🇿🇲 በዛምቢያ በኤምፖክስ በሽታ የተያዘ ሁለተኛው ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
"ከኒዴኬ፣ ኪትዌ የመጣች የ34 ዓመት ሴት ላይ ሁለተኛው የኤምፖክስ ( የዝንጀሮ ፈንጣጣ) በሽታ ትናንት የተገኘ ሲሆን ተጠቂዋ የሰውነት ገጸ መቀየር፣ ትኩሳት፣ ከጎሮሮ እና ከመዋጥ የተያያዙ ችግሮችእና የአፍ ውስጥ ቁስለቶች ምልክቶች ታይተውባታል። ቀደም ሲል በሰሜን ምዕራብ ግዛት በሉሙዋና እያለች በተሳሳተ ምርመራ በቺክንፖክስ መያዟ ተገልጿል። ሆኖም፣ በጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 26፣ 2024፣ በላቦራቶሪ ምርመራዎች በኤምፖክስ መያዟን ተረጋግጧል" ሲሉ የዛምቢያ የጤና ሚኒስትር ዳግላስ ሳይካሊማ በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ።
📍በሰሜናዊ ዛምቢያ በኪትዌ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኒዴኬ ወረዳ ውስጥ ንክኪ ያላቸውን ሰዎችን ለመከታተል እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመከላከል ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ተሰማርቷል። ስምንት የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች በምርመራ ላይ ናቸው እና ከፍተኛ ክትትል በመላ ወረዳዎች በመካሄድ ላይ ነው ብለዋል ሳይካሊማ።
ኤምፖክስ ለዛምቢያ ድንበር ተሻጋሪ ስጋት ሆኖ ቢቆይም ተጨማሪ ስርጭትን ለመከላከል እና ህዝቡን ለመጠበቅ የትብብር ስራ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አፅንዖት ሰጥተዋል።
🧪 በሀገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያው በሽታው በሰሜናዊው ድንበር ከተማ ናኮንዴ በኩል ወደ አገሪቱ የገባ የታንዛኒያ ዜጋ ላይ በጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 10 መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት አድርጓል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia