╔═══════════════╗
ከ ሡልጣን ሱለይማን አልቃኑኒ
ለ ፈረንሳዩ ንጉስ የተፃፈ ደብዳቤ
╚═══════════════╝
በታላቁ ሱልጣን ሱለይማን አልቃኑኒ የአመራር ዘመን በፈረንሳይ ውስጥ ወንዶች ከሴቶች ጋር እየጨፈሩ ነው የሚል ዜና ኸሊፋው ጆሮ ዘንድ ደረሰ። በንዴት በግኖ ደብዳቤን ፃፈ። ወደ ፈረንሳዩ ንጉስም ላከ፡፡
"በሀገራችሁ ያሉ ሀፍረት የሌላቸው ወንዶችና ሴቶች በሰዎች ፊት ተቃቅፈው እየጨፈሩ እንደሆነ ሰምቻለሁ። ሀገራችሁ ከእኛ ድንበር ጎን ስላለች ይህ ጋጠወጥ ስነምግባር ወደእኛም ሊዛመት ይችላልና መልዕክቴ እንደደረሰህ በፍጥነት ይህን እርኩስ ተግባር አስቁም አለዚያ እኔው ዘምቼ ለማጥፋት ወደናንተው ሀገር እመጣለሁ"
ከዚህ ደብዳቤ በኋላ ጭፈራው በፈረንሳይ ውስጥ ለመቶ ዓመታት ሙሉ በምስጢርና በድብቅ ይከወን እንደነበረ የኦስትሪያው ታሪክ ጸሐፊ ሀመር ዘግቧል፡፡
ሱለይማን የአመራር ብቃቱ በታሪክ ድርሳናት ተገልፀዋል። ራሱ ውጊያ ውስጥ እየገባ ከጠላቶቹ ጋር በሠይፍ ይዋጋ ነበር። ወታደሮቹን ሁሉ በውጊያ ውስጥ ይቀሰቅሳቸዋል።
"እናንተ ዘማች ታጋዮች ሆይ! የአላህ ወታደር ሁኑ። ጠንክሩ በርቱ። ለዲናችሁም መስዋዕት ክፈሉ። ከፊት ለፊታችሁ ጀነትንና ሑረል ዓይንን አድርጋችሁ ተዋጉ" እያለ ይመክር ነበር።
ማንኛውም ድርጊቱን የሚከውነው በእስልምና ድንጋጌዎች ሥር ነው። ሸሪዓን በጣም ተግባራዊ ያደርጋል። ኢስላም የሚያዘውን ማንኛውንም ነገር እሱ መጀመሪያ ተግብሮ ህዝቦቹ እንዲተገብሩ ያደርጋል። በእሱ ግዛት ያሉ ሙስሊም ያልሆኑ የሌላ ኃይማኖት ተከታዮች በደልም ሆነ ግፍ አይደርስባቸውም። መመሪያው ሐቅና ፍትህ ብቻ ነው።
በግዛቱ ውስጥ ፍትህ እንዲነግስ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል። በየጊዜው ከተለያዩ አካባቢዎች ዑለማኦች ግዛቱን እንዲጎበኙና የፍትህ መጓደል ካለ መረጃ እንዲያቀርቡለት ያደርግ ነበር። በተለይ ወደ ገጠር ክልሎች እየሄደ የፍትህ ይዞታውን ይመለከታል። ፍትህ ተጓደለብን የሚሉ ሰዎችን በግንባር ያደምጣቸዋል። መፍትሔም ይሰጣቸዋል።
በለሊት ሰዓት በከተማ ውስጥ እየተዘዋወረ ይመለከታል። የሰውን ችግር በመጠየቅ ችግራቸውን ይፈታል።
"ኢስላምን ማገልገል ፍላጎቴ ነው። በክህደት መንገድ ላይ ያሉ ታጋዮች ድልን እንዲጎናፀፉ አልፈቅድም። በገንዘቤና በሕይወቴ አላህን መገዛት የምንጊዜም ትግሌ ነው። ከአላህ የሆነ ድልን ተጎናፅፌ ትልቁን ኢስላማዊ ስርወ መንግስትን ማጠናከር ምኞቴ ነው" ይል ነበር።
═════════════════
ይህ የዩቱዩብ ፔጄ ነው ሰብስክራይብ አድርገው የጀግኖችን ታሪክ ይከታተሉ
👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንታችን ነው
👇👇👇
http://t.me/sehkaliderashid
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like ☑ Comment ☑ Share ☑
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት