#Update🚨
“ በሠራተኛዋ እጅ ላይ የተገኘውን ነው እንጂ ያጋራነው ከየት ነው ? የሚል ዝርዝር መረጃ የለውም ፤ እርሱ የሚቀጥል ይሆናል ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፤ ወረዳ 2 አያት ዞን 1 አካባቢ ተቀጥራ ትሰራበት ከነበረው ቤት 18 ሺሕ የአሜሪካን ዶላርና የህንድ ሩፒን ጨምሮ የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች በአጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በመስረቅ የተጠረጠችን የቤት ሠራተኛ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ ከሰዓታት በፊት መረጃ አጋርቶ ነበር።
ፓሊስ ማህበረሰቡ የቤት ሠራተኛ ሲቀጥር ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መሆን እንዳበት ያሳሰበ ሲሆን፣ መረጃው ከተጋራ በኋላ " ይህን ያህል ዶላር በአንድ ቤት እንዴት ተነኘ ? ይህስ ሌላ ምርመራ አያስፈልገውም ? የሠራተኛዋን መታወቂያ የሰጣት አካልስ ማነው ? " የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ሲንሸራሸሩ ተስተውለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የዶላሩን ምንጭና ማንነትን በደንብ አያሳይም የተባለውን የቤት ሠራተኛዋን መታወቂያ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን ጠይቋል።
ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን ምላሽ ሰጡ ?
“ ጥሩ ነው እንደዚህ አይነት መነጋገሪያ መሆኑ ሰው በደንብ እንዲያነበውና ጥንቃቄ እንዲያደርግም ይጋብዛል። ዞሮ ዞሮ አሁን ጥሬ ምርመራ ላይ ያለን ጉዳይ መረጃ ነው ለህብረተሰቡ ያጋራነው።
በጣም በርካታው የከተማው ነዋሪ ሠራተኛ ስለሆነ ሥራውን የሚያቀለው አብዛኛው በሠራተኛ ነው፤ ብዙው ሰው ተሯሯጭ ስለሆነ። ስለዚህ ዞር ብሎ ሠራተኞቻቸውን የሚያዩ፣ ያስያዙትን መታወቂያ ቼክ የሚያደርጉ፣ ፎርጅድ ከሆነም ለምን? ብለው የሚያስይዙ አናሳ ናቸው።