆን በማለት ጓደኛውን ጠየቀ። ልቡ የተማረከበትን ሰው ወዳጁ በስጦታ አበረከተለት።
ካፉር የቤተ መንግስት ህይወት የተመቸው ይመስላል። በደስታ ያጣጥማት ይዟል። በመላላክና ስራዎች ላይ በመጠመዱ በጣም ቀሎታል። ቤተ መንግስቱ እንዳሻው የሚቦርቅበት ሥፍራም ሆኖ ዓመታት ነጎዱ። የግብፁ ገዢም ወደማይቀረው ሞት ተጓዘ። ኡንጆር የተባለ ትንሽ ልጅ ነበረው። አገልጋዩ ካፉርን ለልጁ እንደ ጠባቂ አድርጎ ሾሞታል። የትንሹ ልዑል ጠባቂ ሆኖ ኃላፍትናውን ተቀብሏል። ኦንጆር ከሁለት አመት በኋላ የአባቱን መንገድ ተከተለ። ወንድሙ አሊ አሚር ተደርጎ ተሾመ። የግብፅ ሰዎች በእርሱ ላይ አደሙ። ከመዝናናት አሊያም ከሰላት በስተቀር ምንም ሥልጣን እንዳይኖረው ተደርጎ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆነ።
አሊም ቀነ ቀጠሮው ደርሶ አፈር ለበሰ። ካፉር አል-ኢኽሺዲ ራሱን የግብፅ መሪ አድርጎ ሾመ። "ኢኽሺዲያ ሥርወ መንግስትን" መሰረተ። የኢስላም ጠላቶች በጀግንነቱ የተነሳ ጥቁሩ ዲንጋይ እስካልጠፋ ግብፅን ማሸነፍ አንችልም እስከማለት ደረሱ።
በካፉር አል-ኢኽሺዲ ወይም በኢኽሺዲያ ስርወ መንግስት ዘመን የገንዘብ ባለቤቶች ዘካ የሚቀበልላቸው ሰው እስከመያገኙ ድረስ ድሆች ከከተማዋ ጠፉ። ሻምና ግብፅ በዓውደ ጥበብ የበለፀገ ዘመንን ኖሩ። ከአራት መቶ ሺህ በላይ ጠንካራ ሠራዊትን መልምሎ ጦሩን አደራጀ። ውብ የአትክልት ሥፍራን ገንብቶ በማራኪ መስህቦቿ ነዋሪዎቿን አጀብ የምታሰኝ ከተማ አደረጋት።
ሷሊሆችን የሚወድ፣ ለኃይማኖቱ ቀናኢ ሰው ነበር። በየሳምንቱ ረቡዕ ከመሻኢኾች ጋር ተቀማምጦ ከማይጠገብ አንደበታቸው ጥበብ ከተሞላው ዕውቀታቸው ይቀስማል። የኢስላም ሊቃውንቶችን፣ ጸሐፊዎችና ባለቅኔዎችን በእጅጉ አከበረ። ወደራሱም አስጠጋቸው። 23 ዓመታት ግዛቱን በፍትህ ሞልቶ፣ በኢስላማዊ ስነምግበር የታነፀ ትውልድን አፈራ። ግብፅን በኢልም ያበበ በአዛን ያሸበረቀ ከተማ አደረጋት።
አላህ ይዘንልህ ያ በጠል
═════════════════
ይህ የዩቱዩብ አድራሻችን ነው ሰብስክራይብ ያድርጉ
👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
http://t.me/sehkaliderashid
http://t.me/sehkaliderashid
╚═══════════════╝