ጦርነቱ በአጥቂና ተጠቂ፣ በሁለት ወገን ጦሮች ደርቷል። አንዱ የአንዱን ሃይል ለማዳከምና ለመደምሰስ የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። አከባቢው የከባድ መሳሪያ ፍንዳታ፣ የክላሺንኮቭ እሩምታ አልበቃ ብሎት የእናቶች፣ የሴቶችና የህፃናት ድምፅ መንደሩን አውኮታል። የጠላት ይሁን የወገን ጦር መሆኑ ባይታወቅም የመንደሩን ቤቶች እያቃጠሉ ነው። የተቃጠለው ተቃጥሎ የተረፈው ተርፎ ወታደሮች ወደ መጡበት ሊመለሱ ሲሉ። አንድ ህፃን ልጅ ወታደሮቹ በእነሱ ጋር ሲያልፉ, ጣቶቹን ወደ ወታደሮቹ በመጠቆም "እማዬ እነዚህ፣ እነዚህ ናቸው ቤታችንን ያቃጠሉት"? በማለት ከአለበት ጣቱን ሳያወርድ ጠየቃት። እናትም መልስ ለልጃ ሳትመልስ; የተቀሰረውን እጆቹን ከተዘረጉበት ከአነር በላቀ ፍጥነት እጆቹን መለሰችው። ጊዜው ሰው ሰውነቱን ያጣበት የዚህ ሀገር ዜጋ መሆን መረገም በሆነበት ሰዓት፤ ይሄን ጥያቄ መጠየቅ ከሞት ከፍ ያለ ሞት ያስከትላል። ማንም ይጠየቅ። ከጠያቂው ይልቅ ጥያቄው ትኩረት ተደርጎበት ቤተሰቡ ላይ ሁሉ እሳት ስለሚያወርዱ ሁሉም ለአፋ ዘበኛ አቁሞ ነው የሚንቀሳቀሰው፤ የሚናገረው። እናትየዋ ከአሁን አሁን ምን መጣብኝ ስትል ከወታደሮቹ መሃከል አንዱ የልጁን ጥያቄ ሰምቶ ኖሮ, ወደ ልጁ መለስ በማለት ቁጢጥ ብሎ በመቀመጥ, እንባው ከዓይኑ ጠብ ጠብ እያለ, "አዋ እኛ ነን ያቃጠል ነው። አዋ" በማለት ወታደሩ ልጁን እቅፍ አድርጎት ስቅስቅ እያለ አለቀሰ። አዋዋ በእኛ በእልኸኞች አዋቂዋች አማካኝነት እናንተ ንፅሁ ባህሪ ልጆችን ቤታቹን እኛ ነን ያቃጠልነው...... እስቲ ምን ላድርግል አሁን"? በማለት ወታደሩ ልጁን ወደ እቅፉ እያስጠጋው ጠየቀው??? ልጁም በልጅ አንደበቱ አፋ በሚኮላተፍ ለዛ "ለምንድነው ቤታችንን ያቃጠልከው አባባ" ለምንድነው እያለ ልጁ የወታደሩ እቅፍ ውስጥ እንደተሸጎጠ ጥያቄውን ጠየቀው....................????
ወታደሩስ ምን ብሎ ይመልስለት፥ መልሱን ቢያቀው እንኳን እንዴትስ ብሎ ለዚህ አንድ ፍሬ ልጅ፣ ምን ብሎ ያስረዳው .......................ግን ለምን ይሁን ቤቶቹን ያቃጠሉት???? ግን ለምን ይሁን በአዋቂዎች ምክንያት አላዋቂዎች የሚያልቁት????? ግን እስከ መቼ ይሁን ህፃናት ከደስታ ርችት ይልቅ የጥይት ድምፅ ሰምተው የሚያድጉት......?? ግን ለምን ይሁን ላቡን ጠብ አድርጎ የለፋው ንብረቱ ስራ በማይወዱ ግለሰቦች ምክንያት ዶግ አመድ የሚሆነው?? ግን ለምን.......????
#ከምህረትዬ B!
#2013 T E.c