ጀብደኛው፣ በአደንዛዥ ዕፅ የናወዘው፣ አምባጏሮ ወዳዱ ታይሰን አሁን የለም:: ያሁኑ ማይክ ታይሰን ሰዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ነገር እንዲያስቡ ሊያስገድድ የሚፈልገውን ድባብ ያሸነፈ ጥልቅ አሳቢ፤ ራሱን የገዛ ታላቅ ሰብእና ነው:: የዛሬውን ግጥሚያም ሆነ ሌሎች ፈተናዎች የጀግንነት ማስመስከሪያ እንዳልሆኑ ደጋግሞ ገልፆዋል:: ትግል ሁሉ ከራስ ጋር ነው፤ ድልም ያለመስካሪ የራስን ግብ መምታት ነው ይላል:: እናም ግቡ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ: የራሱ ምርጥ አቋም ላይ ሆኖ መወዳደር ነበር:: በ58 ዓመቱ ያንን ማድረግ ችሏል:: Can you be the best version of yourself? CAN YOU!? #miketyson