╔═══════════════╗
የወጣቱ ኦታ ቤንጋ ታሪክ
╚═══════════════╝
በ1883 በደኖች በተከበበው ሀገረ ኮንጎ ሞቡቲ በተሰኘ መንደር ውስጥ ኦታ ቤንጋ የተባለ ብልህ እና ደስተኛ ወጣት ተወለደ። በአካባቢው ቋንቋ ጓደኛ እንደማለት ነው።
ሀገረ ኮንጎ በንጉሥ ሊዮፖልድ በጭካኔያዊ ትዕዛዙ በርካቶችን የሚገልበት ወቅት ነበር። ያ ዘመን በእልቂቶች የታወቀ እና በአገሬው ተወላጅ ሕዝብ ላይ የበዙ ግድያዎች የተፈራረቁበት ነበር።
ኦታ ቤንጋ በልጅነት ዕድሜው አግብቶ ሁለት ልጆችን አፍርቶ ኑሮውን ይገፋው ይዟል። በአንድ ወቅት በሀያኛው ዕድሜ ውስጥ ሳለ ሪዝቅን ፍለጋ ለአደን ወጥቶ የከሰባትን ይዞ ወደ ቀዬው ሲመለስ መንደሩ በእሳት ነዶ ወድሟል። ሚስትና ሁለት ልጆቹን ጨምሮ አብዛኛው የቀዬው ነዋሪ ሞቷል። በፈረንጅ ተመራማሪዎች ቦታው ተከቧል።
ገና ከመድረሱ እጅና እግሩ በሰንሰለት ተጠፍሮ ከኋላ እየተገረፈና እየተነዳ በባርነት ይሸጥ ዘንድ ወደ አውሮፓ ምድር በባዶ እግሩ ጉዞውን ጀመረ።
በዚህ መሐል ነበር በሴንት ሉዊስ ከሚገኘው የሉዊዚያና የግዢ ኤክስፖሲሽን ጋር ውል የነበረው አሜሪካዊው ተመራማሪ ሳሙኤል ፊሊፕስ ቨርነር የተመለከተው። የዝግመተ ለውጥን ፅንሰ-ሀሳብ ለማረጋገጥ ምርምር እያደረገ የነበረበት ወቅት ነበር። የሉዊ ወርልድ ፒግሚዎችን ለማሳየት እጅግ የጠለቀ ፍላጎትና እንቅስቃሴ ነበረው። በተለይም በአፈ ታሪክ የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ሚዛን መሠረት ከቺምፓንዚዎች ከጎሬላዎችና ከኦራንጉተኖች ጋር በጣም ቅርብ ነው ይባልበት የነበረበት ዘመን ነው።
ኡታ ቤንጋ ቁመቱ አንድ ሜትር ተኩል ነው። ሳሙኤል ፊሊፕስ ቨርነር ሲመለከተው በጣም አጭር ሆኖ አገኘው። በእጅጉም ተገረመ። አልባሳትንና ጨውን ከፍሎ ከገዛው በኋላ ምርምሩን ለማድረግ ይረዳው ዘንድ ወደ አሜሪካ ይዞት ሄደ።
ቤተሰቡን፣ ሚስቱን እና ሁለት ልጆቹን በማጣቱ ከደረሰበት አሳዛኝ ሁኔታ ገና ያላገገመው ወጣት ኦታ ቤንጋ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1904 በሴንት ሉዊስ አንትሮፖሎጂካል ኤግዚቢሽን የሰው ልጅን ዝግመተ ለውጥ ታሪክ ለማሳየት በሚል በሳጠራ ውስጥ ተከልሎ ለማህበረሰቡ ክፍት ሆነ።
እ.ኤ.አ. በ1906 ከሁለት ዓመት በኋላ በኒው ዮርክ ወደሚገኘው ብሮንክስ ዙ መካነ እንስሳ አዘዋወረው። ሰዎች በተፈጥሮ ተደንቀው እንዲመለከቱት በዛፎችና በአጥሮች በተከለለ እንደ አንበሳ ግቢ በመሰለ ትናንሽ ዛፎች ባሉበት ስፍራ እንዲዘዋወርና እንዲንቀሳቀስ ተፈቀደለት።
አጭር ቁመቱና የጠቆረ መልኩ አግራሞትን ጭሮ ጎብኚዎች እሱን ለማየት እንዲጓጉና እንዲረባረቡ አደረጉት።
ይበልጥ የቱሪስትን መስህብ ይስብ ዘንድ ዝንጀሮዎች ወደሚኖሩበት የእንስሳት መካነ አራዊት ወሰዱት። በዚህ ጊዜ ነበር ኦታ ቤንጋ ሁኔታቸውን የተረዳው። ከጦጣዎች፣ ቺምፓንዚዎች እና ከጎሬላዎች ጋር “የጥንት የሰው ዘር አባት” በሚል ስያሜ ፓርኩ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ።
በወቅቱ የፓርኩ ዳይሬክተር የነበረው ዶ/ር ዊሊያም ሆርናዳይ በዚያ ስፍራ ይህን ልዩ ፍጡር በማግኘታቸው ምን ያህል እንደኮሩ ተናገሩ፡፡
ኦታ ቤንጋ እስከ 32 ዓመት ዕድሜው ድረስ እንደ ሰው ሳይቆጠር በፓርክ ውስጥ እየተጎበኘ አሳለፈ። የወደፊት ህልሙ ጨልሞ በሳጠራ ውስጥ ኑሮን መግፋት ተያያዘው።
ቀፎው ውስጥ እንደ እንሰሳ የመኖርን ጭንቀት መቋቋም ተሳነው። እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 1916 “እኔ የተከበርኩ የሰው ዘር ወንድ ነኝ ...” የሚል መልዕክትን አስፍሮ ራሱን አጠፋ። ከአንድ ጠባቂ ሽጉጥ ቀምቶ ልቡን በጥይት መቶ ራሱን ገደለ።
═════════════════
ይህ የዩቱዩብ ፔጄ ነው ሰብስክራይብ አድርገው የጀግኖችን ታሪክ ይከታተሉ
👇👇
https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንቴ ነው
👇👇👇
http://t.me/sehkaliderashid
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like ☑ Comment ☑ Share ☑
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት