እንዲሁ ወደደን
"እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"(ዮሐ 3:16)
እግዚአብሔር ሳያፈቅር አይኖርም። በእርሱ ዘንድ የፍቅር ባለጸግነት አለ። የእርሱ ፍቅር በቃላት ክምችት የማይገለጽ፣ መጡኑ፤ ስፋቱ፤ ጥልቀቱ፤ እርዝመቱ ይሄን ያህላል ተብሎ የማይታወቅ ነው።
እርሱ ሲያፈቅር ከልኬት በላይ፤ ከሁኔታ በላይ ነው። እርሱ አለሙን በሙሉ የወደደው እንዲሁ ነው።
ሲወደን ታሪካችን ማርኮት፤ ምግባራችን ስቦት አይደለም።እንዲሁ ያለ መስፈርት ወደደን።
እርሱ የመውደዱን ጥግ ያሳየን አንዲያ ልጅን ስለእኛ አሳልፎ በመስጠት ነው። የሚወደውን ልጁን፤ ደስ የተሰኘበትን ልጁን ለእኛ ሲል ለሞት አሳልፎ ሰጠው። ልጁ በመስቀል ላይ ስለእኛ ኃጢአት በሆነ ጊዜ ፊቱን ሰወረበት፤ ከጩኸቱ ድምፅ ርቆ ቆመ። እርሱ ለእኛ ሲል በገዛ ልጁ ጨከነ። ለእኛ ሲል ልጁ ያለልክ ዝቅ እንዲል ፈቀደ።
የእርሱ ፍቅር ከመናገር ብቻ ሳይሆን ከማሰብም በላይ ነው። እርሱ ሁለመናው በፍቅር የተሞላ። እርሱ ያለመታከት ዘወትር የሚወድ ነው። ያለ ዋጋ እንዲህ በልጁ በኢየሱስ የወደደን አምላክና አባት እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ። አሜን።
👇👇👇👇👇👇👇
Join now
✝✝✝✝✝✝✝✝
📥Group :
@slehiywetkal 👈
📥Channel :
@slehiywet 👈
✝✝✝✝✝✝✝✝