ፍጥረታት እንደ አፈጣጠራቸው የራሳቸው ፈጣሪ አላቸው። "የእኔ የአብራኬ ክፋይ የሆኑት ፍጥረታትም ፈጣሪያቸው እኔ ነኝ" ይላል ገሬ። በጠዋት ከተኛበት ፍራሽ ላይ ሲነሳ መጀመሪያ የሚቀናው የፈጠሩትንና እንደዚህ ዓይነት ክፉ ሕይወት እንዲኖር ያደረጉቱን ሰዎችን በመርገምና በማብጠልጠል ነው።
ገሬ ወደ ማያውቃት ወደዚች ምድር አምጥተው ስቃይና መከራ እንዲዘንብበት ያስደረጉት ቤተሰቦቹ ሂወቱን መሪር እንዳደረጉበት፣ እሱም እጁን አጣጥፎ መቀመጥ አልሆነለትም። በእጆቹ ላይ በተሰጠው መክሊት በመጠቀም የተለያየ የጥበብ ስራዎች ይሰራል። በተለያዩ ስዕሎቹ ላይ የሚታዩት ገፀ-ባህሪያት የሀዘን ናቸው። ስዕሉን ለማየት ዕድል የቀናቸው ሰዎች የስዕሉን ሃሳብ ከተረዱ በኋላ ለምን በሀዘን አለንጋ የአብራኩ ክፋይ የሆኑትን ፍጥረታት እንደሚደቁሳቸው ጥያቄ ሲያቀርቡለት። "እኔ የእነሱ ፈጣሪ ነኝ። ስለዚህ በእነሱ ማንነት ላይ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ"። በማለት የ'ሱ ፍጥረታት ለሌሎች ፍጡራን የሚያቀርቡትን ሮሮ በፈጣሪያቸው ምንም ሳይታዘንላቸው አቤቱታቸው ይወድቃል። ፈጣሪው ለፍጡሩ ካልራራለት ማንስ ሊራራት ይችላል።
ገሬም የእሱ ፈጣሪዎች እንዳልራሩለት ሁሉ፤ እሱም ለፍጥረታቱ ምንም ምሕረት አያሳያቸውም። በረሃብ፣ በሀዘን፣ በጭንቀት፣ በብቸኝነት፣ በማማረር፣ ......., ስዕሉ በሚያርፍበት ነገሮች ላይ ሁሉ ያሰቃያቸዋል!
ስዕሎቹም ቀኑ በብርሃን ወጋግታ ሲጀመር ፈጣሪያቸውን በማማረር ይጀምራሉ!
# ከምህረትዬ B.
# 2013 AKu.