➧ሸይኽ ረቢዕ አል መድኸሊ ተጠየቁ ፡ጥያቄ፦ ቤት ለመግዛት ፈልጌ ነበርና ከወለድ ባንክ ብር ተበድሬ ቤቱን መግዛት ይፈቅድልኛልን ?
መልስ፦ ፍፁም አይፈቀድም። ሌላው ይቅርና እንኳን ቤት ለምትገዛበት አይደለም በጣም ርቦህ ነፍስህን ከሞት ለማትረፍ ዳቦ ገዝተህ መብላት ቢያስፈልግህንኳን አደራህን ከወለድ ባንክ ስባሪ ፍራንክ እንዳትበደር !
በጣም ከራበህና ከአጠገብህ የምትበላው ሀላል ነገር አጥተህ ሞት አፋፍ ላይ ከሆንክ ፡ በዚህ ጊዜ በክትም ሆነ የአሳማ ስጋ ካገኘህ እንድትበላ አላህ ፈቅዶልሀል ምክንያቱም ሌላ የምትበላው ሀላል ነገር ሳታገኝ ቀርተህ ህይወትህ ልትጠፋብህ ስለሆነ ፡
ነገር ግን የፈለገ ህይወትህ አደጋ ላይ ብትሆንም እንኳን የወለድ ብር እንድትበላ አልፈቀደልህም ! ይህ የሚያሳየው የወለድ ብር ምን ያክል ከባድ አደጋ እንዳለው ነው።
አደራ የወለድ ብር እንዳትበደር ሶብር አድርግ ታገስ ፡ አላህን ፈርተህ የወለድ ብር አልበላም ብለህ ሶብር ካደረግክና ከታገስክ እርሱ ካላሰብክበት ቦታ ጥሩ ሪዝቅ (ሲሳይ) ያመጣልሃል ፡
አላህ እንዲህ አለ፦ አላህን የሚፈራን ሰው ለእርሱ መውጫ ያደርግለታል ፥ ካላሰበበትም ቦታ ሪዝቅን (ሲሳይን) ይሰጠዋል ።
ሱራ አል-ጦላቅ (65/2-3)
እንዳጠቃላይ ወለድ በጣም ከባድ ወንጀል ነው፣ በጣም ከባድ አደጋ ነው ፣ ወለድ መብላት ይቻላል የሚል ሰው ይከፍራል (ከእስልምና ይወጣል) ።
ቤት ካስፈለገህ ሶብር አድርግ ታገስ አላህ ከሲሳዩ እስኪሰጥህ ድረስ፣ ወደ አላህ ተጠጋ ተመለስ ከዚያም ቤት እንድትገዛ የሚያደርጉህን ሰበቦች ሁሉ አድርስ ፣ አይ አልታገስም የወለድ ገንዘብ ተብድሬ ቤቴን እገዛለሁ ካልክ ግን ከአላህ ጋ ጦር ከፍተህ እርሱን እየተዋጋህ ነው ያለኸው ፡ ምክንያቱም የወለድ ብር የሚበላ ሰው አላህን ተዋጊ አማፂ ነውና ፡
ይሄን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ብሏል፦ እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! አላህን ፍሩት ፡ ከአራጣም (ከወለድም) የቀረውን ተው፣ አማኞች እንደሆናችሁ ከርሱ ተጠንቀቁ።
የታዘዛችሁትን የማትሰሩ ከሆናችሁ ግን ከአላህ እና ከመልዕክተኛው በሆነች ጦር መዋጋታችሁን እወቁ ።
ሱራ አል በቀራህ (27278-279)
አላህ ወለድ የሚበሉ ሰወች ላይ ጦርነቱን አውጆባቸዋል።
እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ "የወለድ ገንዘብ የሚበላን ሰው፣ የሚያስበላውንም ፀሀፊውንም መስካሪዎቹንም" ረግመዋቸዋል።
ከእርግማን ቡሀላ ምን ትፈልጋለህ ?!! ፊትለፊትህ የጀሀነም እሳት እየጠበቀህ ይህ ከወለድ ተበድረህ የገዛሀው ቤትህ ሊጠቅምህ ይችላል ??!
ስለዚህ ማንኛውም ሙዕሚን አላህን ሊፈራ ይገባል ፡ በድህነቱ ሶብር ሊያደርግና ሊታገስ ይገባል ።
ጌታችን አላህ እንዲህ ብሏል፦ በፍርሀት፣ በርሀብም እንዲሁም ከገንዘቦችና ከነፍሶችም ከፍራፍሬወችም በመቀነስ በእርግጥ እንፈትናችኋለን ! ታጋሾችንም (በጀነት) አብስራቸው።
ሱራ አል በቀራህ (2/155)
በድህነትህ ታገስ አላህ ይሄን ታላቅ ምንዳ ይሰጥሃል ። ይሄን አልፈልግም ብለህ ሳትታገስ ከቀረህና የወለድ ገንዘብ ከበላህ ግን የእርሱን ቁጣና እርግማን እንዲሁም ከባድ ቅጣቱን ነው ምታተርፈው ።
ነገ ከአላህ ዘንድ ከሚጠብቅህ ከባድ ቅጣትና ቁጣ አንፃር ሲታይ ዛሬ ያለህበትን ድህነትህን መቻልና መቋቋም በጣም ቀላል ነው ።
አላህ ከትሩፋቱ ለግሶን የወለድ ብር ከመብላት እንዲጠብቀን እንማፀነዋለን ፡ ጌታችን ዱዓችንን (ፀሎታችንን) ሰሚና ተቀባይ ነው።
المصدر : موسوعة مؤلفات ورسائل وفتاوى الشيخ ربيع المدخلي
المجلد الأول
رقم الصفحة 134-135
..🖋𝓱𝓾𝓼𝓮𝓷 𝓪𝓱𝓶𝓮𝓭
፞ •⊰✿🌹✿⊱• ፞
⚘••..¦ t.me/TewhidSunnah