👉 በዝርዝር ከሽርክ ማስጠንቀቅ እብደት አይደለም ።
ተውሒድ የሚለው ቃል የብዙዎችን ጆሮ የሚያሳምም እየሆነ መምጣቱ በጣም አሳዛኝ ነው ። ተውሒድ ማለት ለአላህ በሚገቡ የአምልኮት አይነቶች ባጠቃላይ እሱን ብቸኛ ማድረግ ወይም የአምልኮት አይነቶችን ለአላህ ብቻ አድርጎ እሱን መገዛት ማለት ነው ። እዚህ ውስጥ የአላህ ብቸኛ ፈጣሪነትና ባማሩ ስሞቹና ባህሪያቶቹ እሱን መነጠል ይገባል ።
ተውሒድ ማስተማር የምርጥ የአላህ ባሮች ተግባር ነው ። እነዚህ ምርጥ የአላህ ባሮች ነብያትና መልእክተኞች ሲሆኑ የተላኩበት ብቸኛ ተልእኮ ተውሒድን ማስተማር ነው ። የሰውን ልጅ ፍጡርን ከማምለክ ፣ ለፍጡር ከመተናነስና ከመዋረድ ፣ ለፍጡር ከማጎብደድ ፣ ለፍጡር ከመስገድና ከማጎንበስ ለፍጥረተ ዐለሙ ፈጣሪ ብቻ መተናነስ ፣ ማጎብደድና ለሱ መዋረድን ሊያስተምሩ ነው ።
ተውሒድ ማስተማር ሲባል አብዛኛው ማህበረሰብ የሚረዳው አላህ ብቸኛ ፈጣሪ ፣ ሰጪና ነሺ ፣ ህያው አድራጊና ገዳይ ፣ የሚያመሽና የሚያነጋ ፣ ፍጥረተ ዐለሙን የሚያስተናብር መሆኑን ማስተማር ብቻ ይመስለዋል ። ከዚህ ካለፈም በጥቅሉ አምልኮት ለሱ ብቻ ነው ከሱ ውጪ የሚመለክ የለም ብሎ ማስተማር የተውሒድ ጥግ መድረስ ነው ብሎ ያስባል ። የዚህን ጊዜ አብዛኛው ተከታይ ከዚህ ውጪ ምን አይነት ተውሒድ ሊያስተምር ነው ምትፈልገው ማለት ይጀምራል ።
የትኛውም ተውሒድ አስተምራለሁ የሚል አካል ማወቅ ያለበት ተውሒድ ሲባል ጥቅልና ዝርዝር ነጥቦች ያሉት መሆኑን ነው ። የተውሒድ ጥቅል ነጥቦች አላህ ብቸኛ አምላክ ነው ።ከሱ ውጪ የሚመለክ የለም የሚል ሲሆኑ ዝርዝር ነጥቦቹ ደግሞ እየአንዳንዱ ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አካላትን በዝርዝር ስማቸውን በመጥቀስ ሽርክ መሆናቸውን ማስተማር ነው ። ነገሮች በደንብ ግልፅ የሚሆኑት በተቃራኒያቸው ስለሆነ የተውሒድ ተቃራኒ የሆነውን የሽርክ አይነት በዝርዝር ስታስተምር ትክክለኛ ተውሒድ በሰዎች ልቦና ይሰርፃል ። በሀገራችን ከአላህ ውጪ የወልዮች ቀብር ተብለው የሚመለኩ የቀብር ቦታዎች ላይ አንድ ተውሒድ አስተምራለሁ የሚል ኡስታዝ በአላህ ላይ ማጋራት ትልቅ ወንጀል ነው ። በአላህ ላይ ማጋራት የለብንም ። ቀብር ማምለክ አይበቃም ቢል ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ ሊሰማው ይችላል ። ነገር ግን እዚህ ቦታ የሚደረገው ተግባር ሽርክ ነው ። እዚህ ቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ሽርክ ነው ቢል የወልዩን ስም አንስቶ እሳቸውን ድረሱልኝ ፣ እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ አሽሩኝ ማለት ከእስልምና የሚያወጣ ከባድ ሽርክ ነው ቢል ግን አላህ ካዘነለት በስተቀር አብዛኛው የዳዒውን ህይወት እስከማጥፋት ሊደርስ ይችላል ። መታወቅ ያለበት ግን እውነተኛ ተውሒድ ማስተማር ማለት ይህ ነው ።
አላህ መልእክተኛውን ሲልካቸው ከሙሽሪኮቹ ጋር ፀብ ውስጥ የከተታቸው ላት ፣ መናት ፣ ዑዛ ፣ ሁበል አይጠቅሙም ከራሳቸውም ላይ ጉዳት ማስወገድ አይችሉም እነርሱን ትታችሁ አላህን ብቻ ተገዙ ማለታቸው እንጂ ሌላ አይደለም ። ማንኛውም ወደ ተውሒድ እጣራለሁ የሚል አካል ሞዴሉ ነብዩላሂ ኢብራሂምና ነብያችን ሊሆኑ ይገባል ።
ቁርኣንን በደንብ ተደቡር ያደረገ ዳዒ በነብዩላሂ ኢብራሂምና በነብዩ ሙሐመድ የተውሒድ አስተምሮ በቂ ፋና አለው ። በመሆኑም ጥቅል ተውሒድ ማስተማርና ጥቅል ሽርክን ማስጠንቀቅ የተውሒድ አስተማሪ አያስብልም ። ስንትና ስንት ከንፈራቸውን እየመጠጡ ደርስ ላይ ቁጭ ብለው ሲወጡ በሽርክ የሚጨማለቁ ሞልተዋል ። ይህ ተውሒድና ሽርክን በዝርዝር ያለ ማስተማር ውጤት ነው ። ዛሬ ወደ ሽርክ የሚጣሩ አካላት በዝርዝር ወደ ሽርክ ሲጣሩ ሙስሊሞችን አትከፋፍሉ አልተባሉም ። አንዱ ወደ ዳና ይጣራል ። ሌላው ወደ ከረም, አሁንም አንዱ ወደ ጀማ ንጉስ ይጣራል ሌላው ወደ ዳንግላ አያበቃም አንዱ ወደ ቃጥባሬ ሌላው ወደ አብሬትና አልከሶ ከዚህ በላይ በዝርዝር ወደ ሽርክ ከመጣራት በላይ ምን አለ ? የሚገርመው ግን እነዚህ አካላት አይጠቅሙም ብሎ በዝርዝር ማስተማር ኢኽዋንና ሙመዪዓዎች ጋር ሙስሊሞችን መለያየት ነው ‼ ። ከዛም በላይ አሁን አሁን ሱሪ ያሳጠሩና ፂማቸውን ያስረዘሙ የሱና ሰው የሚመስሉትም ጭምር የዚህ አይነቱን ዳዕዋ አድራጊ እብድ ነው እንዴ እስከማለት ደርሰዋል ። ከዚህም አልፎ ቃጥባሬ ፣ አልከሶ ማለት በቁርኣን አልመጣም እየተባለ ነው ‼ ። ኢኽዋኖችና የእንጀራ ልጆቻቸው ነሲሓዎች ፊታቸውን ወደ ዱንያና ሰው መሰብሰብ ሲያዞሩና ወደ ተውሒድ በዝርዝር መጣራት ሲተዉ ይባስ ብለው በዝርዝር ወደ ተውሒድ መጣራትና ከሽርክ ማስጠንቀቅ ሙስሊሙን መለያየት ነው ሲሉ ወጣቱ ስለተውሒድ የነበረው ግንዛቤ እዚህ ደርሷል ።
አንተ የተውሒድ አስተማሪ ሆይ ኪታቡ ተውሒድን ለተበሩክ እያስቀራህ ተውሒድ እያስተማርኩ ነው እንዳትል ። መጀመሪያ ኪታቡ ተውሒድን እራስህ ተረዳው በሚገርም መልኩ ሽርክና ተውሒድን በዝርዝር ያስተምራል ። አፍራደል ሽርክና አፍራደ አትተውሒድን ለዚህ ነው የሸይኽ ሙሐመድ ዳዕዋ ያን ሁሉ የጠላት ብዥታ አልፎ ፍሬያማ የሆነው ።
አላህ ተውሒድን ተረድተው ወደ ተውሒድ ከተጣሩት ባሮቹ ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka
https://t.me/+cgN7iaP47jhmYmI8