🇵🇱🇮🇱 ፖላንድ ኔታንያሁን እንደምታስር ገለጸች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መታሰርን በመስጋት ኦሽዊትዝ ነፃ የወጣበትን 80ኛ ዓመት መታሰቢያ እንደማይታደሙ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።
ጋዜጣው አክሎም የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዝግጅቱ ላይ እንደማይገኙና የእስራኤል የትምህርት ሚኒስትር ዮአቭ ኪሽ ብቻ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
የፖላንድ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ውላዲስላው ባርቶስዜቭስኪ፤ ሀገራቸው ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ እንደምትገዛ በመግለጽ፤ ኔታንያሁ ወደ ፖላንድ የሚመጡ ከሆነ እስር ይጠብቃቸዋል ማለታቸውን የፖላንድ ጋዜጣ ሬዝፖስፖሊታ ጽፏል።
በጋዛ ሰርጥ በፈጸሙት የጦር ወንጀል አይሲሲ ኔታንያሁ እና የቀድሞው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia