🇪🇹😱⛰ በፈንታሌ ተራራ ታይቶ የማይታወቅ የሜቴን ጋዝ ልቀት ተገኘ
🛰 የሳተላይት ምሥሎች በፈንታሌ ተራራ "ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተለመደ" የሜቴን ጋዝ ልቀት እንዳገኙ ኒው ሳይንቲስት መጽሔት ዘግቧል። ግኝቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለውና ለወራት የዘለቀውን የእሳተ ጎመራ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመጣ ነው። የሚቴኑ መገኛ ምንጭ እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፤ መጠኑ ከፍተኛ መሆኑ ሳይንቲስቶችን አስገርሟል።
የሜቴን ልቀቱን ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 120 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በተከሰተው የእሳተ ጎመራ አቅራቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ የለየው የአውሮፓ ሕብረት ሳተላይት ነው። ግኝቱን ተከትሎ የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀቶች ክትትል አገልግሎት በሰራው ምርመራ፤ ከእሳተ ጎመራው የሚለቀቀው
ሜቴን በሰዓት 58 ቶን ያህል መጠን እንዳለውና ይህም በየቀኑ ከ20 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ገደማ የድንጋይ ከሰል ቃጠሎ ጋር እንደሚወዳደር አረጋግጧል።
የመጊል ዩኒቨርሲቲ የእሳተ ገሞራ ተመራማሪ ጆን ስቲክስ እንዳስረዱት፤ እሳተ ገሞራዎች በተለምዶ እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ሰልፈር ዳይኦክሳይድ ያሉ ጋዞችን የሚለቁ ቢሆንም፤ በዚህ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የሚቴን ልቀት ብዙ ጊዜ እንደማያጋጥም ጠቁመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia